Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊደንበኞችን ያሳተፈው የሽልማት ዕጣ

ደንበኞችን ያሳተፈው የሽልማት ዕጣ

ቀን:

በዘመናዊ መልኩ ደንበኞችን ለመሳብ ከሚፈጽሙት ሒደቶች መካከል የተለያዩ ሽልማቶችን በማዘጋጀት ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም ዋነኛ ተዋናዮች ባንኮች ናቸው፡፡ ‹‹ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ›› በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባንኮች ለደንበኞች የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት አካሄደዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንዱ ነው፡፡

ለ20ኛ ጊዜ ባዘጋጀው የውጭ ምንዛሪ ግኝት ማበረታቻ ፕሮግራም የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገቢ ንግድ ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ቱፋ እንደተናገሩት፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝትን ለማሳደግና ለማበረታታት ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ ለደንበኞች ሽልማት ማዘጋጀት ነው፡፡ ከውጭ አገር ገንዘብ በሐዋላ በማስላክ፣ በባንኩ በኩል የውጭ አገር ገንዘብ እንዲዘረዝሩ በማድረግና የስዊፍት አድራሻ ሲቢኢቴታ በመጠቀም የሚላኩ የውጭ አገር ገንዘቦች በባንኩ በኩል እንዲያልፍ እየተሠራ መሆኑን አቶ ተካልኝ ተናግረዋል፡፡

የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱም ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በብሔራዊ ሎተሪ ቅጥር ግቢ ውስጥ የተከናወነ ሲሆን፣ ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል የሚያስገኘው አንደኛው የዕጣ ቁጥር 7834834 ሆኗል፡፡ በሁለተኛ ዕጣ ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ የሚያስገኙ ሁለት ቁጥሮች ደግሞ 78237609 እና 7906744 ሆነው መውጣታቸው ተገልጿል፡፡ 

ይህ መርሐ ግብርም ደንበኞች ከውጭ የሚላክላቸው ገንዘብ በሕጋዊ መልኩ በባንክ በኩል እንዲያደርጉና እንዲመነዝሩ ለማበረታታት ነው ተብሏል፡፡ በቀጣይም ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ላይ ‹‹ይቆጥቡ ይሸለሙ›› በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ሽልማቶች እንደሚከናወኑ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የዓባይ ባንክ ለሦስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የሽልማት የዕጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓት ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ያካሄደ ሲሆን፣ በዕለቱ የዓባይ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ዋና የሪቴል ባንኪንግ መኮንን አቶ በለጠ ዳኘው እንደገለጹት፣ የማኅበረሰቡን ችግር ለመቅረፍና ልማቱን ለማሳደግ እየሠሩ ላሉ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

ዓባይ ባንክ ‹‹ይቀበሉ፣ ይመንዝሩ፣ ይሸለሙ›› በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀውና ባወጣው ዕጣ የመጀመርያዎቹን አምስት ደረጃዎች ያገኙ አሸናፊዎች ተለይተዋል፡፡  የአንደኛው ዕጣ አሸናፊ የሆነው ቁጥር 8870 ዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል ሲሸለም፣ ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ደረጃ ዕጣ አሸናፊ ለሆኑት እንደ ቅደም ተከተላቸው  አምስት የማቀዝቀዣ ማሽኖች (ፍሪጅ)፣ ኮምፒውተሮች (ላፕቶፕ)፣ ቴሌቪዥንና  የሞባይል ስልክ ቀፎዎችን አግኝተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...