Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውስን ተመልካቾች ይታደማሉ ተባለ

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ውስን ተመልካቾች ይታደማሉ ተባለ

ቀን:

የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአፍሪካ “ምርጥ” ፌዴሬሽን ተብሎ ለሽልማት ቀረበ

የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላይ ተመልካቾች እንዲታደሙ ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ታዳሚዎች ወደ ቶኪዮ ከመግባታቸው በፊት ክትባት ይወስዳሉ ብሏል፡፡ በሌላ በኩል የዓለም አትሌቲክስ (ወርልድ አትሌቲክስ) ከአትሌቶች በተጨማሪ፣ ከሁሉም አኅጉር አንድ አንድ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖችን መርጦ ለሽልማት አቅርቧል፡፡

በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ 2021 እንዲራዘም የተደረገው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ “ቶኪዮ 2020” የሚለውን ስያሜ እንደያዘ ከሐምሌ 16 እስከ ነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ በጃፓኗ ቶኪዮ ከተማ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ባደረጉት ጉብኝት በዝግጅቱ ውስን ታዳሚዎች እንደሚገኙ “እርግጠኛ ነኝ” ማለታቸው ታውቋል፡፡

አይኦሲ በየአራት ዓመቱ የሚያዘጋጀው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በስፖርቱ ዓለም ሁሉም አገሮች በአንድ መድረክ የሚወከሉበት ትልቁ ዝግጅት እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከ200 በላይ አገሮች የተውጣጡ 11,000 ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት፣ እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸው ልዑካን የሚታደሙበት እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡

የአስተናጋጇ አገር ጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሽንዞ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ይፋ በሆነ ማግሥት፣ ብዙ የተደከመበትና ዓለምን ለማቀራረብ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሕዝቦች ሰላምን የሚሰብከው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች እንዲራዘም በጠየቁበት ወቅት ሐዘናቸውን ብቻ ሳይሆን የገለጹት ተስፋቸውን ጭምር ነበር፡፡  ‹‹ይህ የጨለማ ጊዜ አልፎ ብርሃን ሲገለጥ የብርሃኑ ሻማ ለኳሽ ኦሊምፒክ ይሆናል፤›› በማለት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡

መንግሥታት የወረርሽኙን ሥጋት በሚፈለገው ልክ መቆጣጠር የቻሉበት ሁኔታ ባይኖርም በአሁኑ ወቅት ግን በበርካታ አገሮች ስፖርታዊ ውድድሮች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ምን እንደሚመስል ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚነገርላቸው የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ፣ ታዳሚዎች ወደ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ከማምራታቸው አስቀድሞ እንዲከተቡ ለማድረግ ከአዘጋጅ ኮሚቴው ጋር መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡ አስተናጋጇ ቶኪዮም ውድድሩ እንደሚካሄድ ማረጋገጫ መስጠቷ ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ችግሩን ታሳቢ በማድረግ ይመስላል ቶኪዮ 2020 የሚደረግ ከሆነ ውድድሮች በአነስተኛ ታዳሚዎች እንደሚካሄዱ፣ ተሳታፊ አገሮችም የሚመድቧቸው የቡድን አባላት መቀነስ እንደሚጠበቅባቸው ሲያስጠነቅቁ የነበሩት የቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ኃላፊ ቶሽሮ ሙቶ ሐሳባቸውን አንስተው፣ ትኩረታቸውን ስለውድድሩ ድምቀት ብቻ ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ከችግሩ ጋር ተያይዞ አንዳንድ አገሮች በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ላለመሳተፍ አቋም መያዛቸውን አስመልክቶ፣ ‹‹ውድድር ሠርዣያለሁ ያለ አንድም አገር የለም፣ አሁን ላይ ኮቪድ-19 ቢኖርም ባይኖርም ፕሮግራሙ ይካሄዳል፤›› በማለት ማረጋገጫ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

በሌላ በኩል የዓለም አትሌቲክስ በየዓመቱ በፈረንሣይ ሞናኮ የሚያዘጋጀው የዓመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት በተጨማሪ ዘንድሮ አትሌቶችን የሚያፈሩ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የሽልማቱ አንድ አካል ሆነው እንዲካተቱ ማድረጉ ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ 54 አባል ፌዴሬሽኖችን ከያዘው አፍሪካ፣ የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዚህ ሽልማት ዕጩ ሆኖ መመረጡ ታውቋል፡፡ ከኦሺያና ኒውዝላንድ፣ ከሰሜንና መካከለኛው አሜሪካ የኒካራጓ ከእስያ የፍልስጤም ከአውሮፓ የፖላንድና ከደቡብ አሜሪካ የፔሩ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ዕጩ ሆነዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...