Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበምርጫ ዝግጅት ወቅት የምርጫ ሥርዓት ለውጥ ማድረግ አገራዊ ምርጫውን ሊያራዝም ይችላል ሲል...

በምርጫ ዝግጅት ወቅት የምርጫ ሥርዓት ለውጥ ማድረግ አገራዊ ምርጫውን ሊያራዝም ይችላል ሲል ምርጫ ቦርድ ሥጋቱን ገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ውሳኔ ተከትሎ፣ በ2013 ለሚደረገው የምርጫ ዝግጅት እየተደረገ ባለበት ወቅት፣ የምርጫ ሥርዓቱን መለወጥ ምርጫውን ሊያዘገየው ይችላል የሚል ሥጋት እንዳለው ገለጸ፡፡

ይህንኑ ጉዳይ በማስመልከት ለውይይት መነሻ ሐሳብ ይሆን ዘንድ በማለት ቦርዱ በምርጫ ዓመት ውስጥ የምርጫ ሥርዓቱ ላይ የሚደረጉ የተወሰኑ ለውጦች በአጠቃላይ የምርጫ ሒደቱ ተዓማኒነትና ተቀባይነት፣ አካታችነትና ወቅታዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊጥሉ እንደሚችሉ ሥጋቱን ገልጿል፡፡ ምንም እንኳን በምርጫ ሥርዓቱ ላይ ሊደረጉ የሚችሉ ለውጦች ላይ ግልጽ መረጃ ባይኖርም፣ የተመጣጣኝ ውክልና ሥርዓትን በመጨመር የምርጫ ሥርዓቱን ወደ የቅይጥ ሥርዓት የመቀየር ይህም ማለት አሁን ከሚገኘው የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 54 ከተቀመጠው በአብላጫ ድምፅ የሚገኙ መቀመጫዎች በተጨማሪ በተመጣጣኝ ውክልና ተጨማሪ፣ መቀመጫዎችን የመጨመር አሠራር ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል፤›› ሲል ግምቱን አስቀምጧል፡፡ የምርጫ ሥርዓትን መቀየር የምርጫ ሥርዓቱ የሚተዳደርባቸውን ሕጎች በሰፊው መቀየርን እንደሚጠይቅ የሚገልጸው የዳሰሳ ጥናቱ፣ ‹‹በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ የምርጫ ኦፕሬሽን ዲዛይንን መከለስ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎችን አደረጃጀት ክለሳን እንዲሁም ስለምርጫ ሥርዓቱ ሰፊ ትምህርት የመስጠት ዘመቻንም ጭምር ሊያካትት ይችላል፤›› ብሏል፡፡

አዲስ የምርጫ ሥርዓት በሚታሰብበት ወቅት ሥርዓቱ በተለይ በህዳጣን ማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እጅግ በጣም ገጠራማ በሆኑ ቦታዎች፣ ዝቅተኛ የማንበብና መጻፍ ችሎታ ባላቸው ማኅበረሰብ ክፍሎች፣ እንዲሁም በሴቶች ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅዕኖ መገምገም አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል፡፡ ምክንያቱም ሲያስቀምጥ፣ በማሻሻያ ከሚመጣው ከአዲሱ ሥርዓት ጋር በቀላሉ ለመዋሃድ አስቸጋሪ በመሆኑ በአዲሱ የምርጫ ሥርዓት ውስጥ ውክልናቸው አነስተኛ ሊሆን እንደሚችል አመላክቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔ ቁጥር16 (2013) በያዝነው ዓመት 2013 ዓ.ም. (እስከ ነሐሴ ወር 2013 ዓ.ም. ድረስ) ምርጫ እንዲከናወን የወሰነውን ውሳኔ የተመለከተ ነው፡፡ ሕገ መንግሥት የማሻሻል ሒደት የሚጀመር ከሆነ፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳው በውሳኔው ላይ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚያልፍ ሲሆን፣ የምርጫ ቅድመ ዝግጅቶችን በአፋጣኝ መቀጠል ካልተቻ ለቦርዱ ከላይ የተጠቀሰውን የምክርቤቱን ውሳኔ እንዳያከብር ሊያደርገው ይችላል፡፡ በዚህም መሠረት አዲስ ውሳኔ መወሰን ሊያስፈልግ ይችላል፤›› ሲልም ምክረ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ከፍተኛ የበጀት ፍላጎት የሚኖረው ዝግጅት ስለሚደረግ ተፅዕኖ ሊኖረው ይችላል የሚለው የምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ ማከናወንም ከተለመደው ጊዜ በላይ እንዲወስድ ሊያደርገው እንደሚችል አመላክቷል፡፡

የምርጫ ሥርዓት ማሻሻያ መላ አገሪቷን የሚመለከት በመሆኑ፣ ከተለያዩ የማኅበረሰብ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚገባ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገ፣ ‹‹አገራዊ ምርጫን በታለመለት በ2013 ዓመት ለማካሄድ ከታሰበ የምርጫ ሥርዓት ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ መከናወን እንዳለበትና የሚደረገው ለውጥም የምርጫ ኦፕሬሽን ላይ ከፍተኛ ለውጥ የማያስከትል መሆን ይኖርበታል፤›› በማለት ይመክራል፡፡

በምርጫ ዓመት የምርጫ ሥርዓቱ ለውጥ ማድረግ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በጣም አሳሳቢ ቢሆንም፣ ሊኖሩ የሚችሉትን ትክክለኛ ለውጦች መሠረት በማድረግ ተፅዕኖውን መቀነስ እንደሚቻል፣ ነገር ግን መዘግየትንም ሊፈጥር እንደሚችል፣ ነገር ግን መዘግየትም ሊፈጠር እንደሚችል በመጥቀስ ቦርዱ ሥጋቱን አቅርቧል፡፡

‹‹ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል የሚደረጉ ሒደቶች ሊገመቱ የማይችሉ ሲሆኑ፣ ምርጫን ለማድረግ የሚያስችል አስተማማኝ የሕግ ማዕቀፍ ያለመኖር ደግሞ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመነጋገር የምርጫውን ትክክለኛ የጊዜ ሰሌዳ ለመወሰን የሚስቸግርና የምርጫ ዝግጅት ሥራዎችንም መሥራት ለመጀመር አስቸጋሪ የሚያደርግ ነው፤› ሲልም ብርዱ ይፋ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት አመልክቷል፡፡

ቦርዱ የዳሰሳ ጥናቱን ለምን እንዳደረገ ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ ሶልያና ሽመልስ በሰጡት ምላሽ፣ “የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት እየካሄደ በመሆኑ እና ቀጣዩ ውይይትም በምርጫ ጉዳይ ላይ እንደሚሆን በመገለጹ ፤ ምርጫን አስመልክቶ በሚካሄዱ ውይይቶች ላይ የኛ ግብአት እንዲካተት ስለፈለግን ነው” ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...