Sunday, June 23, 2024

ክቡር ሚኒስትሩ ለካቢኔ ሊያቀርቡት በነበረው ሰነድ ዙሪያ ከአማካሪያቸው ጋር የጀመሩት ውይይት ከአጀንዳው ወጥቶ በሌላ ጉዳይ ላይ አተኩሯል

 • ነገ ለሚኒስትሮች ካቢኔ የምናቀርበውን የሕግ ሰነድ የተመለከተ ማብራሪያ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • የነገው ፕሮግራም መተላለፉን አልነገሩህም እንዴ?
 • አልሰማሁም። በምን ምክንያት?
 • ጠቅላዩ ወደ ምዕራብ በመሄዳቸው ተላልፏል።
 • ከአገር ሲወጡ ድምፅ አጥፍተው ሆነ እንዴ? 
 • አልወጡም። እዚሁገር ውስጥ ወደ ምዕራብ ከእንግዳ ጋር ናቸው፡፡
 • እንግዳ?
 • የኤርትራው ፕሬዚዳንት ናቸው?
 • ኢሱ !… እሳቸውማ እንግዳ አይደሉም፡፡ 
 • ታዲያ ምንድን ናቸው?
 • ቤተኛ
 • ፌዘኛ እኮ ነህ አንተ! ለማንኛውም የልማት ሥራዎችን በጋራ እየጎበኙ ነው፡፡ 
 • የልማት አሉኝ? 
 • እንደዛ ነውሚዲያዎች እያስተላለፉት እኮ ነው፡፡ 
 • ጉብኝቱ ሽፋን ነው። ሰውዬው የሚመጡት ለሌላ ጉዳይ ነው። 
 • ሌላው ጉዳይ ምንድን ነው?
 • ለታችኞቹ የሚሆን መላ ለመፈለግ ራቅ ማለታቸው እንጂ ጉብኝቱ እንኳን ሽፋን ነው። 
 • እሳቸውን የመረጡት ለምን ይመስልሀል?
 • ታችኞቹ የሚያደርጉትን ብቻ አይደለም የሚያስቡትንም የሚያውቁት እሳቸው ብቻ ናቸው። 
 • አሃ?!
 • ለዛ እኮ ነው እሳቸው በመጡ ቁጥር የታችኞቹ የተለመደውን ቃል ተጠቅመው መግለጫ የሚያወጡትና የሚብከነከኑት? 
 • የተለመደው ቃል ምንድን ነው? 

[ሚኒስትሩ ዘንድሮ እንዲካሄድ የተወሰነውን አገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ ምርጫውን ከሚያስፈጽመው አካል ኃላፊ ጋር በስልክ እየተወያዩ ነው] 

 • ለኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ መሠረት የሚሆን፣ በንፁህ የሕዝብ ድምፅ ብቻ ሥልጣን የሚያዝበት ምርጫ እንዲሆን ነው ፍላጎታችን፡፡ 
 • ክቡር ሚኒስትር ይህ የእኛም ፍላጎት ነው። ስብዕናችን የሚፈቅደውም ይህንኑ ነው፡፡ ነገር ግን…
 • ከነገር ግን በኋላ የሚመጣ ሐሳብ አይስማማኝም… ግን ልስማው እስቲ 
 • የገጠመንን አስቸጋሪ ሁኔታ ከመናገር ውጪ አማራጭ የለንም ክቡር ሚኒስትር፡፡ 
 • ምንድን ነው የገጠማችሁ ችግር?
 • ሰሞኑን ያሳለፋችሁት ውሳኔ ነው፡፡ 
 • ችግሩ እናንተ ናችሁ እያሉኝ ነው?
 • ለችግሩ ባለቤት መፈለግ የእኛ ሥራ አይደለም ነገር ግን መንግሥት ያሳለፈው ውሳኔ የምንፈልገውን ምርጫ ለማካሄድ ችግር ፈጥሮብናል …
 • የችግሩ ባለቤት ማን እንደሆነ እየነገሩኝ እኮ ነው… ለመሆኑ የትኛው ውሳኔ ነው?
 • የፌዴራል መንግሥት ተቋማት ከትግራይ ክልል ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ አይችልም በሚል የተላለፈው ውሳኔ ነዋ!
 • ይህ ውሳኔ ከእናንተ ጋር ምን ያገናኘዋል? 
 • ተቋማችን ገለልተኛ ሆኖ ቢደራጅም የፌዴራል መንግሥት ተቋም ነው በተጨማሪም…
 • በተጨማሪ ምን?
 • ውሳኔው የትግራይ ክልል ምክር ቤትንና የክልሉ መንግሥትን ሕጋዊ አይደሉም ብሏል። 
 • እና ትክክል አይደለም እያሉኝ ነው?
 • እሱ አይመለከተንም። ይህ ውሳኔ እያለ በትግራይ ክልል እንዴት ምርጫ ማካሄድ እንደምንችል ነው የተናገርነው?
 • አልገባኝም?
 • የክልሉ መንግሥት ሕገወጥ በመሆኑ የፌዴራል መንግሥት ዕውቅና የለውም እንዲሁም የፌዴራል ተቋማት ከትግራይ ክልል ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ አይችሉም ተብሏል። እኛ ደግሞ ምርጫውን ለማካሄድ ከክልሉ የመንግሥት መዋቅር ጋር መነጋገር የግድ ይለናል። የክልሉ የፀጥታ ኃይል ጋር መነጋገር የግድ ይለናል። ይህ ባልተሟላበት ሁኔታ በዚህ ክልል ምርጫ ማድረግ እንቸገራለን።
 • ይህንን ችግር ብላችሁ ማሰባችሁ ይደንቃል! ከክልሉ ሌሎች መዋቅር ጋር አትሠሩም?
 • ከየትኞቹ?
 • ከወረዳዎች። ቀበሌዎችም ዞኖችም አሉ አይደል? ፀጥታን በተመለከተስ ቢሆን ከልዩ ኃይሉ ጋር አትሠሩም?
 • አልተረዱኝም መሰል ክቡር ሚኒስትር? 
 • ተረድቻለው። በደንብ ነው እንጂ የገባኝ!
 • ምንድን ነው የገባዎት? 
 • የገባኝንማ ያውቁታል። የክልሉ ገዥ ፓርቲንስ ቢሆን ዝም ያላችሁት ለምን ሆነና?
 • የክልሉን ገዥ ፓርቲ ምን ማድረግ ነበረብን?
 • ሕገ መንግሥቱን ጥሶ የተካሄደውን የክልሉ ምርጫ ማነው እንዲዘጋጅ ያደረገው? በዚህ ከእናንተ ዕውቅና ውጪ በተካሄደ ምርጫ ተወዳድሮ አሸነፍኩ ያለውስ ይኸው ገዥ ፓርቲ አይደለም?
 • ልክ ነው። ግን ይህንን የመከላከል ሥልጣን የእኛ ተቋም ኃላፊነት አይደለም።
 • ራሳችሁ አዘጋጅታችሁ ባፀደቃችሁት የምርጫ ሕግ መሠረት እንደዚህ ዓይነት ፓርቲ ሕጋዊ ዕውቅና ይዞ መቀጠል ይችላል?
 • አይችልም።
 • እና ለምን አልሰረዛችሁትም? 
 • መሠረዝ እኮ አሁንም ይቻላል ቀላል ነው። 
 • እና ምነው ከበዳችሁ?
 • ከዛ በፊት ግን በክልሉ ምርጫ እንዳይካሄድ ማድረግ እየተቻለ ምርጫው ሲካሄድ ዝም ብሎ የተመለከተው፣ የፈቀደው መንግሥት አይደለም? 
 • ለክልሉ ሕዝብ ስንል ነዋ? 
 • እነሱም ነገሮችን ከማባባስ ብለው ትተውት ነው ብለው ለምን አላሰቡም? 
 • ለምን አስባለው፣ ፍላጎታችሁ ምን እንደሆነ እየገባኝ?
 • ምንድን ነው ፍላጎታችን?
 • እናንተ የምታሸንፉበት ምርጫ መሆኑን ማረጋገጥ። 
 • እኛ ማሸነፍ የምንፈልገው አንድ ነገር ነው? 
 • ምንድን ነው?
 • ሕዝብ ያለ ተፅዕኖ የሥልጣን ባለቤት የሚሆንበት ምርጫ ማካሄድ፡፡ 
 • እና ይህንን ለምን አታደርጉም?
 • እሱን ለማድረግ ለፓርላማው የውሳኔ ሐሳብ እናቀርባለን።
 • የምን ውሳኔ ሐሳብ?
 • በትግራይ ያለው ሁኔታ እስኪፈታ ምርጫው እንዲራዘም የሚል ውሳኔ ሐሳብ! 

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...