Sunday, June 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በትግራይ ክልል የተከፈተ የባንክ ሒሳብ እንዳይንቀሳቀስ መታገዱ ጥያቄ አስነሳ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ጥቅሙ ለባለሒሳቡም ለባንኩም በመሆኑ ዕርምጃው ተገቢ ነው››

የባንክ ባለሙያዎች

በትግራይ ክልል የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት እንዳቆሙ በብሔራዊ ባንክ ከተላለፈው ውሳኔ በተጨማሪ ሰሞኑንም በዚያ ክልል የተከፈቱ አካውንቶች የገንዘብ እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቋረጥ መደረጉ ታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ባሉ ቅርንጫፎች ያሉ አካውንቶች እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉም በዚያ አካውንት ኖሯቸው ከክልሉ ውጭ ባሉ ቅርንጫፎች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ማድረጉ ከተለያዩ ወገኖች የተለያየ አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡

ትግራይ አካውንት ከፍተው አሁን ባለው ሁኔታ ወደ መሀል አገር የተመለሱ ገንዘባቸውን አለማንቀሳቀሳቸው ችግር እንደገጠማቸው ሲገልጹም እየተሰማ ነው፡፡ በውሳኔው ተጎጂዎች ሊኖሩ ቢችሉም በጥቅል ሲታይ ግን ውሳኔው ተገቢ ስለመሆኑ ያነጋገርናቸው የባንክ ባለሙያዎች ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል ሕግ የማስከበር ሥራው ከተጀመረ በኋላ ሲስተም በመቋረጡ፣ ባንኮች በክልሉ ካሉ ቅርንጫፎቻቸው መገናኘት አለመቻሉን የጠቀሱት ባለሙያዎች፣ በክልሉ የሚገኙ ቅርንጫፎች ያሉበት ሁኔታ ማወቅ ስላልተቻለ አገልግሎት እንዳይሰጡ መገደቡ ትክክል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ የተሰጠው ውሳኔ ሊተገበር የቻለው፣ ባንኮቹ አገልግሎት እንዳይሰጡ ከተደረገ በኋላ በመሀል ላይ አንዳንድ ቅርንጫፎች ምንም ሲስተም በሌለበትና ገንዘብ ለማንቀሳቀስ የማያስችል ኔትዎርክ እንደሌለ እየታወቀ፣ ገንዘብ እየወጣ ስለመሆኑ በመሰማቱና እየተዘረፈ ነው የሚል መረጃ በመኖሩ፣ ባንኮች በትግራይ ክልል ባሉ ቅርንጫፎች የተከፈቱ አካውንቶች በየትም ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ መደረጉን ባለሙያዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከትግራይ ባለው ሁኔታ ገንዘብ ማንቀሳቀስ ያልቻሉ የባንክ ደንበኞች፣ በእርግጥም ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል የሚገልጹት ያነጋገርናቸው የባንክ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ዕርምጃው የብዙኃኑን አስቀማጮች ገንዘብ ከመጠበቅና የባንኮችን ህልውና ከመጠበቅ አኳያ የተወሰደ ስለመሆኑ ግንዛቤ ውስጥ መግባት እንዳለበት ይናገራሉ፡፡

እንደ ባለሙያዎቹና ኃላፊዎቹ ገለጻ፣ ብሔራዊ ባንክ እንዲህ ያለውን ዕርምጃ ለመውሰድ የተገደደበት ሌላ ምክንያት ሊኖር የሚችልበት ነገር እንዳለ ባያውቁም፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን በትግራይ ክልል ያሉ ቅርንጫፎችን በሲስተም በማገናኘት መደበኛ ሥራ መሥራት በማይቻልበትና ስለቅርንጫፎቹ ምንም መረጃ በሌለበት ሁኔታ ገንዘብ እንደተፈለገ ማንቀሳቀስ መፍቀድ ተገቢ እንደማይሆን ያስረዳሉ፡፡

 በትግራይ ክልል ካለ አካውንቱ ገንዘብ ማውጣት አለማውጣቱ ያልታወቀና በስሙ ገንዘብ መኖር አለመኖሩ ማረጋገጫ በሌለበት አዲስ አበባ ላይ ወይም ሌሎች አካባቢዎች ክፍያ መፈጸም አስቸጋሪ በመሆኑ፣ እስኪጣራ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ መገደቡ ተገቢነት ያለው ነው ይላሉ፡፡

በተለይ አንዳንድ በትግራይ በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች አገልግሎት እንዳይሰጡ መመርያ ከተላለፈ በኋላ ገንዘብ ሕገወጥ በመሆነ መንገድ እንዲንቀሳቀስ ከተደረገ፣ ይህንን ያደረጉትን ሰዎች በሕግ ለመጠየቅ ጭምር እንዲህ ያለው ጉዳይ ተገቢ እንደሆነም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ ባንኮች በትግራይ ክልል ከሚገኙ ከየትኛውም ቅርንጫፍ ጋር አለመገናኘታቸው ብቻ፣ ቅርንጫፎቹ ‹‹ገንዘብ አውጡና ክፈሉ እየተባሉ ነው›› የሚለው መረጃ ወደዚህ ዕርምጃ እንዲገባ አድርጓል ብለው እንደሚያምኑም እኝሁ የባንክ ባለሙያዎች ማብራሪያ ያመለክታል፡፡

ያለው ሁኔታ ባንኮችንም አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የሕዝብ ገንዘብ ከመጠበቅ አኳያ ግድ የሚሉ ዕርምጃዎች ይኖራሉ ሲሉም ያክላሉ፡፡ ሆኖም ገንዘቡ ሳይንቀሳቀስ የሚቆይበት ጊዜን ማሳጠርና ሌላ መፍትሔ ካለም መፈለግ ተገቢ መሆኑን ሳያመለክቱ አላለፉም፡፡ የታገደው ገንዘባቸው አለመሆኑንና ክፍያው አሁን ባለው ሁኔታ ግልጽ የሆነ ነገር ስለሌለ፣ ችግሮችም እየተፈጠሩ ስለሆነና የአስቀማጮችን ገንዘብ ከመጠበቅ አንፃር ውሳኔው ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች