Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያ 100 ሺሕ ገደማ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ናት

ኢትዮጵያ 100 ሺሕ ገደማ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች በማስመዝገብ ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ናት

ቀን:

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለምም ሆነ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋና ጉዳት እያስከተለ መሆኑን በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ወርልድ ሜትር በድረ ገጹ ከዳሰሳቸው አካባቢዎች አንዱ በኢትዮጵያና በጎረቤት አገሮች ያለውን የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያመለክት ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ኢትዮጵያን ጨምሮ ካሉት ሰባት አገሮች በወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነችው ኢትዮጵያ ናት፡፡

ድረ ገጹ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. እኩለ ቀን ላይ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ በበሽታው የተያዙ 98,391 ሲሆኑ ሕይወታቸው ያለፈ ደግሞ 1,508 ነው፡፡ በሁለተኛነት የምትገኘው ኬንያ በበሽታው የተያዙ 59,595 ሰዎች ሲሆኑ ሕይወታቸው ያለፈው 1,072 ነው፡፡ ሱዳን 13,943 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ሕይወታቸውን ያጡት ደግሞ 837 ናቸው፡፡ ምንም ሞት ያልተመዘገበባትና 484 ሰዎች ብቻ በበሽታው የተያዙባት ኤርትራ ናት፡፡

በኢትዮጵያ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዘው ሰው ቁጥር እየጨመረ መሄዱን ተከትሎ መንግሥት ሕዝብ በሚበዛበትና ከቤት ውጭ በሆኑ ሥፍራዎች ሁሉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ግዴታ የሚያደርግ መመርያ አውጥቶ እየተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

የቫይረሱን መስፋፋት ለመቆጣጠር እንዲያስችል በሚል ካለፈው ግንቦት ጀምሮ ማንኛውም ሰው ከመኖሪያው ቤት በሚወጣበት ጊዜ ማስክ ማድረግ እንደሚገባው፣ ካላደረገ ግን በሕግ ሊቀጣ እንደሚችል ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመታደግ ሳይንሳዊ መረጃን በዜና መጽሔቱ አማካይነት ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ፣ በቅርቡ ባወጣው ዕትሙ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጠቀሜታን፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የት የት መደረግ እንዳለበትየአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ያለባቸውና የሌለባቸው እነማን እንደሆኑ እንደሚከተለው በዝርዝር አስቀምጦታል፡፡

ለመሆኑ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ለምን ይጠቅማል?

ሰዎች በሚያስሉበት፣ በሚያስነጥሱበትና በሚያወሩበት ጊዜ ከአፍ የሚወጡ ፍንጣቂዎች በአየር ላይ ተለቀው በቅርበት ባለው ሰው አፍና አፍንጫ ያርፉና በመተንፈስ ሒደት ወደ ሳምባ ይገባሉ፡፡ ስለሆነም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ፡

 • በዋነኝነት ከአፍ የሚወጡ ብናኞችን ወደ ሌላ ሰው እንዳያልፉ ስለሚገድባቸው፣ የኮሮና ቫይረስ ከትንፋሽ ጋር በሚወጡ ብናኞች ምክንያት የሚተላለፍበትን መንገድ ለመቀነስ ይጠቅማል፤
 •  በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌላ ሰው እንዳያስተላልፍ ይከላከላል፤
 • ቫይረሱ፣ ከአፍ በሚወጡ ብናኞች አማካይነት በቫይረሱ መያዛቸውን ካላወቁና ምልክቶችን ካላሳዩ ሰዎች ወደ ሌላው ሰው እንዳይዛመት ይከላከላል፤
 • በተለይ ደግሞ ሰዎች በሚበዙበትና ማኅበራዊ/አካላዊ ርቀትን መጠበቅ በማይቻልበት ሁኔታ (በመገበያያ ሥፍራዎች፣ በሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች፣ ርቀትን ጠብቆ ለመሥራት የማያስችሉ የሥራ ቦታዎች) እጅግ ወሳኝ የሆነ የመከላከያ መንገድ ነው፡፡
 •  ስለሆነም ጭምብል ማድረግ ቫይረሱ ከሌላ ሰው እንዳይተላለፍብን ራሳችንን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ለመጠበቅ ጭምር የምናከናውነው፣ ለሌሎች አሳቢ መሆናችን የሚገለጽበት የትብብር ድርጊት ነው፡፡

ነገር ግን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው እንዳይተላለፍ የሚረዱ ሌሎች ጥንቃቄዎችን በሙሉ ሊተካ አይችልም፡፡ የቫይረሱን መስፋፋት የሚቀንሰው ማኅበራዊ ርቀትን ከመጠበቅና ከሌሎች የተለያዩ የመከላከያ ተግባራት ጎን ለጎን ዘወትር ሲተገበር መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ የት የት መደረግ አለበት?

የኮሮና ቫይረስ ካለበት ሰው ከአፍ የሚወጡት ጠብታዎች በቅርበት (ሁለት ሜትር ባነሰ ርቀት) ወዳለ ሰው ይገባሉ፡፡ ስለሆነም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ የሚገባን ሥፍራዎች የሚከተሉት ናቸው (የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል ሐምሌ 30 ቀን 2012)

 • ሕዝብ በሚበዛባቸው ሥፍራዎች ላይ ሲገኙ (የመገበያያ ሥፍራዎች፣ የሕዝብ ማመላለሻ መኪናዎች፣ ወዘተ…)
 • አብረዋቸው ከሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ውጪ ከሆኑ ሰዎች ጋር ሲገናኙ፤
 • ማኅበራዊ ርቀትን ለመጠበቅ አስቸጋሪ በሚሆንበት ሁኔታ ላይ ሲሆኑ፤

የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ ኮቪድ-19 ያለባቸው ሰዎች የሕመሙ ምልክቶች የማይታዩባቸው በመሆናቸው ቫይረሱን በቀላሉ ወደ ሌላ ሰው ሊያስተላልፉ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ከቤት ውጭና ሕዝብ በሚበዛቸው ሥፍራዎች በምንሆንበት ጊዜ ሁሉ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የሥራቸው ሁኔታ (መመገቢያ ሥፍራዎች፣ ሱቆች፣ ወዘተ…) አብዛኛውን ጊዜ ከሰዎች ጋር የሚያገናኛቸው ሰዎችና በቫይረሱ ከተያዙ ለከፍተኛ ሕመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች መሸፈኛውን ማድረግ አለባቸው፡፡

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ ያለባቸው እነማን ናቸው?

 • ዕድሜያቸው 12 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ዕድሜያቸው 6-12 የሆኑ ልጆች የጭምብል አጠቃቀም በአካባቢያቸው ባለው የኮቪድ-19 የመተላለፊያ መጠን፣ በልጆቹ ጭምብልን በትክክል የማድረግ ብቃትና ጭምብል ማድረግ በመማር፣ በሥነ ልቦናና በማኅበራዊ ዕድገት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ ይወሰናል (የዓለም ጤና ድርጅት ነሐሴ 15 ቀን 2012)
 •  በኮቪድ-19 የተያዘ ወይም ሊኖርብኝ ይችላል ብሎ የሚያስብ ሰው በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጪ ካሉ ሰዎች አጠገብ በሚሆንበት ጊዜ፤
 • በቤት ወይም በጤና ተቋም ውስጥ የኮቪድ-19 ሕመምተኞችን የሚከታተሉ ሰዎች፡፡ የበሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል እንደገለጸው በቤት ውስጥ ወይም ከጤና ተቋም ውጭ በሆነ ሥፍራ የኮቪድ ሕመምተኞችን የሚንከባከቡ ሰዎች ከጨርቅ የተሠራ ጭምብል ማድረግ ቢችሉም ጭምብሉ ቫይረሱ ከተያዘው ሰው ወደ ጤነኛው ሰው መተንፈሻ ክፍል እንዳይገባ የመከላከል ብቃቱ በደንብ የተረጋገጠ ስላልሆነ ሌሎችን የመከላከያ መንገዶችም የግድ መጠቀም ይኖርባቸዋል::

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን ማድረግ የሌለባቸውስ እነማን ናቸው?

 • ዕድሜያቸው አምስት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት የመተንፈስ ችግር ያለባቸው፤
 • መስማት የተሳናቸው፤ · በጤና ችግር ምክንያት ራሳቸውን የማያውቁ፤
 • መንቀሳቀስ የማይችሉና መሸፈኛን ያለዕርዳታ ማውለቅ የማይችሉ፤  የአዕምሮ ዕድገት ውስንነትና የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው፤
 • ከባድ እንቅስቃሴየሚጠይቅ ሥራ የሚሠሩ (ለምሳሌ፡የሚሮጡ)
 • መሸፈኛውን ማድረግ አደጋ ሊፈጥር በሚችልባቸው የሥራ ሁኔታዎች ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች (ከሚፈጥረው ሙቀት ጋር የተያያዘ ሕመም የሚያስከትል ወይም የደኅንነት ችግር የሚፈጥር ከሆነ)፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...