Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአቶ ልደቱ አያሌው የተመሠረተባቸው ክስ ተነበበላቸው

አቶ ልደቱ አያሌው የተመሠረተባቸው ክስ ተነበበላቸው

ቀን:

ኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በአቶ ልደቱ ላይ የመሠረተውን የወንጀል ክስ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በንባብ አስምቷቸዋል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በአቶ ልደቱ ላይ የመሠረተው ክስ፣ ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ አስበው፣ ሕገ መንግሥቱን በሚቃረን ሁኔታ የሽግግር መንግሥት ማቋቋም የሚሉ ሰነዶችን ማዘጋጀት መሆኑንም ታውቋል፡፡

አቶ ልደቱ ክሱ ከተነበበላቸው በኋላ የክስ መቃወሚያ ካላቸውና የሚያነሱት የመብት ጥያቄም እንዳላቸው ተጠይቀው፣ መቃወሚያ እንዳላቸው በመግለጻቸው ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ በመሆኑም የክስ መቃውሚያቸውን ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

- Advertisement -

አቶ ልደቱ ጥቅምት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበባቸው ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል ክስ ላይ የዓቃቤ ሕግ ሦስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡፡ በተሰጠው ምስክርነት ላይ ብይን ለመስጠት ለጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ሸዋ ዞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ አቶ ልደቱ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የሰጠው ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ፣ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ ኃላፊ ቀርበው እንዲያስረዱ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንዲያቀርባቸው የታዘዘው ኃላፊ በሌላ ኃላፊ በመቀየራቸው ሳይቀርቡ መቅረታቸው ታውቋል፡፡

በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የቢሾፍቱ ፖሊስ መምርያ ወንጀል ምርመራ ኃላፊንና የመምርያው ኃላፊ ለምን እንዳልቀረቡ እንዲያስረዱ እንዲያቀርብና ኮሚሽኑም አቶ ልደቱን በቀጥታ ከእስር እንዲፈታቸው በድጋሚ ትዕዛዝ ቢሰጥም፣ አቶ ልደቱ አለመፈታታቸውን የኢዴፓ ሊቀመንበር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...