Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየእግር ኳስ ፌዴሬሽን ሠራተኞቹ የሕግ አውጪና አስፈጻሚ ድርብ ሚና እንዳይኖራቸው ዕግድ ጣለ

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ሠራተኞቹ የሕግ አውጪና አስፈጻሚ ድርብ ሚና እንዳይኖራቸው ዕግድ ጣለ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሠራተኞቹ የሕግ አውጪና የሕግ አስፈጻሚ ተደራራቢ የኃላፊነት ሚና እንዳይኖራቸው በመመርያ ዕግድ መጣሉን አሳወቀ፡፡ ተቋሙ በዋናነት በፌዴሬሽኑ አመራርነት ላይ የሚገኙና የእግር ኳስ ጨዋታዎችን በታዛቢነት የሚመሩ ኮሚሽነሮች እና የእግር ኳስ ዳኞች አንደኛውን ኃላፊነት ሊመርጡ ይገባልም ብሏል፡፡

በፌዴሬሽኑ ይፋ የሆነው አዲሱ መመርያ በውሳኔ አሰጣጥና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያሉ መጣረሶችን ያስቀራል በሚል ከወዲሁ ተስፋ እንደተጣለበት የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

ባለፉት ዓመታት በፌዴሬሽኑ የሕግ አውጪና የሕግ አስፈጻሚነት ድርብ ሚና በመያዝ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ባለሙያዎች፣ መመርያው ከመተግበሩ በፊት ረቂቅ መመርያው ለሙያተኞች ቀርቦ በውይይት ሊዳብር እንደሚገባው የሚጠይቁ በርካታ ናቸው፡፡ ይሁንና ጉዳዩን በሚመለከት ሪፖርተር ያነጋገራቸው የፌዴሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ “ይህ ድርብ የኃላፊነት ሚና ለፌዴሬሽኑም ሆነ ለእግር ኳሱ ዕድገት እንቅፋት ከመሆኑ ባሻገር፣ ግልጽና ተጠያቂነት እንዳይኖር ያደርጋል፤” በማለት የተቋሙን አካሄድ ይደግፋሉ፡፡

“ከመመርያ ጋር ተያይዞ ለምን ቅሬታዎች እንደሚቀርቡ ግልጽ አይደለም፤” የሚሉት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በበኩላቸው፣ መመርያው በዋናነት ተቋሙ ውስጥ የአመራርነት ድርሻ ያላቸው ሙያተኞች ከ2013 የውድድር ዓመት ጀምሮ አንዱን መምረጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በአመራርነት እየሠሩ የሚገኙ ባለሙያተኞች ውድድሮች ሲኖሩ “ለጨዋታ ታዛቢ ዳኝነትና ለእግር ኳስ ዳኝነት” በሚል ሰዎቹ ሳምንትና ከዚያም በላይ ቆይታ ሲያደርጉ በመደበኛው የዕለት ዕለት ሥራቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት ሲፈጥር መቆየቱን የሚናገሩት ኃላፊው፣ ክፍተቱን ለመድፈን መመርያው ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው ያስረዱት፡፡

በአቶ ኢሳያስ ጅራ የሚመራው ብሔራዊ ፌዴሬሽን ዘንድሮ ተግባራዊ እንደሚደረጉ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል፣ ከሁለት አሠርታት በላይ በፌዴሬሽኑ አማካይነት ሲተዳደር የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ በሊግ ካምፓኒ እንዲመራ ያደረገበት አሠራር በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡         

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...