ማረሚያ
የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ‹‹የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ለከተማዋ በቀን ለማቅረብ ያቀደው የውኃ መጠን በግማሽ መቀነሱን አስታወቀ›› በሚል ርዕስ ሪፖርተር በረቡዕ ዕትሙ የዘገበ ቢሆንም፣ ባለሥልጣኑ የተሰጠው መግለጫ ሙሉ ሐሳብ ከአጠቃላይ እውነታው የራቀ በመሆኑ እንዲስተካከል ጠይቋል፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣኑ በመግለጫው ያስታወቀው፣ የማምረት አቅሙ በቀን 575 ሺሕ ሜትር ኪዩብ ቢሆንም፣ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት በየዕለቱ እያመረተ የሚያሠራጨው 544 ሺሕ ሜትር ኪዩብ መሆኑን ገልጿል፡፡ የከተማዋ ፍላጎት ግን በቀን 1.2 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ መሆኑን በመጠቆም አንባቢያን በዚህ መሠረት እንዲረዱት ተስተካክሏል፡፡ ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡