Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ዕድሉን አሰፋ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ዕድሉን አሰፋ

ቀን:

ማዳጋስካርና አይቮሪኮስት ነጥብ ተጋርተዋል

ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያውን እያከናወነ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) የኒጀር አቻውን 3ለ0 ማሸነፉን ተከትሎ ዕድሉን አሰፋ፡፡ በምድቡ የሚገኙት ማዳጋስካርና አይቮሪኮስት በማዳጋስካር ሜዳ አንድ እኩል መለያየታቸው፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ በሜዳውና ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በጉጉት እንዲጠበቁ አድርጓል፡፡

በአሠልጣኝ ውበቱ አባተ የሚሠለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ባለፈው ዓርብ ኅዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ወደ ኒጀር ኒያሚ አምርቶ አንድ ለዜሮ በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፎ መመለሱ ይታወሳል፡፡ በቀናት ልዩነት የመልሱን ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም ያደረገው ብሔራዊ ቡድን ከጥሩ የጨዋታ ብልጫ ጋር ባደረገው እንቅስቃሴ ዕድሉን ተጠቅሞበታል፡፡

ቡድኑ የምድቡን አራተኛ ጨዋታ አድርጎ ከሜዳው ውጪ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በሽንፈት ሲያጠናቅቅ፣ በሜዳው ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ደግሞ በአሸናፊነት አጠናቋል፡፡ የቡድኑን ኃላፊነት በአወዛጋቢ ሹመት የተረከቡት አሠልጣኝ ውበቱ አባተና ረዳቶቻቸው ቀሪዎቹን ሁለት የማጣሪያ ጨዋታዎች ለማድረግ ከሁለት ወር ያላነሰ ጊዜ ስለሚኖራቸው እስካሁን ባደረጓቸው አራት ጨዋታዎች የሚያገኟቸውን ዕድሎች በመጠቀሙ ረገድ የተስተዋሉባቸውን ክፍተቶች ለማረም ሊጠቀሙባቸው ይገባል፡፡

በምድቡ የሚገኙት ማዳጋስካርና አይቮሪኮስት በዕለቱ ባደረጉት ጨዋታ አንድ እኩል በመለያየታቸው በእኩል ሰባት ነጥብ በጎል ልዩነት ተበላልጠው አንደኛና ሁለተኛ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ በስድስት ነጥብ ሦስተኛ ሆናለች፡፡ ከመሪዎቹ አንድ ነጥብ ዝቅ ብላ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ በቀጣይ ማዳጋስካርን በሜዳዋ፣ አይቮሪኮስትን ደግሞ ከሜዳዋ ውጭ ትገጥማች፡፡

በአይቮሪኮስት ሜዳ በጠባብ ውጤት 2 ለ 1 ተሸንፋ በሜዳዋ አንድ እኩል ተለያይታ ነጥብ የጣለችው ማዳጋስካር የምድቡን የመጨረሻው ጨዋታ በሜዳዋ ኒጀርን የምታስተናግድ እንደመሆኗ ከሜዳዋ ውጪ ለምታደርገው የኢትዮጵያ ጨዋታ ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥ ይጠበቃል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳውም ሆነ ከሜዳው ውጭ ለሚያደርገው ወሳኝ ጨዋታ ከወዲሁ ጠንካራ ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በዋሊያዎቹ በኩል የተሰለፉት ኃይለማርያም ሻንቆ፣ ሱሌማን ሀሚድ፣ አስቻለው ታመነ፣ ያሬድ ባየህ፣ ረመዳን የሱፍ፣ መሱድ መሐመድ፣ ሽመልስ በቀለ፣ አማኑኤል ዮሐንስ፣ አቡበከር ናስር፣ አማኑኤል ገብረሚካኤልና ጌታነህ ከበደ ሲሆኑ፣ ጎሎቹን ያስቆጠሩት አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ መሱድ መሐመድና ጌታነህ ከበደ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...