Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ለዓለም ቁንጮነት ቅዳሜ ከሚፎካከሩት አምስቱ አንዷ ሆነች

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ለዓለም ቁንጮነት ቅዳሜ ከሚፎካከሩት አምስቱ አንዷ ሆነች

ቀን:

በዓለም አትሌቲክስ 2020 ምርጥ የሴት አትሌትነትን ክብር ለመቀዳጀት ከተመረጡት አምስት ምርጦች ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ አንዷ ሆናለች፡፡ አሸናፊዋ የምትታወቀው ቅዳሜ ኅዳር  26 ቀን 2013 ዓ.ም. ነው፡፡ የዓለም አትሌቲክስ እንዳስታወቀው፣ አምስቱ አትሌቶች 2020 በተለያዩ የአትሌቲክስ ዘርፎች ድንቅ አፈፃፀም በማምጣት የላቀ ውጤት አሳይተዋል፡፡ አምስቱ ዕጩዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ለተሰንበት ግደይ (ኢትዮጵያ) 5000 ሜትር የዓለምን ክብረ ወሰን በ14፡06.6.62 የሰበረች፣ ሲፋን ሀሰን (ኔዘርላንድስ) በአንድ ሰዓት ሩጫ ውስጥ 18,930 ሜትር በመሮጥ የዓለም ሪኮርድን ያስመዘገበች፣ ፔሬስ ጄፕቺር (ኬንያ) የዓለም ግማሽ ማራቶን አሸናፊና ባለሪከርድሆነች፣ ዩሊማር ሮጃስ (ቬኑዝዌላ) በአራት የሥሉስ ዝላይ ውድድሮች በቤት ውስጥ እና ከቤት ውጭ ያሸነፈችና ክብረ ወሰን የሰበረች፣ ኢሌን ቶምሰንሄራ (ጃማይካ) በሰባት የ100 ሜትር ውድድሮች ያልተሸነፈችና የዓለም ምርጥ ሰዓት የጨበጠች፡፡ አሸናፊዋ የሚለይበት የመጨረሻው ሥነሥርዓት በመጪው ቅዳሜ በዓለም አትሌቲክስ ዩቲዩብ ቻናል፣ በፌስቡክ ገጹ እና በትዊተር በኩል በቀጥታ ይተላለፋል፡፡

ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ለዓለም

ፎቶ የዓለም አትሌቲክስ

- Advertisement -

                                                         

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...