ዘምዘም ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የሥራ ፈቃድ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ከብሔራዊ ባንክ በይፋ ተረክቧል፡፡ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል በተደረገው ሥነ ሥርዓት ፈቃዱን የባንኩ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሊካ በድሪ ከብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ ተረክበዋል፡፡ ወ/ሮ መሊካ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን እስከ ምክትል ፕሬዚዳንትነት የመሩና የ30 ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ አሁን ላይ የባንክ ኢንዱስትሪውን ከሚመሩ ፕሬዚዳንቶች ብቸኛ ሴት ያደርጋቸዋል፡፡ ዘምዘም ባንክ በ1.7 ቢሊዮን ብር የተፈረመ ካፒታል የተቋቋመ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ ባንክ ነው፡፡ ፎቶዎቹ የሥነ ሥርዓቱን ከፊል ገጽታዎች ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -