Tuesday, January 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለታላቁ የህዳሴ ግድብ አለመግባባት ተጨባጭ የመፍትሔ ሐሳብ በሰባት ቀናት ለማቅረብ ድርድር ተጀመረ

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ አለመግባባት ተጨባጭ የመፍትሔ ሐሳብ በሰባት ቀናት ለማቅረብ ድርድር ተጀመረ

ቀን:

ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሰባት ቀናት ውስጥ መፍትሔ ላይ ለመድረስ የተግባቡበት ድርድር ተጀመረ። 

ድርድሩ ከእሑድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆንድርድሩን ለተከታታይ ሰባት ቀናት በማካሄድ ለውዝግቡ መፍትሔ ለማበጀት ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል። 

ድርድሩን ሦስቱም አገሮች በየዕለቱ እየተቀያየሩ የሚመሩት ሲሆን፣ የመጀመርያው ቀን ውይይት በሱዳን መንግሥት ሰብሳቢነት እንደተጀመረ ለማወቅ ተችሏል። 

በዚህ መሠረት ኢትዮጵያና ግብፅ እያንዳንዳቸው ሁለት ጊዜ ድርድሩን በሰብሳቢነት የመምራት ዕድል የሚያገኙ ሲሆንሱዳን ከሰባቱ ቀናት ውስጥ ሦስቱን በሰብሳቢነት የመምራት ዕድል ታገኛለች። 

ይህ የድርድር አማራጭ ተግባራዊ እንዲደረግ የተወሰነው በደቡብ አፍሪካ አደራዳሪነት የሦስቱ አገሮች ባለሥልጣናት ማክሰኞ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ከተወያዩ በኋላ መሆኑ ታውቋል። 

በዚህ ውይይት ላይ የሱዳን መንግሥት በቀጣዩ ድርድር ታዛቢዎችና የየአገሮቹ የቴክኒክ ባለሙያዎች ሰፊ ሚና ተስጥቷቸው ልዩነቶችን እንዲያጠቡ ሐሳብ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ተቀባይነት እንዳላገኘ ታውቋል። 

በመሆኑምሦስቱ አገሮች ሚኒስትሮችና የቴክኒክ ባለሙያዎች የሚሳተፉበት ድርድር እንዲካሄድ፣ ድርድሩንም ራሳቸው አገሮቹ እየተቀያየተሩ እንዲመሩት ተወስኗል። 

የታዛቢ አገሮች ተወካዮችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ዕገዛ አስፈላጊ ሲሆን፣ እንዲያግዙ እንደሚደረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።  በሰባት ቀናት ወይም እስከ መጪው ሳምንት እሑድ ድረስ በሚካሄደው ድርድር አገሮቹ ተጨባጭ መግባባት ላይ ደርሰው፣ ይህንንም ድርድሩን በበላይነት ለሚመራው ለአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሚያቀርቡ ይሆናል። 

ሦስቱ አገሮች በእነዚህ ቀናት በሚያደርጉት ድርድር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ መግባባት ያልቻሉባቸውን አጀንዳዎች ግልጽ አድርገው ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆንባልተግባቡባቸው ጉዳዮች ላይ ለመደራደር አጭር የጊዜ ሰሌዳና ግልጽ የሆነ የድርድር ሥነ ሥርዓት ቀምረው ለአፍሪካ ኅብረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል መባሉን የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 

የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለ (/) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከእሑድ ጀምሮ ለሰባት ቀናት የሚቆየው ድርድር በህዳሴ ግድቡ የመጀመርያ ምዕራፍ የውኃ ሙሌትናዓመታዊ የግድቡ ኦፕሬሽን ላይ እንደሚሆን ገልጸዋል። 

በዚህ አጀንዳ ላይ አገሮቹ በመጨረሻ የሚደርሱበት ስምምነት አስገዳጅ መሆን አለበትና የለበትም የሚለው ጉዳይ አንዱ ሲሆንሌላው የግድቡ ሙሌትና ዓመታዊ ኦፕሬሽን ቀመር ኢትዮጵያ በዓባይ ውኃ ላይ ወደፊት ከምታከናውናቸው የልማት ተግባራት ጋር መያያዝ የለበትም ወይስ አለበት የሚለው ነጥብ ነው። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...