Thursday, June 1, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ዕጩ የሚያደርገው የፈጠራ ሐሳብ ውድድር በመጪው ወር ይካሄዳል

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዘንድሮ ለአምስተኛ ጊዜ የሚካሄደውና ‹‹አፍሪካ ፊንቴክ›› የተሰኘው የፈጠራ ሐሳብ ጉባዔ ተሳታፊዎች፣ በኦንላይን የሚታደሙበት አግባብ በኅዳር ወር እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ተቀማጭነቱ በአሜሪካ የሆነው ‹‹ዴድለስ ግሎባል›› የተሰኘ አማካሪ ኩባንያ ትኩረቱን በኢትዮጵያ ላይ ካደረገውና ‹‹አይቤክስ ፍሮንቲዬር›› ከተሰኘ ሌላ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር፣ ፍሎውለስ በተሰኘው አገር በቀል ድርጅት አሰናጅነት የሚካሄደው ጉባዔ፣ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው አካላትን ጨምሮ ሌሎችም በክፍያ የሚታደሙበትና አንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለሚያስገኘው ውድድር የሚታጩበት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

አዘጋጆቹ ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ መሠረት፣ ጉባዔው በዲጂታል ዘዴ ለአራት ቀናት ይካሄዳል፡፡ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ተሳታፊዎችም ሐሳቦቻቸውን በአጭሩ የሚያስረዳ ሰነድ ከወዲሁ በኦንላይን ማስገባት የሚችሉበት ድረገጽ በኩባንያዎቹ አማካይነት ተሰናድቶ፣ ምዝገባ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ‹‹አፍሪካ ፊንቴክ ሰሚት›› በሚል ርዕስ በተሰናዳው ድረገጽ አማካይነት ከ500 በላይ ታዳሚዎች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል ተብሏል፡፡ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ የተካሄደው ይህ ጉባዔ፣ ከ30 በላይ አገሮችን የወከሉ 400 ተሳታፊዎች በተገኙበት ተከናውኖ ነበር፡፡

ዘንድሮ በሚካሄደው የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ጥምር በሆነው የጀማሪ ድርጅቶችና የፈጠራ ሐሳብ ባለቤቶች ጉባዔ፣ በዳሸን ባንክ በኩል የዲጂታል ክፍያ ማስተግበሪያ በሆነው አሞሌ አማካይነት እንደሚፈጸም ሲገለጽ፣ ለኢትዮጵያውያን ተሳታፊዎች ከ1850 እስከ 6475 ብር እንደየታሳታፊዎች ምርጫ መሳተፍ እንደሚችሉ ሲገለጽ፣ ሌሎች ከ95 ዶላር እስከ 225 ዶላር በመክፈል መሳተፍ እንደሚችሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ጀማሪ የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ሥራዎቻቸውን ወይም አዳዲስ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ተሳታፊዎች ተወዳድረው፣ አሸናፊዎቹ ሽልማት የሚያገኙበትና በካሊፎርኒያ ግዛት ሲሊከን ቫሊ ውስጥ በሚካሄድ ዝግጅት ላይ የመታደም ብሎም በዚያው በሚሰናዳው ዓለም አቀፍ የጀማሪ ንግድ ሥራዎች የዋንጫ ውድድር ላይ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለማግኘት መሳተፍ የሚችሉበት ዕድል እንደያዘ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች