Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጊኒዎርም በሽታ ሥጋት ፈጥሯል

የጊኒዎርም በሽታ ሥጋት ፈጥሯል

ቀን:

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዓምና ሚያዝያ አንስቶ እስካሁን ይህም ሁኔታ በሽታው ለማጥፋት የተደረገውን ጥረት ወደ ኋላ እንዳይመልሰው ሥጋት መፍጠሩን የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በጊኒዎርም የማጥፋት ፕሮግራም ላይ ትኩረት አድርጎ በተወያየው ዓውደ ጥናት መክፈቻ ሚኒስትሯ እንደገለጹት፣ በሽታውን ለማጥፋት በርካታ ሥራዎች ቢከናወኑም ከሚያዝያ ወር ወዲህ በሽታው በ11 ሰዎችና በ15 እንስሳት ላይ መገኘቱ፣ በሽታውን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ወደኋላ እንዳይመልሰው ሥጋት ፈጥሯል፡፡

አሁን የተከሰተውን ችግር በተገቢው መንገድ ለመቅረፍ ዘርፈ ብዙ የሆነ ቅንጅትና ርብርብ እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

የጊኒዎርም በሽታ የመከላከያ ክትባት የሌለው ከመሆኑም በላይ ንፁህ የመጠጥ ውኃ በሌለባቸው አካባቢዎች የሚፈጠር፣ በእንስሳትና በሰው ላይ መገኘቱ ደግሞ ችግሩ በፍጥነት እንዳይወገድ ማድረጉንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር)፣ የጊኒዎርም በሽታ ከሌሎች በሽታዎች የሚለየው ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት የሚፈጠሩ ክፍተቶችን ማወቅ የሚቻለው ከዓመት በኋላ በመሆኑ በሽታውን በቀላሉ ለማጥፋት አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ይህን ችግር ለመቅረፍ ማንኛውም የመንግሥት ኃላፊነት የተቀበለ አካል ሁሉ በሽታውን ለማጥፋት መሥራት እንዳለበት ከዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኢንስቲትዩቱ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር ማዕከል፣ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ኅዳር 16 እና 17 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ባካሄደው ዓውደ ጥናት፣ በሽታውን ለማጥፋት እስካሁን እየተካሄደባቸው ባሉ ሥራዎችና ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የመፍትሔ ሐሳቦችም ተቀምጠዋል፡፡

የጊኒ ዎርም በሽታ እንዴት ይከሰታል?

የጤና ሚኒስቴር ‹‹ትኩረት የሚሹ በሽታዎች መከላያና መቆጣጠሪያ ፓኬጅ›› በሚለው ሰነዱ ላይ እንደተገለጸው፣ የጊኒዎርም በሽታ (ድራኩንኩልያሲስ) ርዝማኔው ከ100 ሴንቲ ሜትር በላይ በሆነ ገመድ መሠል ትል የሚከሰትና አቅም የሚያሳጣ ነው፡፡ ሰዎች በበሽታው የሚያዙት የጊኒ ትል ዕጭን የተሸከሙ የውኃ ቁንጫዎች (Cyclopes) ከሚገኙበት ኩሬ ወይም ማንኛውም የረጋ ውኃ የሚጠጡ ነው፡፡ ትሉ የበሽተኛውን ቆዳ በመብሳት ሊወጣ ጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት ሲቀረው ትኩሳት፣ እብጠት እንዲሁም ትሉ ባለበት አካባቢ ሕመም ሊሰማም ይችላል፡፡

በንክኪ፣ አብሮ በመኖር፣ በመተኛትና በመሥራት የማይተላለፍ ቢሆንም፣ ነገር ግን አሣን ጨምሮ ልዩ ልዩ የውኃ አካላትን ወይም ውጤቶችን ሳያበስሉ ጥሬውን መብላት ለበሽታው ሊዳርግ ይችላል፡፡

በጊኒዎርም እጭ የተበከለውን ውኃ የጠጣ ሰው እጩ በሰውነቱ ውስጥ እንደሚገባ፣ ይህም ከሆነ ቢያንስ እስከ አሥር ወራት፣ ግፋ ቢል ደግሞ 14 ወራት ድረስ ሕመሙ እንደማይሰማውና ችግርም ሆነ ምልክት የማይታይበት ነው፡፡

ከእነዚህ ወራት በኋላ ከሚታዩት ምልክቶች መካከል ማሳከክ፣ በጣም የሚያቃጥል ውኃ የቋጠረ እባጭ መውጣት ይገኙበታል፡፡ ቆየት ሲል ደግሞ እባጩ ይፈነዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ጠቅላላ ርዝመቱ እስከ አንድ ሜትር የሚደርስ ነጭ ትል ይታያል፡፡ ትሉ ከወጣ በኋላ ለአንድ ሳምንት ግፋ ሲል ለወራት ያህል ልዩ ልዩ ተጓዳኝ  ችግሮችን ቢያስከትልም ለሞት አይዳርግም፡፡

ጊኒዎርም በአብዛኛው ጊዜ የሚያጠቃው ማኅበራዊ አገልግሎቶች ባልተዳረሱባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ማኅበረሰቦችን እንደሆነ ይወሳል፡፡

ጊኒዎርም መታከምና መዳን የሚችል ቢሆንም፣ ሕሙማን በግልጽ ወጥተው ወደ ሕክምና መሄድን ባለመምረጣቸው የማኅበረሰቡን በሽታን የመደበቅ ልማድ ለመስበር ጤና ሚኒስቴር ‹‹በበሽታው የተያዘ ሰውን ለጠቆመኝ እሸልማለሁ›› ብሎ ማስታወቂያ እስከማስነገር መድረሱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...