Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናህወሓት "ቀዩን መስመር በማለፉ" መንግስት የኃይል እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታወቁ

ህወሓት “ቀዩን መስመር በማለፉ” መንግስት የኃይል እርምጃ መወሰድ መጀመሩን ጠቅላይ ሚንስትሩ አስታወቁ

ቀን:

ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት በመሰንዘሩ ሀገር እና ህዝብ ለማዳን ሲባል መከላከያ ሠራዊቱ የኃይል እርምጃ እንዲወስድ መታዘዙን ገለጹ። 

ጠቅላይ ሚንስትሩ ከእኩለ ሌሊት በኋላ እንዳስታወቁት ህወሓት ትግራይ በሚገኘው የመከላከያ ካምፕ ላይ ጥቃት ማድረሱን እና የሰሜን እዝን ለመዝረፍ መሞከሩን አስታውቀዋል። 

ህወሓት በአማራ ክልል በዳንሻ በኩልም ጥቃት መክፈቱን የተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህ ሙከራ በአማራ ክልል በነበረው ኃይል እንደተመከተ ገልጸዋል። 

“ቀዩ መሥመር የመጨረሻው ነጥብ ታልፏል ፤ ሀገር እና ህዝብ ለማዳን ሲባል ኃይል የመጨረሻው አማራጭ ሆኗል” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ነገሮችን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል እና በየአካባቢው ሊከሰቱ የሚችሉ ትንኮሳዎችን በንቃት በመቃኘት ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅረበዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...