Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለሕፃናት ልጆች የተዘረጉ እጆች

ለሕፃናት ልጆች የተዘረጉ እጆች

ቀን:

በተለያየ ቦታ ላይ በየፊናቸው ቁጭ ብለው ሲቦርቁ ይታያል፡፡ የሚኖሩበት አካባቢ ሰፋ ያለ በመሆኑ እንደ ልብ እንዲጫወቱ አድርጓቸዋል፡፡ ከፊታቸው ገጽታ ላይም የደስታ ስሜት ይታያል፡፡ ከዚያም ከዚህም እየዘለሉ ግቢውን ሞልተውታል፡፡ እነዚህ ሕፃናት በቀጨኔ የሴት ሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡

በዓለም ለ31ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የተከበረውን ‹‹የዓለም ሕፃናት ቀን›› የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤና ሌሎች የመንግሥት ሹማምንቶች በተገኙበት ኅዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ‹‹ትውልድን እንቅረፅ፣ አገርን እንገንባ›› በሚል መሪ ቃል በማዕከሉ ተከብሮ ውሏል፡፡

የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሀብታም ነጋሽ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በማዕከሉ ውስጥ 183 ሕፃናት ልጆች አገልግሎት እያገኙ ነው፡፡ በማዕከሉ ከስምንት እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ ልጆች የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም  የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

ልጆቹ በሥነ ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ ለማድረግ ማዕከሉ ላይ በሚገኙ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች አስፈላጊውን ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ወደፊት ከማዕከሉ ሲወጡ ለሚገጥማቸው የአኗኗር ዘይቤ ከፍተኛ አስተዋትኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

በማዕከሉ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች በሚኖርበት ወቅት መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው፣ ከዚህ በፊትም ዕድሜያቸው ከስምንት እስከ 14 ዓመት  የሚገኙና ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ወደ ማዕከሉ እንዲቀላቀሉ መደረጉን ሥራ አስኪያጇ አስታውሰዋል፡፡

ልጆቹ ታንፀውና ብቁ ዜጋ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ መንግሥት የተለያዩ ባለሙያዎችን በመመደብና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እየሠራ እንደሚገኝና ከዚህ ጋር ተያይዞ በመንግሥት ሥር የሚገኙ ሌሎች ማዕከሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር የልምድ ልውወጦችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙም አክለዋል፡፡

የማዕከሉ ታዳጊዎች 18 ዓመት ሞልቷቸው ከማዕከሉ ሲለቁ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ የተለያዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል የሚሉት ወ/ሮ ሀብታም፣ ማዕከሉ ይህንንም ክትትል በማድረግ የሚሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በማዕከሉ ውስጥ ያሉት ሴት ሕፃናት ልጆች በመሆናቸው ችግር እንዳይገጥማቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታቸው እንዳይበላሽ ጥንቃቄ በተሞላ መልኩ አገልግሎትን እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተቋሙ ውስጥ የጤና፣ የትምህርት፣ የአልባሳትና የደኅንነት አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፣ በጤናቸው ላይ ችግር ሲያጋጥማቸው የመጀመርያ ዕርዳታ በማዕከሉ እንደሚደረግላቸው ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሐዳስ ኪዱ እንደተናገሩት፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ አራት የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋሞች ውስጥ ከ600 በላይ ሕፃናት እንክብካቤና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ በእነዚህም ተቋሞች ውስጥ የምግብ፣ የአልባሳትና የትምህርት ጥያቄ ሲነሳ የነበረ ሲሆን፣ ይህንንም ጥያቄ የከተማ አስተዳደሩ ግምት ውስጥ በማስገባት አፋጣኝ መልስ መስጠቱን ወ/ሮ ሐዳስ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም አስተዳደሩ ደስተኛ ሕፃናት በአዲስ አበባ ውስጥ የሚል ፕሮጀክት በመቅረፅና ለፕሮጀክቱ አገልግሎት የሚውል 140 ሚሊዮን ብር በመመደብ አዲስ አበባ ያሉ ሕፃናት እንክብካቤ የሚያገኙበትን ማመቻቸቱን ኃላፊዋ አስረድተዋል፡፡

 ፕሮጀክቱ አሥሩም ክፍላተ ከተሞች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን ይህም ብቁ ዜጋ ለማፍራት የሚጠቅም ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት፣ ጠንካራ ትውልድ ለመፍጠርና ለመቅረፅ የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰው የቤት ሥራ መሆን እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ሕፃናት ልጆችን በሚፈለገው ደረጃ በማነፅ፣ አስፈላጊውን በማቅረብና ከጎናቸው ሆኖ ክትትል በማድረግ ለአገራቸው ብዙ እንዲሠሩ እንዲሁም የበኩላቸውን እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡ ማዕከሉንም በማስፋትና ተጨማሪ ግብዓቶችን በማስገባት ሕፃናት ልጆች ትልቅ ቦታ እንዲደርሱ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...