የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፣ የ39 የሕወሓት አባል የሆኑ የትግራይ ክልል የሕዝብ ተወካዮችን ያለ መከሰስ መብት አነሳ።
ምክር ቤቱ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል(ዶ/ር)ን ጨምሮ፣ ሌሎች ከፍተኛ የትግራይ ክልል ተወካዮችን ያለ መከሰስ መብት አንስቷል።
ከእነዚህም መካከል አቶ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ፣ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ አዲስ ዓለም ባሌማ (አምባሳደር)፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ አቶ አፅበሃ አረጋዊ፣ አቶ ገብረ እግዚአብሔር አርዓያና ሌሎችም ይገኙበታል።
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎችም ጦር መሣሪያ ይዞ በማመፅ፣ የአገር መከላከያን በመውጋትና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት መሆኑ ተገልጿል።
ምክር ቤቱ አቶ ፍቅረ ገብረሒዎትን የምርጫ ቦርድ አባል ሹመትን አጽድቋል።
- Advertisement -
- Advertisement -