Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናባለስልጣናት የፍርድ ውሳኔዎችን ሳያወላዱ እንዲያስፈጽሙ ጠቅላይ ሚንስትሩ አሳሰቡ

ባለስልጣናት የፍርድ ውሳኔዎችን ሳያወላዱ እንዲያስፈጽሙ ጠቅላይ ሚንስትሩ አሳሰቡ

ቀን:

– ባለስልጣናት ለግል ክብር ብለው ሚዲያዎች እንዳይተቿቸው መከልከል የለባቸውም ብለዋል

የአስፈጻሚው መንግስት ባለስልጣናት የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን ማክበር እና ሳያወላዱ መፈጸም እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚንስትር ዓበይ አህመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህንን የተናገሩት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የመንግስታቸውን የ2013 ዓም ትኩረት የሚደረግባቸውን ዓበይት ተግባራት ባስደረዱበት ወቅት ነው።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በወቅቱ ከምክር ቤቱ አባላት ከቀረቡላቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ የህግ የበላይነትን የተመለከተ ሲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ምላሽም የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ረገድ ክፍተት መኖሩን አምነዋል።

የህግ የበላይነት አለመኖር እና የፍትህ እጦት እርሳቸውን ወደ ስልጣን ካመጡ ጉዳዮች አንዱ እንደሆነ ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፤ እርሳቸው የሚመሩት የለውጥ ኃይል የፍትህ ስርዓቱን ከፖለቲካ ጫና እንደሚያወጣ ቃል የገባ ቢሆንም የዚሁ የለውጥ ኃይል የሆኑ አስፈጻሚዎች አሁንም በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጫና እያደረሱ መሆናቸውን አምነው ይፋ በማድረግ ማሳሳቢያ ሰጥተዋል።

አስፈጻሚው አካል የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን እያከበረ እና እያስፈጸመ እንዳልሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፤ ” አንዳንዱ ወንጀለኛ ይደብቃል ፣ አንዳንዱ ደግሞ የፍርድ ቤት ውሳኔ አያከብርም ሲታዘዘም አይፈጽምም” ሲሉ ተችተዋል።

ይህ አካሄድ መቀየር እንዳለበት ያሳሰቡት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፤ የአስፈጻሚው አካል አመራሮች ፍርድ ቤት የሚሰጣቸውን ውሳኔዎች ምንም ሳያወላዱ መቀበልና መፈጸም ይገባቸዋል ብለዋል።

“እኛ ያላከበርነውን ፣ ያልታዘዝነውን ፍርድ ቤት ነፃ እና ገለልተኛ ሁን ማለት ከንቱ ነው። ከቆምንለት ፍላጎትም የሚቃረን ነው” ሲሉ በግሳጼ መልክ ተናግረዋል።

በተጨማሪም አስፈጻሚው መንግስትን የሚቀላለቀሉ ባለስልጣናት ስለ ግል ስም እና ክብር እንዲሁም ዝና መጨነቃቸውን መተው እንዳለባቸው መክረዋል።

ባለስልጣናት ስለ ግል ስም እና ክብር መጨነቃቸውን ትተው ሰዎች እንዲሁም ሚዲያዎች እንዲተቿቸው መፍቀድ እንዳለባቸው የመከሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ፤ ሚዲያዎች አንዱን በአንዱ ላይ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ ከሆነ ብቻ በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ የሚፈለገውን ዲሞክራሲያዊ ባህል ለመገንባት የተሻለ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በፌዴራልና በትግራይ ክልል መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ፤ የፌዴራል መንግስት የትግራይ ህዝብን ከተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ለይቶ አይመለከትም በዚህ ረገድም ችግር አለመኖሩን ገልጸው ፤ ችግሩ ያለው በክልሉ ከፍተኛ የስልጣን አካል ላይ ከተቀመጠው ስብስብ ጋር መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ ኃይል ጋር የሚያያዘው ጉዳይም በህግና በህግ ብቻ እንደሚወሰን እና በዚህ ጉዳይ ላይ የፌዴራሉ ስራ አስፈጻሚ መንግስት ሚና የሚሆነው የፌዴሬሽን እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች ህግን ተከትለው የሚወስኑትን ጉዳይ እንደሚያስፈጽም ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...