Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እንዳይፀድቅ ጥያቄ...

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት እንዳይፀድቅ ጥያቄ ቀረበ

ቀን:

ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በአገልግሎት ላይ የቆየውን ‹‹የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ›› እንዲተካ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ይሁንታን አግኝቶ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁለት ሳምንታት በፊት የቀረበው ‹‹የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ረቂቅ›› እንዳይፀድቅ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ጥያቄውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው፣ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ሲሆን፣ ረቂቁ እንዳይፀድቅ ጥያቄ ያቀረበው፣ በቀረበው ረቂቅ የወንጀል ሕግ ሥነ ሥርዓት ድንጋጌዎች ላይ መሻሻል፣ መስተካከልና እንደ አዲስ መካተት ያለባቸው ነጥቦች ስላሉ መሆኑን በመጥቀስ ነው፡፡ የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ጠበቃ ፊሊጶስ ዓይናለም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ እንደ ሕግ ባለሙያ ረቂቁን ሲፈትሹት ወይም ሲያነቡት ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች መስተካከል፣ መታረምና ያልተካተቱት መጨመር አለባቸው፡፡ ምክንያቱም ሕጉ ከፀደቀ በኋላ ለዘመናት የሚያገለግል መሆን ስላለበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ረቂቁ ሕግ በ1954 ዓ.ም. ፀድቆ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ለ58 ዓመታት ሲያገለግል የቆየና በማገልገል ላይ ያለን ሕግ የሚተካ መሆኑን የገለጹት አቶ ፊልጶስ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ ሕግ፣ ከአራት ጊዜ በላይ የተረቀቀና ለአሥር ዓመታት ውይይት ተደርጎበት የነበረ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ከለውጥ በኋላ የተቋቋመው የሕግና ፍትሕ ማሻሻያ ምክር ቤት ከተቋቋመ በኋላ እንደገና ታይቶና ለውይይት ቀርቦ በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ መሆኑንም አቶ ፊልጶስ ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 እና 21 ድንጋጌዎች ስለ የሕግ አማካዎች (ጠበቆች) ደንግጎ የሚገኝ ሆኖ ሳለ፣ አዲሱ ረቂቅ ሕግ ሥነ ሥርዓት ግን ስለጠበቆች ያለው ነገር እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

ረቂቁ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ዓቃቤ ሕግንና ፖሊስን አካቶ እያለ ለፍትሕ ሥርዓቱ ከፍተኛ ዕገዛና ድጋፍ የሚሰጠውን ጠበቃ ሳያካትት መቅረቱ ትክክል ስላልሆነ፣ ሊታረምና መካተት እንደሚገባውም አስረድተዋል፡፡

ረቂቁ በትርጉም ክፍሉ ስለ ተከላካይ ጠበቃ ትርጉም ሲሰጥ እንኳን ጠበቃን ዝም ብሎ ማለፉ፣ ‹‹ጠበቆች የፍትሕ አካሉ አይደሉም›› እንደማለት ስለሆነ፣ በደንብ ታይቶ ሊታረም እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡ ረቂቁ በጣም ብዙ በጎ ነገሮች እንዳሉት ጠቁመው፣ ለዓቃቤ ሕግና ለፖሊስ የሰጠው ሥልጣን ሰፊ ከመሆኑ አንፃር ግዴታም ሊጥልበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ከፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅም ጋር ስለሚጋጭ በደንብ ሊታይ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ፍርድ ቤት፣ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግና በጋራ ዕቅድ አውጥተው እንዲሠሩ የሚደነግገው ክፍል፣ የፍርድ ቤቶችን ነፃነት የሚገፉ በመሆኑ ሊታሰብበትና በደንብ ሊታይ እንደሚገባም መክረዋል፡፡ በረቂቁ የተጠቀሱ ድንጋጌዎች እርስ በርሳቸውና ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋርም ስለሚጋጩ፣ የሕግ ባለሙያዎች ተወያይተውና ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ሳይሰጡ እንዳይፀድቅ፣ ምክር ቤቱ የውይይት መድረክ እንዲያዘጋጅላቸው በደብዳቤ  መጠየቃቸውን አቶ ፊልጶስ ተናግረዋል፡፡ ጉዳዩ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑን ጠቁመው፣ ‹‹የፍትሕ ሥርዓት ማስከበር ከሕግ አወጣጥ ስለሚጀምር ረቂቁ በደንብ መፈተሽ አለበት፤›› ብለዋል፡፡

ለክልል በፌዴራል የሚሰጠው ሥልጣን፣ ስለባህላዊ የዕርቅ መፍቻ ዘዴዎች፣ ስለዋስትና መብት፣ ስለግባኝና ሌሎችም በረቂቁ የተጠቀሱ ድንጋጌዎች ጥልቅ ውይይትና ዕይታ ስለሚፈልጉ፣ በተለይ የሕግ ባለሙያዎች ሳይወያዩበት እንዳይፀድቅ መጠየቃቸውን ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ምክር ቤቱ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንፃር ተመልክቶ ሐሳባቸውን እንደሚቀበላቸውም ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...