Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናዓቃቤ ሕግ ሃብታቸውን ላላስመዘገቡ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፃፈ

ዓቃቤ ሕግ ሃብታቸውን ላላስመዘገቡ ሚኒስትር ዴኤታዎችና የከተማ አስተዳደር ባለስልጣናት የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ፃፈ

ቀን:

– በወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ በተባሉና ከተፈረደባቸው ተከሳሾች 412 ሚሊዮን ብር በድርድር ተቀበለ
– የአቶ ልደቱ አያሌውን ዋስትና በሚመለከት ስልጣኑ የክልሉ ነው አለ

የፌደራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን የፌደራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት ባለስልጣናት ሃብታቸውን እንዲያስመዘግቡ አዋጁን መሠረት አድርጎ በተለያየ ጊዜ ያቀረበውን ጥሪ ከቁብ ያልቆጠሩ አሥር ሚኒስትር ዴኤታዎችና በርካታ የከተማ አስተዳደሩ ባለስልጣናት ከቅጣት ጋር ሃብታቸውን ባጭር ጊዜ እንዲያስመዘግቡ  የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማስጠንቀቂያ ፃፈ።
ዋና ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ጌዴዮን ጢሞቴዎት ዛሬ ከአንድ ሰዓትበፊት በሰጠት የሦስት ወራት የመስራቤታቸው የሥራ አፈፃጸም ሪፖርት ላይ እንዳብራሩት፣ ኮሚሽኑ ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለስልጣናትን ሥም ዝርዝር አሳውቋል። ተቋማቸውም አዋጁን መሰረት አድርጎ ከቅጣት ጋር ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያስመዘግቡ ደብዳቤ ጽፎላቸዋል። የማያስመዘግቡ ከሆነ ሕጉን ጠብቀው ሕግ የማስከበር ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ዓቃቤ ሕግ አደረጃጀቱን በማሻሻል ሦስት የነበሩትን የምክትል ጠቅላይ ዓቃቤያነ ሕግ ወደ አራት ከፍ በማድረግ አሰራሩን ማጠናከሩን ጠቁመው አዳዲስ ዳይሬክቶሬቶች መደራጀታቸውን ገልጸዋል። ዓቃቤ ሕግ በወንጀል ክስመስርቶባቸው በክርክር ከተረቱ ፍርደኞች 412 ሚሊዮን ብር በድርድር እንዲመልሱ መደረጉን ጌዴዮን(ዶ/ር) ተናግረዋል።
የዋስትና መብት ቢከበርላቸውም ሊለቀቁ ስላልቻሉት የኢዴፓ አመራር አቶ ልደቱ አያሌው የተጠየቁት ዋና ዓቃቤ ሕጉ፣ የሳቸው ጉዳይ በክልል የተያዘ በመሆኑ ማብራሪያ መስጠት የሚችለው ክልሉ መሆኑን ጠቁመዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...