Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በነደፈው የቀውስ ጊዜ እስትራቴጂ መሠረት ትምህርት ያስጀምራል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በነደፈው የቀውስ ጊዜ እስትራቴጂ መሠረት ትምህርት ያስጀምራል

ቀን:

የ8ኛ እና 12 ኛ ክፍል ትምህርት ነገ ይጀመራል

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመንን የሚያስጀምረው በቢሮው የተነደፈውን የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ መሠረት አድርጎ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ኮሮና ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት በነበረው የትምህርት አሰጣጥ ሥርዓት መቀጠል እንደማይችል ያስታወሰው ቢሮው፣ የዘንድሮን ትምህርት ለማስጀመር አማራጭ የቀውስ ጊዜ የትምህርት አመራርና አስተዳደር ስትራቴጂ ነድፎ በከተማዋ በሚገኙ የመንግሥትና የግል ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንዲደረግ መሠራቱን ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2013 ዓ.ም. የትምህርት ዘመንን የትምህርት አጀማመር አስመልክቶ የተዘጋጀው ሰነድ፣ ትምህርተ ቤቶች፣ አመራሮችና ወላጆች እንዲፈጽሙት የሚጠበቀው የቀውስ ወቅት የትምህርት ስትራቴጂ ወላጆች ያለ ሥጋት ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንዲልኩ ተማሪዎችም ተረጋግተው እንዲማሩ የሚያስችል መሆኑን አመላክቷል፡፡

በአንድ የትምህርት ፈረቃ ከአንድ ሺሕ ተማሪዎች እንዳይበልጥ፣ ትምህርት ቤቶችን በተደጋጋሚ በኬሚካል ማፅዳት፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ፣ የሙቀት መለኪያ መኖር፣ ከንክኪ የፀዳ የመማር ማስተማር ሥራ ማከናወን፣ ሳኒታይዘርና የእጅ ንፅህና አቅርቦትን በማረጋገጥ፣ ትምህርት ቤቶች የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ነገ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ትምህርት የሚያስጀምሩ ሲሆን፣ ጥቅምት 30 ደግሞ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ፡፡

የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከኅዳር 21 እስከ 23 ቀን፣ የ12 አገር አቀፍ ፈተና ከኅዳር 28 እስከ ታኅሳስ 1 ቀን 2013 የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ትምህርት አከፋፈትን አስመልክቶ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም. መግለጫ የሰጡት የቢሮው ኃላፊው አቶ ዘለዓለም ሙላቱ፣ ኮሮና ወረርሽኝን ተከላክሎ መማር ማስተማሩን ለማስቀጠል 230 ትምህርት ቤቶች ተገንብተው ለአገልግሎት እንዲበቁ እንደሚደረግ፣ በ513 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 2,052 የጤና ባለሙያዎች ቅጥር መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

ነገ ትምህርት በሚጀመርባቸው ትምህርት ቤቶች ፀረ ተህዋስያን መረጨቱን፣ የሙቀት መለኪያና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛም ለሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተሠራጨ መሆኑን አክለዋል፡፡

በ2012 በዓለም ከመቶ 90 በላይ አገሮች ላይ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት 1.6 ቢሊዮን ያህል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተስተጓጉለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከ26 ሚሊዮን፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ከ950 ሺሕ በላይ ተማሪዎች የገጽ ለገጽ ትምህርት ላለፉት ዘጠኝ ወራት ተቋርጧል፡፡ 

የትምህርት ቤቶችና ሌሎች ማዘውተሪያ ቦታዎች መዘጋትም ተማሪዎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የዓለም ጤና ድርጅት መግለጹ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...