በአሜሪካ ሜሪላንድ የሥነ ጥበብ ኮሌጅ መምህርና ሠዓሊ አማረ ሰልፉ ‹‹የኛ ታሪክ›› (The Story of Us) በሚል ርዕሰ ያዘጋጀው የሥዕል ትርዒት ስድስት ኪሎ በሚገኘው የገብረ ክርስቶስ ደስታ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ሙዚየም በመታየት ላይ ይገኛል፡፡
መሠረቱን በአሜሪካ ያደረገው ሠዓሊው፣ በመስመሮች ላይ በመጠበብ በሚሥላቸው ሥዕሎቹ ይታወቃል፡፡ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ሥራዎቹን አስመልክቶ ካሠፈረው ምልከታው ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፡፡
‹‹መስመሮች የአንድን ሰው ማንነት ባለበት ሁኔታና ቦታ ለመወሰን የመጀመርያም የመጨረሻም ናቸው። የድንበሮች የሚታይም ሆነ ምናባዊ ባህሪ እንደዚሁም ከእዚህና ከዚኛው መካከል ባሉ ወይም ደግሞ ከሁለቱም ባልሆኑ የሐሳብ ቀጣናዎች ላይ ነው፣ እኛና እነሱነት እንደዚሁም የእኛነትና የእነሱነት የሚኖረው። የአካታችነት፣ የአግላይነት አልያም የሌላነት ስሜቶች የሚፈጠሩት።››
የሠዓሊው ትርዒት እስከ ታኅሣሥ 9 ለሕዝብ ክፍት ይሆናል::