Sunday, July 14, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሞባይል መተግበሪያን የሚጠቀመው ‹‹ወዬ›› የከተማ ጭነት ትራንስፖርት ሥራ ጀመረ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ጂኢቲ አይቲ ሶሉሽን የተሰኘው ኩባንያ በሞባይል መተግበሪያና በነፃ የስልክ መስመር አማካይነት አገልግሎት ማግኘት የሚቻልበትን የከተማ ውስጥ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ለሚገኙ ከተሞች መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ ነዋሪዎች የጭነት ተሸከርካሪ ፍለጋ መባዘን የለባቸውም የሚለው ኩባንያው፣ ‹‹ወዬ›› በሚል ስያሜ ያበለፀገውን የሞባይል መተግበሪያና ነፃ የስልክ መስመር በመጠቀም የጭነት ትራንስፖርት (የሎጂስቲክስ) አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በጋሻው ባይለየኝ (/) ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ለማንኛውም ዓይነት የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ለትልልቅና አነስተኛ የግንባታ  ተቋራጮች፣ የመኖሪያ ቤታቸውንም ሆነ የሥራ ቦታቸውን ለሚቀይሩም ሆነ ማናቸውም ዓይነት ንብረታቸውን ከቦታ ቦታ ማጓጓዝ የሚፈልጉ  ነዋሪዎች ጭነታቸውን ከቦታ ቦታ ለማጓጓዝ የጭነት አመላላሽ ተሽከርካሪዎችን ፍለጋ መንከራተት ሳይጠበቅባቸው የእጅ ስልካቸውን በመጠቀም በወዬ የሞባይል መተግበሪያ እንዲሁም በአጭር የስልክ መቀበያ አማካይነት በወዬ ሎጂስቲክስ ሥር የታቀፉ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎችን ያሉበት ቦታ ድረስ መጥራት እንደሚችሉ አስታውቋል።

የጭነት አገልግሎት ፈላጊዎች በመጀመሪያ “woye” የተሰኘውን መተግበሪያ ከጉግል ፕለይ ስቶር ወደ ስልካቸው በመጫን እንዲሁም 7380 አጭር የስልክ ጥሪ ላይ በመደወል በአቅራቢያቸው የሚገኙ የጭነት ተሽከርካሪዎችን መጥራት እንደሚችሉ ድርጅቱ አስታውቋል። 

ድርጅቱ ‹‹ወዬ›› በሚል መጠሪያ ያቀረበውን መተግበሪያ ስልካቸው ላይ የጫኑ ወይም 7380 በአጭር የስልክ ጥሪ በመደወል ለጭነታቸው ዓይነትና መጠን ይስማማል ያሉትን የመኪና ዓይነት በመምረጥ  በፍጥነት አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ኃላፊው አስረድተዋል።  

‹‹ወዬ›› የሎጂስቲክስ አገልግሎት ማንኛውንም ዓይነት የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት ኃላፊው፣  ከወደፊቱ የአገልግሎት ማስፋፊያ ዕቅዶቹ ውስጥ የፈሳሽ ጭነቶችን እንዲሁም መንገድ ላይ ብልሽት ያጋጠማቸውን ተሽከርካሪዎች የማንሳት አገልግሎት እንደሚካተቱ አስረድተዋል። 

‹‹ወዬ›› የከተማ ሎጂስቲክስ ወይም የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ወደ ሥራ ከመግባቱ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በሚገባ ማጥናቱን የተናገሩት ኃላፊውበጥናቱ የተገኘው ውጤትም የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ፈላጊዎችና አገልግሎቱን ሰጪዎች በቀላሉ እንደማይገናኙና አገልግሎት ሰጪዎችም መሥራት ከሚችሉት አቅም በታች እንደሚሠሩ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ወዬ የሎጂስቲክስ አገልግሎት ይህንን አሠራር በዘመናዊ መልኩ የሚቀይር ከመሆኑ ባሻገርተመጣጣኝ ዋጋ የሚከፈልበት፣ አስተማማኝና ቀልጣፋ የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል። 

በተለምዶ  የጭነት ማጓጓዝ አገልግሎቱን የሚሰጠው አሽከርካሪ የሚያስከፍለው ዋጋ፣ ጭነቱን ካደረሰ በኋላ ያለጭነት ወይም ባዶውን የሚመለስበትን ጉዞም አጠቃሎ የነበረ ቢሆንም ይህንን አሠራር በማዘመን አንድ ተሽከርካሪ ጭነቱን ካወረደ በኋላ እንደቀድሞው ወደ መነሻ ቦታው ባዶውን ስለማይመለስ፣ የተሽከርካሪዎቹን የሥራ ምልልስ በመጨመር ገቢያቸውንም በዚያው ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸዋል። 

በመሆኑም ጥቅሙ ከተገልጋዮችና ከትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው ባለፈ፣ የንግድ ሥርዓቱ ቀልጣፋ እንዲሆን፣ የግንባታ ሥራዎች የግብዓት አቅርቦት ፈጣን እንዲሆን በማድረግ የንግድ ዘርፉ ወጪ እንዲቀንስ ታስቦ የተጀመረ ዘመናዊ አገልግሎት እንደሆነ በገበያ ጥናቱ ወቅት በግልጽ መለየቱን ተናግረዋል። 

ወዬ የጭነት ትራንስፖርት የሚያስከፍለው ዋጋ እንደ ተሽከርካሪው ዓይነት በተለያየ የመነሻ ዋጋበኪሎ ሜትር እንደሚወሰን የገለጹት ኃላፊው፣ ጭነቱን ለመጫንና ለማውረድ የሚፈጀው ደቂቃ ወይም ሰዓት በዋጋ ስሌቱ ውስጥ እንደሚካተት ጠቁመዋል። 

በአሁኑ ወቅት  ከሞተር ሳይክል፣ ፒክ አፕና ቫን ጀምሮ እስከ ትልልቅ የጭነት ተሽከርካሪዎች  ‹‹ወዬ›› የጭነት አገልግሎት ድርጅት ሥር ተመዝግበውና አሽከርካሪዎችም ለተሻለ የደንበኛ አያያዝ እንዲረዳ ተገቢውን ሥልጠና ወስደው በመተግበሪያው አማካይነት አገልግሎቱን በመስጠት ላይ ሲሆኑ፣ በየቀኑ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች እንዲሁም ከዚህ ቀደም በጭነት ትራንስፖርት ሥራ ላይ ያልተሰማሩ የፒክ አፕ ተሽከርካሪ ባለቤቶች ጭምር እየተመዘገቡ እንደሚገኙ ገልጸዋል። 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች