Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ይድረስ ለሪፖርተር‹‹ብልሹ አሠራርን ከማጥፋት አንፃር ድርጅቱ ዕርምጃ ወስዷል››

  ‹‹ብልሹ አሠራርን ከማጥፋት አንፃር ድርጅቱ ዕርምጃ ወስዷል››

  ቀን:

  ጋዜጣችሁ በቅጽ 26 ቁጥር 2140/ እሑድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሳተመው ዕትም ስለ ጽሕፈት ቤታችን አጭር ዘገባ ማቅረባቸሁ ይታወቃል፡፡ ይሁንና ዘገባችሁ ሙሉ መረጃ የማይሰጥና ከትክክለኛው መስመር የወጣ ነው ብለን እናምናለን፡፡ እናንተ ጋ አቤቱታ በማቅረብ ለማስፈራራት የሞከሩት እነማን እንደሆኑ ባናውቅም ትናንት የፓርቲ አባል በመሆን በሹመት ጽሕፈት ቤቱንና ፓርቲውን ሲያገለግሉ የነበሩና ድርጅቱ ባካሄደው አዲስ ምደባና ሽግሽግ ከሥልጣናቸው በመነሳታቸው በማኩረፍ ወደ እናንተ በመምጣት ስማቸው እንዲደበቅ የፈለጉ መሆናቸውን ከዘገባችሁ መረዳት ችለናል፡፡

  ምንም እንኳ ትክክለኛ መንገድ ባይሆንም የመሥሪያ ቤታችን ስም በዘገባችሁ በመጠቀሱ ሐሳባችን በማስተካከያነት ተወስዶ በሚቀጥለው ዕትም በዚሁ ገጽ እንዲወጣ በማሳሰብ ይህን ጽሑፍ ወደ እናንተ ልከናል፡፡

  በመጀመርያ ደረጃ በሕዝብ ምርጫ መንግሥት የመመሥረት ሥልጣን ያለው ፓርቲ አስፈጻሚውን አካል በሚያደራጅበት ወቅት ከአባላት መካከል በአመራርነት ይሾማል ይሽራል፡፡ ፓርቲያችንም ቢሆን አባላት አምነው በሚተዳደሩበት ደንብ  መሠረት ለሚመራው ሕዝብ ፍትሐዊ አሳታፊና ግልፀኝነት የሰፈነበት አገልግሎት ለመስጠት በሚያስተዳድራቸው ተቋማት ላይ ኃላፊዎችን የመመደብና የማሰማራት ተግባር ያከናወናል፡፡

  ከዚሁ በመነሳት በተለያዩ የሥልጣን እርከኖች ላይ በመሾም በአመራርነት ሲያገለግሉ የነበሩ የከተማችን አስተዳደር ባለሥልጣናት ዕቅድ አውጥተው ሥራ ሲሠሩ ነበርና የሥራ አፈጻጸማችንን ለውጡን ከማስቀጠልና ከሌብነት ከአድሎና ብልሹ አሠራርን ከማጥፋት አንፃርና ጥልቅ የሥራ ግምገማ በየደረጃው ተደርጓል፡፡ በተደረገው ግምገማም ለሥራችን እንቅፋት የሆኑና ውጤታማነታችንን የሚገዳደሩ የአመለካከትና የድርጊት ዝንፈቶች በአመራራችን ውስጥ የሚታይ መሆኑ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶበታል፡፡ የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው ነጥቦችም-

  1. በአመለካከት ጥራት ችግር ያለባቸውና ሁለት ቦታ በመርገጥ ለጎራ መደበላለቅ የተጋለጡ መኖራቸው
  2. ሙስና፣ ብልሹ አሠራር፣ ሌብነትና ሕገወጥ ድርጊት የሚፈትናቸው መኖራቸው፣
  3. ለከተማዋ የሚመጥን አገልግሎት መስጠት ያልቻሉና በሥራ ውጤታማ አለመሆን፣
  4. ለሥነ ምግባር ችግር የተጋለጡና በኃላፊነታቸው በተመደቡበት ቦታ በመገኘት ምሳሌ መሆን ያቃታቸው
  5. በዘመድ አዝማድና በማይገባ የጥቅም ግንኙነትና ከሚጠበቀው  ብስለት በታች ሆነው  ወደ አመራርነት የመጡ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

  እነዚህ የጠቃቀስናቸው ችግሮች ደግሞ ባካሄድነው ኮንፍረስ በነባሩ አመራር እንደ አካል የተገመገመና ድርጅቱ በአቋም መግለጫ ያረጋገጣቸው ነጥቦች ሆነው እንደ ግለሰብ በሚሄድበት ወቅት ደግሞ አመራሩና አባላት የወሰዷቸው ሂሶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ከዚህ ግምገማ በመነሳት ድርጅቱ ዕርምጃ ወስዷል፡፡

  ዕርምጃዎቹም ሽግሽግና አዲስ ምደባ ሲሆን፣ በአጠቃላይ ከከተማና ክፍለ ከተማ በጠቅላላው 65 ሚሆኑ አመራሮች በሽግሽግ ተመድቧል፡፡

  በመተካትም የትምህርት ዝግጅታቸው የላቀ፣ ሕዝብን ለማገልገል ዝግጁ የሆኑ እንዲሁም ከ12 ዓመታት በላይ በተለያዩ የሥራ እርከኖችና ዘርፎች ሲሠሩ የቆዩና ከተማዋን በደንብ የሚያውቁ አመራሮች ወደፊት ማምጣት ተችሏል፡፡

  ሌሎች ከአመራር የተነሱና የተሰጠኝ ቦታ አይመጥነኝም ያሉ አመራሮች ደግሞ አመራርነት እርስት አይደለምና በትምህርት ዝግጅታቸው በሥራ አፈጻጸምማቸውና ባላቸው ልምድ ወደ ሲቪል ሰርቫንትነት እንዲመደቡ ተደርጓል፡፡ ይህ ደግሞ የድርጅቱን በአባልነት ሲቀላቀሉ ከመተዳደሪያው እንደ ተረዱት ማንኛውም ከሹመት የሚነሳ አባል ሁሉ በሚመጥነው ቦታ መመደብ እንደሚገባው ስለተደነገገ ሲሠራበትም የቆየ ነው፡፡

  የሆነውም የተፈጸመውም ይኼ ሆኖ ሳለ አርስት እንደ ተቀማ ሰው እገሌ የሰጠኝን ሹመት እገሌ የቀማኝ ሹመት የሚባል ጉዳይ በድርጅታችንም ሆነ በመንግሥት የሌለ በመሆኑ መታወቅ ይገባዋል፡፡ ማንኛውም አባል መንግሥት የሰጠውን ግዴታ በሹመት ከተወጣ በኋላ ለተሻለ የሕዝብ አገልግሎት ተብሎ ከሹመት የሚያስነሳ ከሆነ የሚመጥነው ቦታ መመደብና መሥራት ብቻ ሳይሆን በሕዝብ አገልጋይነት ወደ ተመደበበት ቦታ በመሄድ የድርጅቱን ዓላማ ማሳካት ይጠበቅበታል፡፡ ካልሆነ ደግሞ እኔ አመራር እንጂ አገልጋይ አልሆንም የሚል ከሆነ መብቱ ነውና በራሱ ጊዜ የተሰጠውን ዕድል እያባከነው እንደሆነ ማወቅ ይገባዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...