Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልዩኔስኮ በነአሸንዳ አሸንድዬ ሻደይ ወካይ ቅርስነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ

ዩኔስኮ በነአሸንዳ አሸንድዬ ሻደይ ወካይ ቅርስነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ

ቀን:

ኢትዮጵያ፣ በትግራይና በአማራ ክልሎች በሚገኙ ብሔረሰቦች ዘንድ የሚከበረው የልጃገረዶች የአደባባይ ክብረ በዓል፣ በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገቡላት ያቀረበችውን ጥያቄ የሚመረምረውና ውሳኔ የሚሰጠው የሚቀጥለው ዓመት መሆኑ ታወቀ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የኢንታንጀብል ባህላዊ ቅርስ ክፍሉ በድረ ገጹ እንዳስታወቀው፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ፣ ዓይኒዋሪ፣ ማርያ፣  ሻደይ፣ ሶለል በመባል የሚጠራውን የልጃገረዶች ክብረ በዓል አሥራ ስድስተኛ ስብሰባውን እ.ኤ.አ. በ2021 ኖቨምበር/ዲሴምበር ወር (ኅዳር 2014 ዓ.ም.) በሚያካሂድበት ጊዜ ከሌሎች 60 ፋይሎች ጋር ይመለከታቸዋል፡፡

ከእነዚህ ፋይሎች ውስጥ ከአፍሪካ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ካሜሩን፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ኬንያ፣ ማዳጋስካር፣ ማሊ፣ ሞሪታኒያ ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ሲሸልስ፣ ሱዳን፣ (ከሌሎች የመካከለኛ ምሥራቅ አገሮች ጋር በጋራ ግብፅ፣ ሱዳን፣ ቱኒዝያ አልጄሪያ)  የተለያዩ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶቻቸውን ለውሳኔ አቅርበዋል፡፡

- Advertisement -

ዩኔስኮ በነአሸንዳ አሸንድዬ ሻደይ ወካይ ቅርስነት ላይ ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ ያዘ

ባህላዊ የሴቶች ነፃነት ቀን

የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ለዩኔስኮ በላከው ሰነድ ላይ እንደተገለጸው፣ አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ዓይኒዋሪ፣ ማርያ፣ ሻደይ፣ ሶለል (Ashenda Ashendye Aynewari Maria Shadey Solel) በመባል የሚጠራው ይህ የልጃገረዶች ክብረ በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ መሠረት ያለው ሲሆን፣ የፍልሰታ ጾም ፍቺን ተከትሎ ልጃገረዶች በቡድን በቡድን እየሆኑ ወገባቸው ላይ የአሸንዳ/አሸንድዬ/ሻደይ ተክል አስረው የሚጫወቱት እንደ ባህላዊ የሴቶች ነፃነት ቀን የሚከበር የአደባባይ ክብረ በዓል ነው፡፡ ይህ በዓል በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ከነሐሴ 16 ቀን ጀምሮ ይከበራል፡፡

“ይህ የልጃገረዶች/የሴቶች ክብረ በዓል በአማራና ትግራይ ክልሎች በሰፊው ከሚተገበሩ ባህላዊ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በአማራ ክልል ዋግኽምራ አካባቢ ሻደይ፣ በላስታ ላሊበላና ጎንደር አካባቢዎች አሸንድዬ እንዲሁም በራያ-ቆቦ ሶለል በመባል ሲጠራ፤ በትግራይ ክልል እንደርታና ተምቤን አካባቢዎች አሸንዳ፣ በአክሱም ዓይኒዋሪ እና በዓዲግራት ማርያ በመባል በሰፊው ይከበራል፡፡ ክብረ በዓሉ ሴቶች ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ነፃ በመሆን ያለምንም ገደብ በመንቀሳቀስ በነፃነት ከአቻዎቻቸው ጋር እንዳሻቸው የሚጫወቱበት፣ ባህላዊ ክብረ በዓል ከመሆኑ የተነሳ እንደ ባህላዊ የሴቶች ቀን የሚከበር ትውፊታዊ የልጃገረዶች/የሴቶች በዓል ነው፡፡

“በበዓሉ ትግበራ ጊዜ ሴቶች ወገባቸው ላይ ከሚያስሩት ተክል መጠሪያ በመነሳት አሸንዳ፣ አሸንድዬ፣ ሻደይ በመባል በትግርኛ፣ በአማርኛ እና በኸምጣንኛ ቋንቋዎች የሚጠራ ቢሆንም በተለይ በምሥራቅ አማራ ራያ-ቆቦ አካባቢ ከግዕዝ ግስ በመነሳት ሶለል በመባል ሲታወቅ፣ በማዕከላዊ ትግራይ በአክሱም አካባቢ ዋሪ ከምትባል ወፍ መጠሪያ በመነሳት ዓይኒ-ዋሪ እንዲሁም በምሥራቃዊ ትግራይ በዓዲግራት አካባቢ ደግሞ ማርያ በመባል ይታወቃል፡፡

“አሸንዳ/አሸንድዬ/ሻደይ የሁለት ነገሮች ስያሜ ነው፡፡ የመጀመርያው በበዓሉ ጊዜ ሴቶች ተልትለው በገመድ ወባቸው ላይ የሚያስሩት ስር ነጭ ሆኖ ሌላው ክፍሉ አረንጓዴ የሆነ የኮባ ቅጠል ትልትል የመሰለ ተክል ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ልጃገረዶች/ሴቶች በቡድን በቡድን እየሆኑ የሚጫወቱት ባህላዊ ጨዋታ ስያሜ ነው፡፡ በተለይ በኸምጣንኛ ቋንቋ ‘ሻ’ ማለት ሳልስት (ሦስት) ማለት ሲሆን ‘ደይ’ የሚለው ደግሞ ‘-ቱ’ የሚለውን ቅጽል የሚወክል ሲሆን ይህም ሰልስቱ እንደማለት ሲሆን የድንግል ማርያምን እርገት በዓል (የፍልሰታ ጾም ፍቺን) ምክንያት በማድረግ ለሦስት ቀናት የሚከበር የልጃገረዶች ጨዋታ ነው፡፡

ነሐሴ 16 ቀን ከሚከበረው የቅድስት ማርያም በዓል ጋር የተያያዘው ክብረ በዓል ከዋዜማው እስከ ማግስት ልጃገረዶች የአሸንዳ ቅጠልን አሸርጠው አደባባይ በመውጣትና በየቤቱ በመዞር እየጨፈሩና እያዜሙ ያከብሩታል፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ የበዓሉ መገለጫ በሆኑ አልባሳትና መጋጊያጫዎች ተውበው ይታዩበታዋል፡፡ የፀጉር አሠራራቸው ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፣ ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው አደባባይ የሚውሉበት ነው፡፡ ጌጣ ጌጣቸውም ልዩ ልዩ ዓይነት ሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ፣ መስቀል ሲሆን፣ አለባበሳቸውም በመልጉም /ጥልፍ ቀሚስ/ ሹፎን፣ ጃርሲ ይታጀባል፡፡

የአሸንዳ መንፈስ፣ በፀጉር አሠራርና በአልባሳት፣ በመዋቢያ ቁሶችና በመጋጋጪያዎች ብቻ አይደለም የሚገለጠው፣ እርሱን የሚያገዝፉ የሚያጎሉ የተለያዩ ዘፈኖች ይገኙበታል፡፡ 

ለሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት

ከዓመታት በፊት በመቐለው አሸንዳ በክብር እንግድነት ተገኝተው የነበሩት  የዩኔስኮ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው እንግዳ፣ ዩኔስኮ የሴቶች በዓል የሆነው አሸንዳ አከባበር ልዩ ትርጉም እንደሚኖረው በምክንያትነት ያብራሩት፣ ‹‹የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥና የአፍሪካ አኅጉርን መደገፍ ድርጅቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የትኩረት አቅጣጫ በመሆናቸው ነው፤›› በማለት ነበር፡፡

የነሐሴውን ክብረ በዓል የሰው ልጆች ድንቅ የባህል ቅርሶች ወካይ የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ ለማስመዝገብ እንዲቻል ሁለቱም ክልሎች ባለፉት ዓመታት ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርበው በጋራ ሲያስጠኑ ነበር፡፡ የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች የሠሩት ጥናትም ታትሞ መቅረቡ ይታወሳል፡፡

 የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን ለአንድ አገር ቢያንስ በየሁለት ዓመት ልዩነት ውስጥ የሚመዘግበው ዩኔስኮድረ ገጽ እንዳመለከተው እ.ኤ.አ. 2020 በወካይ ቅርስ ፋይሎች ውስጥ ለኅዳር 2013 .. ለውሳኔ ከሚታዩት 42 ፋይሎች ውስጥ ኢትዮጵያ የለችበትም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...