Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ተነሱ የተባሉ አባወራዎች አቤቱታችን ሰሚ አጣ አሉ

ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ተነሱ የተባሉ አባወራዎች አቤቱታችን ሰሚ አጣ አሉ

ቀን:

ጽሕፈት ቤቱ ከተማ አስተዳደሩን ሰባት ሔክታር መሬት ጠይቆ እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል

ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ከይዞታቸው እንዲነሱ ማስታወቂያ የደረሳቸው 37 አባወራዎች ያቀረቡት ቅሬታ ሰሚ ማጣቱን ገለጹ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የላኩት ደብዳቤ ተመላሽ እንደተደረገባቸውም ተናግረዋል፡፡

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፣ ቦሌ ደንበል ተብሎ በሚጠራውና ግሪክ ትምህርት ቤት አካባቢ የሚኖሩ 37 አባወራዎች ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ ነዋሪዎቹ እንደሚሉት፣ ወረዳው ሲመሠረት ጀምሮ በቦታው ቤት ሠርተው መኖር ከጀመሩ ከ60 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ‹‹ቦታው ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሕፈት ቤት ማስፋፊያ ስለሚያስፈልግ ትነሳላችሁ›› በሚል፣ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ሕፈት ቤት በስልክ እንጨት ላይ ማስታወቂያ በመለጠፍ ‹‹ተነሺ መሆናችንን እየገለጸልን ይገኛል፤›› በማለት ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹ለፕሬዚዳንት ሕፈት ቤት ማስፋፊያ በሚል 37 በላይ የምንሆን ቦታውን ያለማንከ60 እና ከ70 ዓመት በላይ በቦታው የኖርነውን ሰዎች ቤታችሁን አፍርሳችሁ ተነሱ መባሉ አግባብነቱ ሊያሳምነን ስላልቻለ፣ ጉዳዩን በእርስዎ በኩል በሚገባ አይተውልን በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጠን እንዲያደርጉልን በማክበር እንጠይቃለን፤›› ብለዋል፡፡

ለምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ብሎም ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጽፎ በ37 ነዋሪዎች የተፈረመው ደብዳቤ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቅ ይዞታ በመርህ ደረጃ በመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ወይም በመሠረተ ልማት መሪ ፕላን መሠረት እንዲመራ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ይጠቅሳል፡፡

‹‹አዋጁ መልሶ ማልማት በፕላን ሊመራ የሚገባው ብቻ ሳይሆንየትኛውም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚለቀቅ ይዞታን በተመለከተ ተነሺው ቢያንስ ከአንድ ዓመት በፊት ይህንኑ እንዲያውቀውና ስለልማቱ አጠቃላይ ሒደት ገለጻ እንዲደረግለት ያስገድዳል፡፡ ጉዳዩ አጣዳፊ ነው ከተባለም ቅሬታ በማያስነሳና የእኛንም የተነሽዎችን ክብር በጠበቀ መልኩ ሊከናወን የሚገባ መሆኑ ተደንግጓል፤›› በማለት፣ እነዚህ ሕጋዊ ሒደቶች ሳይሟሉ ይልቁንም በመኖሪያ ቤቶቻቸው አካባቢ የኤሌክትሪክ ፖሎች ላይ በተለጠፈ ማስታወቂያ ተነሽ መሆናቸው እንደተነገራቸው በደብዳቤያቸውም፣ ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያም አስታውቀዋል፡፡

አቤቱታ አቅራቢዎቹ በከተማዋ በየትኛውም የፕላን ጥናት ላይ ያልተመለከተውን ‹‹የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ›› በሚል ‹‹የአካባቢውን ነዋሪ ማፈናቀል አግባብነት አለው ወይ? አስቀድሞ ተወስኖ የነበረው ሁለት ነጥብ ስድስትክታርስ በምን አግባብ ታይቶና ተጠንቶ ነው ተጨማሪ ይዞታዎች ተካተው በሰባት ሔክታር ላይ ያላችሁ በሙሉ ትነሳላችሁ የተባለው? ለፕሬዘዳንቱ ጽሕፈት ቤት እንዲሆን ለማስፋፊያነት የተጠየቀው ቦታስ ጠመዝማዛ እንዲሆን የተፈለገው አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ነው? ወይስ የተለየ ምክንያት አለው የሚል ጥያቄ የፈጠረብን ጉዳይ ነው›› ብለዋል፡፡

ይህንን ቅሬታ በሚመለከት ከከተማ አስተዳደሩ ምላሽ ለማግኘት ሪፖርተር ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡ ይሁን እንጂ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ሪፖርተር ጠይቋቸው እንዳብራሩት፣ እንደ ማንኛውም ለልማት ጥያቄ የሚያቀርብ አካል ጽሕፈት ቤቱም ጥያቄ አቅርቦ ምላሽ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል፡፡

ነዋሪው ማልማት ከቻለ ቅድሚያ ሊሰጠውና ስለሚነሳበት ጉዳይ ማወቅ አይጠበቅበትም ነበር ወይ? ለሚለው ጥያቄም፣ ምንም እንኳ ይህ የሚመለከተው የከተማ አስተዳደሩ ቢሆንም፣ የተጠየቀው መሬት ለንግድ ሥራ ወይም ለሪል ስቴት ሳይሆን፣ ለሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የሚገነባበት በመሆኑ ነዋሪው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባ ነበር የሚለውን ሐሳብ አስተባብለዋል፡፡

ለከተማ አስተዳደሩ የቀረበው የመሬት ሥፋት ሰባት ሔክታር ሲሆን፣ በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በኪራይ የሚሠሩ የኦሮሚያ ክልል ተቋማትን ወደ አንድ በማምጣት አገልግሎታቸውን ለማሻሻል ታስቦ እንደሆነ ከፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡ ለከተማው አስተዳደር የቀረበው የማስፋፊያ መሬት ጥያቄ ጊዜ እንደፈጀ አቶ ጌቱ ገልጸው፣ የተሰጠው ምላሽም ነዋሪዎች አምነውበትና ተዋያይተውበት በምክክር እንዲነሱ፣ ተገቢውን የካሳ ክፍያ እንዲያገኙ ከተማው እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ለፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤት ማሳወቁን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ከይዘታቸው ለመነሳት የተስማሙ ነዋሪዎች እየቀረቡ ካሳ እየተሰጣቸው እንደሚገኙ ያስታወቁት አቶ ጌቱ፣ የፕሬዚዳንቱ ጽሕፈት ቤትም ሰነዳቸው ተጠናቆ ለቀረቡለት ተነሽዎች ተገቢውን ካሳ መክፈል ግዴታው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በበኩላቸው የማልማት ዕድሉ ሳይሰጣቸው መቅረቱ ሳያንስ በተገቢው መንገድ እንዲያውቁትና እንዲቀበሉት ሳይደረግ ተነሱ መባላቸው የበታች ኃላፊዎች እንጂ፣ የመንግሥት ውሳኔ ነው ብለው ለመቀበል እንደሚቸግራቸው በመግለጽ፣ ለምክትል ከንቲባ ያስገቡትን ዓይነት ተመሳሳይ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ እንዲሁም ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ቢልኩም፣ ተመላሽ እንደተደረገባቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ የበላይ አካል ምላሽ ይሰጠናል ብለው ሲጠብቁ የተገላቢጦሹ አጋጥሞናል ያሉት ነዋሪዎቹ ቅሬታቸው ሰሚ ማጣቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...