Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኤችአይቪ/ኤድስ ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከቀጠለ ሥርጭቱ ሊጨምር ይችላል ተባለ

በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ የሚታየው ቸልተኝነት ከቀጠለ ሥርጭቱ ሊጨምር ይችላል ተባለ

ቀን:

በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ የሚስተዋለው ቸልተኝነት በዚሁ ከቀጠለ የሥርጭት መጠኑ ሊጨምር እንደሚችል፣ የፌዴራል የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የሃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኃን፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ ከፍተኛ ሥራ ሠርተው፣ ንቅናቄ ካልተደረገ፣ የሥርጭት መጠኑ ከፍ ሊል እንደሚችል፣ የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በትረ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

ዳይሬክተሩ ከዛሬ 15 እና 20 ዓመታት በፊት በኤችአይቪ/ኤድስ ላይ ከፍተኛ ንቅናቄ መደረጉ ያመጣውን ለውጥ አስታውሰው፣ ከዚያ በኋላ ለብዙ ዓመታት ባለመሠራቱ አሁን ላለው ወጣት ትልቅ ሥጋት ፈጥሯል ብለዋል፡፡  

በየአምስት ዓመቱ ጥናት በሚያደርገው የኢትዮጵያ ዲሞግራፊክ ሔልዝ ሰርቬይ ሪፖርት መሠረት፣ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላከል ከመሠረታዊ ዕውቀት፣ ከግንዛቤና ከባህሪ ለውጥ አኳያ እዚህ ግባ የሚባል ሥራ በሁሉም አካላት እንዳልተከናወነ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ጥናቱ እንደ ማሳያ ያስቀመጠው የሴቶች ግንዛቤና መሠረታዊ ዕውቀት 19 በመቶ ብቻ ሲሆን፣ የወንዶች ደግሞ 39 በመቶ መሆኑን ያስረዱት አቶ ዳንኤል፣ ግንዛቤና ዕውቀት ያለውን ክፍተት በደንብ የሚያጎላ ጥናት መቅረቡን ጠቁመዋል፡፡

ጥናቱ እ.ኤ.አ. 2016 የተሠራ መሆኑን፣ ወጣቶች ስለኤችአይቪ/ኤድስ ያላቸው መሠረታዊ ዕውቀት፣ ግንዛቤና የባህሪ ለውጥ ላይ በጥልቀት ካልተሠራ ትውልድ አደጋ ላይ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

ከ15 እና 20 ዓመታት በፊት ሰፊ ንቅናቄ በተደረገበት ወቅት ሕፃን የነበሩ አሁን ደግሞ ወጣት መሆናቸውን ያስረዱት ዳይሬክተሩ፣ እነዚህ ወጣቶች ስለቫይረሱ መሠረታዊ ግንዛቤና ዕውቀት እንዲያገኙ ካልተደረገ እንደ አገር ትልቅ አደጋ መጋረጡን አብራርተዋል፡፡

ይህ ሥራ በዋነኝነት የአንድ ተቋም ብቻ ባለመሆኑ በሁሉም ተሳትፎ ችግሩ በጋራ ሊቀረፍ ይገባል ብለዋል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ 669,236 ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኝ መኖራቸውን፣ ከእነዚህ ውስጥ ከ500 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ፀረ ኤችአይቪ መድኃኒት የሚወስዱ መሆናቸውን፣ የሥርጭት መጠኑ እንደ አገር ሲታይ 0.91 እንደሆነ፣ በዓለም የጤና ድርጅት መሥፈርት መሠረት ከአንድ በታች ከሆነ ወረርሽኝ እንዳልሆነ ያመለክታል፡፡

ደቡብ ኦሮሚያ አማራና ሶማሌ፣ ክልሎች ከዜሮ በታች ሥርጭት ያላቸው መሆናቸውንና ወረርሽኝ የሌለባቸው ናቸው ሲባሉ፣ በኤችአይቪ/ኤድስ ወረርሽኝ ሥርጭት ጋምቤላ ክልል ቀዳሚ ሆኑ የሥርጭት መጠኑ 3.4 በመቶ ነው ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 3.4 በመቶ ሆኖ የሥርጭት መጠኑ ወረርሽኝ ውስጥ ሲሆን፣ በገጠርና በከተማ የቫይረሱ ሥርጭት ሲታይ ገጠር ላይ 0.4 እንደሆነ፣ ከተማ ወደ ሦስት ነጥብ እየተጠጋ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡ በማኅበረሰብ ደረጃ የቫይረሱ ሥርጭት ሲቃኝ በሴተኛ አዳሪነት በሚተዳደሩት የሥርጭት መጠኑ ከፍ ያለ መሆኑን፣ የርቀት አሽከርካሪ ሾፌሮች ከሁለትና ከዚያ በላይ በመቶ የሥርጭት መጠን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

በተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥርጭት መጠኑ የተለያየ መሆኑን ሴቶች ከወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ፣ 61 በመቶ ሴቶች፣ 39 በመቶ ወንዶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአገር አቀፍ ደረጃ 14 ሺሕ ሕፃናት ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ15 ሺሕ በላይ አዲስ ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኝ የሚመዘገብ ሲሆን፣ 11,545 ደግሞ በኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡ እንደ አገር በቀን 31 ሰዎች በኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ በሽታዎች ሕይወታቸውን የሚያጡ መሆናቸው፣ 41 ሰዎች ደግሞ በየቀኑ ኤችአይቪ/ኤድስ ቫይረስ እንደሚያዙ ተመልክቷል፡፡

የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪ ጽሕፈት ቤት ልዩ ልዩ አጋር ድርጅቶችንና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር የሚመራ መሆኑን አቶ ዳንኤል ገልጸዋል፡፡ የሚተባበረው ኃይል በተባለው ልክ ኃላፊነቱን ሲወጣ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል ጠቁመዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን፣ ከዛሬ 15 እና 20 ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲወዳደር በፊት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ይገልጻሉ፡፡ አክለውም በቫይረሱ ዙሪያ በከፍተኛ ሁኔታ ንቅናቄ ካልተደረገ የነገ አገር ተረካቢዎችን ሊያሳጣ ይችላል ብለዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...