Thursday, September 21, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለሥራ ፈጣሪ ሴቶች ድጋፍ መስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

ለሥራ ፈጣሪ ሴቶች ድጋፍ መስጠት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

ቀን:

ዋና መሥሪያ ቤቱ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የሆነውና ‹ኢቮልቪንግ ውሜን› የተሰኘው ሥራ ፈጣሪ፣ ሴቶችን በማሠልጠንና በመደገፍ ላይ የተሰማራ ተቋም፣ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በሥልጠናና በሌሎችም የቴክኒክ ድጋፎች ላይ አብሮ ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

‹‹ሴንተር ፎር አክሰለሬትድ ውሜን ኢኮኖሚክ ኢምፓወርመንት›› የተሰኘውና በሴቶች ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለውጥ ላይ የሚሠራው አገር በቀል ተቋም ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ‹‹ኢቮልቪንግ ውሜን›› ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪ ለሆኑ ሴቶች በጋራ ድጋፍ መስጠት በሚችሉበት አግባብ ላይ አብሮ ለመሥራት ስምምነት መፈረማቸውን አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ኤምባሲ በአዲስ አበባ ጽሕፈት ቤቱን በመክፈት እየተንቀሳቀሰ ከሚገኘው የዱባዩ ንግድ ምክር ቤት ጋር በታደሙበት በዚህ ሥነ ሥርዓት፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል የተደረገውን ስምምነት ከኢትዮጵያው ተቋም መሥራችና ዋና ዳይሬክተሯ ወ/ሮ ንግሥት ኃይሌ ፈርመዋል፡፡ ኢቮልቪንግ ውሜንን የወከሉትም የተቋሙ መሥራች አሲያ ሪክሲዮ ናቸው፡፡

 የኢቮልቪንግ መሥራቿ ሪክሲዮ እንዳሉት፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል በደረሰው ስምምነት መሠረት ኢትዮጵያውያን ነጋዴ ሴቶች በንግድ አሠራርና ክህሎት ላይ ያተኮረና እንደሚወክሉት የንግድ ሥራ ዘርፍ ሥልጠና የሚያገኙበት ዕድል ይመቻቻል፡፡ ሥልጠናውም በኢትዮጵያና በዱባይ ሊሰጥ እንደሚችል ተመላክቷል፡፡ ወ/ሮ ንግሥትም ኢቮልቪንግ ውሜንና የዱባይ ንግድ ምክር ቤት በጋራ ለኢትዮጵያ ሴቶች ደረጃውን የጠበቀ የሥልጠና ዕድል ለመስጠት ስምምነት በመፈጸም፣ ተቋማቸው በአጋርነት እንዲሠራ መመረጡ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ለሥልጠናው ብቁ የሆኑ ሥራ ፈጣሪዎችን ተቋማቸው እየመለመለ በማቅረብ ለጋና፣ ለደቡብ አፍሪካ፣ ለዛምቢያና ለሩዋንዳ ነጋዴ ሴቶች የተሰጠው ዕድል ለኢትዮጵያውያንም እንደሚሰጣቸው ተስፋ ተደርጓል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ መንግሥትና የዱባይ ንግድ ምክር ቤት ላለፉት ሁለት ዓመታት እንዲህ ያሉ ለሴት ነጋዴዎች የሚደረጉ ድጋፎችን ሲያግዙ እንደነበር፣ በኢትዮጵያ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውሷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ድጋፍ ሚዛኑን የጠበቀ የፆታ እኩልነት የሰፈነባትና በመጪው ዓመት ከ25 የዓለም ትልልቅ አገሮች ተርታ እንድትሠለፍ፣ የኤምሬትስ መንግሥት ያስቀመጠውን ትልም ለማሳካት ከያዘው ግብ ጋር የሚጎዳኝ እንደሆነ ኤምባሲው አስታውቋል፡፡ ለዚህ ግብ መሳካት እንዲረዳው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ፆታዊ ሚዛናዊነትን የሚያስጠብቅ ምክር ቤት እንደመሠረተም ይፋ አድርጓል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...