Thursday, June 13, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ አመሻሽ ላይ መኖሪያ ቤታቸው ሲደርሱ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እያዩ አገኟቸው]

 • ምን አዲስ ነገር ብትሰሚ ነው ያለ ወትሮሽ ቲቪው ላይ ያተኮርሽው? 
 • ሰሞኑንማ በአናት በአናቱ ነው የምታሰሙን። 
 • ምን?
 • አዲስ ነገር ነዋ፡፡
 • አይ አንቺ?
 • እውነቴን ነው፣ አንዱ ተቆጣጠርኩ ያለውን ሰምተን ሳንጨርስ ሌላኛው ይመጣና አንድ ክፍለ ጦር ደመሰስኩ ይላል፣ ግራ ገባን እኮ? 
 • ደመሰስኩ ብሎ ሳይጨርስ ምን እንደሚልስ አልሰማሽም? 
 • ምን አለ? 
 • ተቆጣጥረውት ሳይሆን ሥልታዊ ማፈግፈግ አድርገን ነው። 
 • ሆ. . .  ሆ. . . ሆ. . .  
 • በቁጥጥር ሥር ሲውሉ ምን እንደሚሉ አልናፈቀሽም? 
 • አልናፍቅም፣ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ብትነግረኝ ግን አልጠላውም። 
 • ካልናፈቀሽ ምን ይፈይድልሻል? 
 • እባክህ ንገረኝ?  ምን ሊሉ ይችላሉ?
 • ከውጭ ጠላት የራስ ጠላት ብዬ ነው፡፡
 • አልገባኝም?
 • እጄን ለውጭ ጠላት አልሰጥም ብዬ ነው፡፡
 • አልሰጥም ብዬ ምን?
 • የውስጥ ጠላት ለሆነው ለመንግሥት የሰጠሁት። 
 • አታመጡት የለ እናንተሆ. . .  ሆ. . . ሆ. . .! ቢሉስ ግን?
 • አይሉም ብለሽ ነው? 
 • ሰላማዊው ሕዝብ ግን ተንገላታ። 
 • እሱስ ልክ ነሽ። 
 • ታዲያ መንግሥት ምን እያሰበ ነው? 
 • ስለምኑ? 
 • ስለሰላማዊው ሕዝብ? 
 • እነሱ ነበሩ በቀዳሚነት ማሰብ ያለባቸው። 
 • ፌዴራል መንግሥቱ ማሰብ የለበትም? 
 • አለበት እንጂ ቀዳሚውን ማለቴ ነው። 
 • መንግሥት እንዲህ ብሎ ኃላፊነቱን መሸሹ ተገቢ አይሆንም፡፡
 • ምን ብሎ ሸሸ?
 • ቀዳሚ. . . ተከታይ. . .
 • መቼም አታሳልፊም አይደል? 
 • የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግሥት እንደሆነ ማንም አይጠፋውም። 

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አማካሪያቸው ያቀረበላቸውን ሪፖርት አድምጠው ተጨማሪ ውይይት እያደረጉ ነው]

 • ባለሥልጣኑ ለሚዲያ ተቋማት የሰጠው ማሳሰቢያ ትክክለኛና የዴሞክራሲ መርህን የተከተለ ነው። 
 • ክቡር ሚኒስትር ባነሱት ሐሳብ እስማማለሁ፣ ነገር ግን…
 • ነገር ግን ከተባለ በኋላ የሚመጣ ሐሳብ አይስማማኝም፣ ቢሆንም ልስማህ። 
 • ክቡር ሚኒስትር ምን መሰለዎት ጋዜጠኞችም እኮ ተቸግረዋል፡፡
 • እንዴትና በምን? 
 • ከጋዜጠኞቹ በተጨማሪ ባለሥልጣኑም አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል እኮ? 
 • እንዴት?
 • የሕግ ማስከበር ዘመቻ ቢሆንም መንግሥት የሚሰጠው መግለጫ ለጋዜጠኞቹም ለተቆጣጣሪ ባለሥልጣኑም አስቸጋሪ ይመስለኛል። 
 • የመንግሥት መግለጫ ችግሩ ምንድነው?
 • በአንድ በኩል የሕግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ነኝ ይልና ትንሽ ቆይቶ ደግሞ እንትንና እንትን ከተሞችን ተቆጣጠርኩ ይላል። 
 • ታዲያ ምን ችግር አለው? 
 • የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከሆነ ለምን ተቆጣጠርኩ ይባላል?
 • እውነቱ እንደዚያ ነዋ፡፡ እና ምን መባል አለበት ነው የምትለው? 
 • የዘመቻው ዓላማ ሕግ ማስከበር እስከሆነ ድረስ ይህንኑ የሚገልጽ መሆን አለበት። ለምሳሌ ሕገወጦችን በማፅዳት በከተማው ሙሉ በሙሉ ሕግ ማስከበር እንደተቻለ ቢገለጽ የተሻለ ይመስለኛል። 
 • ጥሩ ሐሳብ ቢመስልም ውኃ አይቋጥርም፡፡  
 • መንግሥት መከላከያ ሠራዊቱን አሰማርቶ ከተማ ተቆጣጠርኩ እያለ ጋዜጠኞች ጦርነት ብለው ለመዘገብ ይቸገራሉ። 
 • መንግሥት በሚያወጣው መግለጫ ያለውን እንጂ ማለት ያለባቸው ለምን ይቸገራሉ?
 • ከተማ መቆጣጠር የሚቻለው በጦርነት እንደሆነና ከጦርነት ዓላማዎች አንዱ መቆጣጠር እንደሆነ ይገነዘባሉ። በዚያ ላይ የሙያ ነፃነታቸው ይህንን ድምዳሜ የመስጠት መብት ይሰጣቸዋል እንጂ፣ መንግሥት ያለውን ብቻ እንዲደግሙ አያስገድዳቸውም። 
 • ጦርነት ከሚሉት ሌላ ስያሜ መፈለግ ተስኗቸዋል ለማለት ይቸግረኛል። 
 • ምን ዓይነት ስያሜ ሊሰጡ ይችላሉ ክቡር ሚኒስትር? 
 • ውጊያ! 
 • የምን ውጊያ?
 • የሕግ ማስከበር ውጊያ! 

[ክቡር ሚኒስትሩ ሥራ ለማዘዝ  ጸሐፊያቸው ቢሮ ሲገቡ በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን በተመስጦ እየተከታተለች አላስተዋለቻቸውም] 

 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር አላስተዋልኩዎትም ነበር። 
 • ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የያዘው ነገር? አዲስ መረጃ አለ እንዴ?
 • በባለሥልጣኑ ቃለ መጠይቅ ተገርሜ ነው ክቡር ሚኒስትር። 
 • ምን ቢሉ ነው እንዲህ ያስገረመሽ? 
 • በአንድ ወቅት ሌላ ነገር ነበር ሲሉ የነበረው። 
 • ምን ብለው ነበር?
 • ሰከን ይባል ብለው ነበር እኮ?
 • ማንን ነው ሰከን በሉ ያሉት፡፡
 • ሁላችንንም፡፡
 • አሁን ምን አሉ ታዲያ?
 • ሕግ ይከበር!
 • እንደዚህ ነው ለካ ኅብረተሰቡም የሚመረምረን፡፡
 • እውነት ነው እናንተ ብትረሱት እኛ አንረሳም።
 • ለነገሩ እሳቸው ገር መሆናቸው ይታወቃል፣ በዚያ ላይ ደግሞ…
 • በዚያ ላይ ደግሞ ምን?
 • ንፁኃን ይጎዳሉ የሚል ሥጋትና ፍርኃት ገብቷቸው ነበር፤ ነገሩ ያን ያህል አስቸጋሪ እንዳልሆነ ሲያስተውሉ ነው አሁን ሕግ ይከበር ያሉት፡፡
 • እንደዚያ ከሆነ ሌሎችም ሊመለሱ ይችላሉ ማለት ነው? 
 • ሌሎቹ እነማን ናቸው? 
 • የፈረጠጡት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...