Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ኤጂንሲ ከፌዴራል ተቋማት ጋር መከረ

ዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ኤጂንሲ ከፌዴራል ተቋማት ጋር መከረ

ቀን:

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ዓለም አቀፍ የፀረ አበረታች ቅመሞች ስምምነትን ለማስተግበር ከተቋቋመ የፌዴራል ኮሚቴ የጋራ ውይይት አካሄደ፡፡

አስተባባሪ ኮሚቴ የጤናውን፣ የትምህርትን፣ የፍትሕንና የስፖርቱን ዘርፍ የሚመለከቱ የፌዴራል ተቋማትን ያካተተ ሲሆን በስፖርት ኮሚሽን ሰብሳቢነት ይመራል፡፡

ስብሰባውን ያከናወነው ኮሚቴው በስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖርና በተቀናጀ መልኩ እንዲሠራ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዶፒንግን ለመከላከልና የዩኔስኮን የፀረ አበረታች ቅመሞች ስምምነትን (UNESCO Ant-Doping Convention) 1999 .ም. ተቀብላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 554/1999 አፅድቃለች፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ በስምምነት ሰነዱ ውስጥ በእያንዳንዱ አንቀጽ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮችን በአግባቡ መተግበር እንደሚያስፈልግ የብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመገምገም አተገባበሩን የበለጠ ለማጠንከርና ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲቻል ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ አባላትን የያዘ ብሔራዊ ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ሥራ መገባቱን  ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል፡፡

በተለይ በአጭር ጊዜ ሊከናወኑ ከሚገባቸው ተግባራት መካከል ራሱን የቻለ የድጋፍ ስጪ ምግቦችን (Nutritional Supplements) የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማስቻል፣ የሙያ ማኅበራት የሥነ ምግባር መመርያ ማውጣት፣ጥናትና ምርምር አስፈላጊው በጀት እንዲመደብ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባሮች መሆናቸው ተጠቅሰዋል።

የስፖርት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጂሎ በበኩላቸው፣ ዶፒንግ ዓለም አቀፍ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመው በኢትዮጵያም የሚጠበቀውን ተግባር ለማከናወንሚቴው የማይተካ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ አስተያየት ከሆነ ተቋማት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ያላቸውን እምነት በመግለጽ ተቀናጅተው በጋራ በመሥራት በዶፒንግ ላይሚነሱ ክፍተቶችን ለማስተካከል ትልቅ አቅም ይፈጥርላታል ሲሉም አክለዋል።

ዶፒንግ የአትሌቲክሱ ትልቅ ፈተና እየሆነ ከተመጣ ሰነባብቷል፡፡ በተለይ ንጥረ ነገሮች ቴክኖሎጂው ባደገው መጠን እያደጉ መሄዳቸው ለዓለም አቀፉ የፀረ ዶፒንግ ኤጀንሲ (ዋዳ) ራስ ምታት ሆኖበታል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2018 ዋዳ ኬንያና ኢትዮጵያን አሥጊ ደረጃ ላይ የሚገኙ አገሮች ናቸው ማለቱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...