ሆራ ትሬዲንግ በአዳማ ከተማ በ1.5 ቢሊዮን ብር ያቋቋመውና ሥራውን የጀመረው የባጃጅ ተሸከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካን ሹማምንትና እንግዶች ባለፈው ማክሰኞ ኅዳር 8 ቀን 2013 ዓ.ም. ጎብኝተውታል፡፡ በዓመት እስከ 25 ሺሕ ባጃጆች እንደሚያመርት የተነገረለት ፋብሪካው፣ ‹‹ማክሲማ ዜድ›› የተባለውን አዲሱን የባጃጅ ምርት በቀን 70 ሲገጣጥም፣ አርኢ የተሰኘውን የባጃጅ ዓይነት በቀን 100 ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጥም ታውቋል፡፡