የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ በትግራይ ለክልላዊ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለስድስት ወራት በትግራይ ክልል ላይ ታውጆ እንደሚቆይ የገለጸ ሲሆን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም የሚቋቋመው ግብረ ኃይል በሚያወጣው መመርያ አዋጁ የሚፈጸምበት አካባቢ ሊሰፋ ይችላል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም ግብረ ኃይል የተቋቋመ ሲሆን፣ ግብረ ኃይሉን የሚመሩት የአገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም እንደሚሆኑና የሌሎች አስፈላጊ ተቋማት አመራሮችም በአባልነት ይሳተፉበታል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ግብረ ኃይል ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚሆን፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማውጣት ምክንያት የሆነው የትግራይ ክልል ሕገወጥነትና ጠብ አጫሪነት እንቅስቃሴዎች፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ በመሆኑ ነው ሲል የጠቅላ የሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡