Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

እኔ የምለዉኢዓለም አቀፋዊ ግጭት በኢትዮጵያ

ኢዓለም አቀፋዊ ግጭት በኢትዮጵያ

ቀን:

በህሊና እስጢፋኖስ

ጠቅላይ ሚኒስትር ብይ አህመድ (ዶ/ር) ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.  ከእኩለ ለሊት በኋላ በቴሌዥን መስኮት ብቅ ብለው የመከላከያ ራዊቱ የሰሜን ዝ የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ በሚገኘው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትሕነግ) እንደተጠቃ አስታወቁ። ይህም ቀይ መስመር ማለፍ በመሆኑ የጦር ምላሽ እንደሚሰጠው በመግለ ወራትን የተሻገረው የሁለቱ ጎራዎች የቃላት ሽኩቻ ወደ ጦር ግጭት መግባቱን ይፋ አደረጉ። ከቀናት በላም ከትሕነግ በኩል ሴኮቱሬ ጌታቸቅድመ ላከል ነው በሚል የገለትን ይህንኑ ጥቃት በቡድናቸው መፈሙን መኑ።

ይህንን ተከትሎ 20 ቀናትን በተሻገረው ግጭት ላይ የተለያዩ ይታዎች በተለያዩ የመረጃ ማራጫዎች ላይ ሲቀርቡ ቆይተዋል። በግጭቱ ላይ የሚሳተፉ ወገኖችም የየራሳቸውን መገናኛ ብዙንን በመጠቀም`እውነታውን´ በራሳቸው መነር ለማሳየት ተደጋጋሚ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። የማበረሰቡ አመለካከት ወደ እነርሱ እንዲያጋድል በሚያደርጉት በዚህ ደትም በአግባቡም ይሁን ያግባብ በተደጋጋሚ ከሚወረወሩ ቃላት መካከል ጋዊና ወንጀል የሚሉት ይገኙበታል። ይህ አካሄድ እንደ ግለሰብ ስለግጭት ያለንን አረዳድ ሊያዛባ ስለሚችል የእነዚህ ቃላት አገባብ ምን ያል ተገቢ ነው የሚለውን መመዘን አስፈላጊ ነው።

- Advertisement -

ለዚህ ነው ከፖለቲካዊ በተጨማሪ ጋዊ አንምታ ባለው በዚህ የግጭት ሁኔታ ላይ ጉዳዩ በግ መነር እንዴት ይታያል የሚለውን በዚህች አጭር ጽሑፍ ለማንሳት የምሞክረው። በዚህም መሠረት ጦርነት በግ ይገዛል ወይ? ይህ ከሆነስ በምን የግ ማቀፍ ይሸፈናል? ጉ ግጭቱን እንዴት ይመለከተዋል? እንዲሁም ምን ምን ይነት ግዴታዎችን ይጥላል? የሚሉትን ጥያቄዎች በማስከተል እመልሳለሁ።

ይህች ለም በታሪ እጅግ በጣም ብዙ ጦርነቶችን አስተናግዳለች። እነዚህ ጦርነቶች እንዳይከሰቱ ለማድረግ ይቻል ዘንድ የሚከላከሉ የግ ማቀፎች የመኖራቸውን ያ ሲከሰቱ ደግሞ በተቀመጡ የግ ገደቦች መረት እንዲሆኑ የሚያስገድዱ ጎችም አሉ። እነዚህን ጎችን አቅፎ የሚይዘው የይነት የለም አቀፍ የጦርነት ጎች ሲባል በውስጡም በሮች የተፈረሙ ስምምነቶችና እንደ ለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ያገኙ ልምዶችን (International Customary Laws) ያቅፋል። ይህ የግ ማቀፍ ጦርነት ላይ እንደ ተዋጊ የማይሳተፉ ግለሰቦችንና ቁሶችን ከጦርነቱ ለመታደግ በዋናነት የጄኔቫ ስምምነቶችን ይጠቀማል፡፡ በጦርነት የሚሳተፉት ግለሰቦች በጎቹ ውስጥ የተፈቀዱ የጦርነት ዘዴዎችና መሪያዎችን ብቻ እንዲጠቀሙ ደግሞ የግ ስምምነቶች ላይ ይደነግጋል። የጄኔቫ ስምምነቶች ተጨማሪ ፕሮኮሎች በበኩላቸው በእነዚህ ሁለት ስምምነቶች ውስጥ የተካተቱትን ሁለት ላማዎች ለማሳካት ያለሙ አንቀችን አቅፈው ይዘዋል።

ከዚህም ባለፈ በጄኔቫና በሄግ ስምምነቶች መካከል ያሉትን ልዩነቶች ታሪካዊ አመጣጥን ከመረዳት ያለፈ ፋይዳ እንዳይኖራቸው አድርገዋል። በዚህም መረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትና በትግራይ ክልል ልዩ ይል መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በግ የሚገዛ ነው ማለት ነው።

ለም አቀፍ የጦርነት ጎች የበላይ ጠባቂና አስተዋዋቂ የሆነለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴበጄኔቫ ስምምነቶች መረት ግጭትን ለም አቀፋዊና ለም አቀፋዊ ሲል ለሁለት ይከፍለዋል። ለም አቀፋዊ ግጭት የሚባለው ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ሮች ከል በጦርነት አዋጅ አልያም በማንኛውም ሌላ ሁኔታ የሚፈጠር በጦር የታገዘ ግጭት ነው። ለም አቀፋዊ ግጭት ደግሞ ለም አቀፋዊ ያልሆነ በሚል ጠቅለል ያለአልያም የአንድ ገር የጦር ይሎች የራሳቸው አመራር ኖሯቸው፣ ቀጣይነት ያለውና የተቀናጀ ውግያ ለማካሄድ የሚያስችል ግዛት ከያዙና ጉን ሊያስፈሙ ከሚችሉ ተዋጊ ይሎች ወይም የተደራጁ ቡድኖች ጋር የሚያደርጉት የጦር ፍልሚያ ሲል ዘርዘር ያለ ትርሜ ይሰጠዋል።

 እነዚህ ሁለት ትርሜዎች ተደጋጋፊ ግን የተለያዩ ሲሆኑ የሚገኙትም በሁለት የተለያዩ የግ ሰነዶች ውስጥ ነው። እዚህ ላይ የግጭት ሁኔታ በግጭቱ ውስጥ ያሉ ቡድኖች ባሳዩት የመቀበልና አለመቀበል አዝማሚያ ሳይሆን መሬት ላይ ባለ እውነታ የሚመረት ውሳኔ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። በመሆኑም ውጊያ ላይ የሚሳተፉ አካላት ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም በጉ ላይ የተመለከቱ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟላ ግጭት ከሁለቱ ቢያንስ በአንዱ ውስጥ መውደቁ አይቀሬ ነው።

የኢትዮጵያ መንግት በተደጋጋሚ በሚሰጣቸው መግለጫዎች በመከላከያ ራዊቱ የሚወሰደው ርምጃ የግ ማስፈም እያለ ሲገል ይስተዋላል። ሆኖም ከላይ በተጠቀሰው የለም አቀፍ የጦርነት ግ አንፃር ሲታይ በአንድ ጎራ የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊት በሌላ ጎራ ደግሞ በትግራይ ልዩ ይል ከል የሚካሄድ የጦር ግጭት ነው። የትግራይ ልዩ ይል አደረጃጀትና የግጭቱ ሁኔታ ከባድነት የኢለም አቀፋዊ  ግጭት ሁለት ዋና ዋና መፈርቶች እንዲሟሉ ያደርጋ አደረጃጀቱን በተመለከተ የትግራይ ልዩ ይል ተቀማጭነቱን መቀሌ ላይ ባደረገው በትነግ ቡድን እየተመራ ቀጣይነት ያለውና የተቀናጀ ውግያ ለማካሄድ የሚያስችል ሰፊ መሬት በትግራይ ክልል ተቆጣጥሮ የሚገኝ የነበረ ሲሆን የጦርነት ግን ሊያስፈም የሚያስችል ሁኔታ ላይ ያለ ነው። የግጭቱ ሁኔታ ከባድነትን ለመረዳት ደግሞ በኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትም ሆነ በትግራይ ልዩ ይል በኩል የሚሳተፉት በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች፣ ከግጭቱ አስቀድሞ በነበሩ የተለያዩ የጦር ትርቶች ላይ በሁለቱም በኩል ለይታ የቀረቡ የጦር መሪያዎች እንዲሁም ግጭቱ ከተጀመረ ወዲህ አገልግሎት ላይ የዋሉት ለምሳሌ የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊት እየተጠቀመ ያለው የአየር ይልና ከትግራይ ልዩ ይል በመቶዎች የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተሻግሮ ባህር ዳርና ጎንደር ላይ በተደጋጋሚ የተተኮሱ ሮኬቶች፣ እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ራሳቸውን ከግጭቱ ለማትረፍ ድንበር ተሻግረው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጥቂቶቹ ማሳያዎች ናቸው።

ከእነዚህ ቡድኖች በተጨማሪ የአማራና ትግራይ ክልል ሚሊሻዎችእንዲሁም ከሰሜን ዝ በፍላጎትም ይሁን በጉልበት የተወሰዱ ይሎች በተለያዩ ወገን ያሉትን ቡድኖች እየረዱ እንዳሉ ተሰምቷል። ሆኖም የእነዚህን ቡድኖች ጥልቅ አደረጃጀትና በእነሱ በኩል የሚካሄደውን ግጭት ሁኔታ ከባድነት ለማስረዳት በቂ መረጃ ስለሌለ ለዚህ ጽሑፍ በግጭቱ ላይ ተሳታፊ ተብለው የሚገለት የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትና የትግራይ ልዩ ይል ብቻ ይሆናሉ። በዚህም መረት ግጭቱን የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትና የትግራይ ልዩ ይል መካከል የሚካሄድ ኢለም አቀፋዊ የግጭት ሁኔታ ስንል ልንጠራው ንችላለን። ይህ ትርጉም ጠባብ የሆነው የግ አተረጎም ላይ  በመመረት የተገኘ ይታ በመሆኑሰፋ ያለውን የኢለም አቀፋዊ ግጭት ትርጉም ብንጠቀምም ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ እንድንደርስ ያስችለናል።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ራዊትም ሆነ የትግራይ ልዩ ይል በዚህ ትርሜና ተያያዥ የግ ድንጋጌዎች የሚገዙበት የተለያዩ የግ አግባቦች አሉ። በአንድ በኩል ኢትዮጵያ የጄኔቫ ስምምነቶችና ተጨማሪ ፕሮኮሎቹን ከፈረሙ ሮች መካከል ስትሆንገሪቱ መንግት በአንቀ 9 (4) ገሪቱ የፈረመቻቸው ስምምነቶች የገሪቱ ግ አካል ንደሆኑ ይገልል። ስለሆነም የጄኔቫ ስምምነቶችና ተጨማሪ ፕሮኮሎቹ በኢትዮጵያ ተፈጻሚነት አላቸው ለማለት እንችላለን። በሌላ በኩል ደግሞ አብዛኞቹ በስምምነቶቹና ተጨማሪ ፕሮኮሎቹ ውስጥ የተካተቱ ድንጋጌዎችእንደ ሕግ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትን አግኝተዋል። ይህም በማንኛም ቡድንና ሁኔታ ተፈሚነት እንዲኖራቸው ያስችላል። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትም ሆነ የትግራይ ልዩ ይል አባላት ለኢለም አቀፋዊ ግጭት አስፈላጊ በሆኑት የጄኔቫ ስምምነቶች የጋራ አንቀ 3 የጄኔቫ ስምምነቶች ተጨማሪ ፕሮትኮል 2፣ እና እንደ ለም አቀፋዊ ተቀባይነትን ባገኙ ጎች የመገዛት ሲጥሱ ደግሞ በግ ማቀፉ በተቀመጠው መጠን ላፊነት የመውሰድ ግዴታ አለባቸው። ይህንን ለማድረግ እንዲያስችል ለም አቀፍ የጦርነት ጎች በዝርዝር የተቀመጡ ግጋቶች ቢኖሯቸውም የተመረቱባቸው ዋና ዋና መርሆች ግን የመለየት፣ የተመጣጣኝነት፣ የአስፈላጊነት (ከመጠን በላይ ጉዳትና አላስፈላጊ መከራ ያለ መፍጠር) እንዲሁም የሰብዊነት በመባል ይታወቃሉ።

የመጀመያ የሆነው የመለየት መርህ ማንኛውም በጦርነት የሚሳተፍ ወገን ለጥቃት ተጋላጭ ማድረግ ያለበት በጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊነት ያላቸውን ተዋጊዎችና ለጦርነቱ አስፈላጊ የሆኑ ቁሶች ብቻ እንደሆነ ያሳስባል። በመሆኑም የጦርነቱ ላማ ሊሆኑ የሚችሉት በተፈጥሮ፣ በአቀማመጥ፣ በላማ አልያም በሚሰጡት አገልግሎት ለአንድ ጦርነት የበላይነት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ማናቸውን ይነት ነገሮች ናቸው። በተጨማሪም በጦርነቱ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚዋጉ በመደበኛነት ግን በጦርነቱ ውስጥ እንደ ተዋጊ የማይሳተፉ ግለሰቦችም ጥቃት በሚፈሙበት ወቅት የጥቃት ላማ ሊሆኑ ይችላሉ። ከዚህ በተቃራኒ ማንኛውም በጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ/ኑ/ ግለሰብ/ቦች/ እና ቁስ/ሶች/ ጥበቃ ይደረግላቸዋል።

ከዚህም ባለፈ በውጊያ ወቅት ጉዳት ደርሶባቸው ጥቃት የመፈም አቅማቸውን ያጡ ተዋጊዎችን ከጥቃት የሚጠብቀው ይኸው የመለየት መርህ ነው። በግጭቱ ወቅት በሚሰጡት አገልግሎት ወይም በተለየ ሁኔታ ተጋላጭ በመሆናቸው ምክንያትጉ ልዩ ጥበቃ የሚደረግላቸው ግለሰቦችና ቁሶችም ይገኛሉ። የክምና መስጫ ቦታዎችና የመጓጓዣ አገልግሎት መስጫዎቻቸው በሚሰጡት አገልግሎት ጥበቃ የሚደረግላቸው ቁሶች ሲሆኑክምና ባለሙያዎች፣ የእምነት መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ርዳታ አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች፣ እንዲሁም የሰላም ማስጠበቅ አገልግሎት ላይ የተማሩ ሰዎች በሚሰጡት አገልግሎት ምክንያት ጥበቃ የሚደረግላቸው ግለሰቦች ናቸው። በተለየ ሁኔታ ተጋላጭ በመሆናቸው የተለየ ጥበቃ የሚደረግላቸው ቁሶች ደግሞ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ቦታዎች፣ ቅርሶች፣ እንደ ግድብ ያሉ ከፍተኛ ይል የሚያመነጩና ጨረር የሚረጩ ራዎችና የተፈጥሮ አካባቢ ሲሆኑ፣ ሴቶችና ፃናት ደግሞ በተጋላጭነታቸው ምክንያት ልዩ ጥበቃ የሚደረጉላቸው ናቸው።

 የመለየት መርህን በአግባቡ መፈም ይቻል ዘንድ የተወሰነ የጦር ላማ የሌለው ጥቃት ማድረስ፣ አንድን የጦር ላማ ለማጥቃት የማያስችል ዘዴና የማጥቂያ መሪያዎች መጠቀም፣ እንዲሁም ውጤቱ ሊገደብ የማይችል የጦርነት ዘዴና የማጥቂያ መሪያዎች መጠቀም በጦር ግጭት ወቅት የተከለከለ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት ሁለቱም ወገኖች እንደ ተዋጊ የማይሳተፉ ግለሰቦችን በማጥቃት እርስ በርስ ቢወነጃጀሉም በአሁኑ ወቅት የበይነ መረብና የስልክ መስመሮች በመቋረጣቸው የመረጃዎቹን እውነተኝነትም ሆነ በመሬት ላይ ያለን የጉዳት መጠን ማረጋገጥ አይቻልም። ሆኖም የተባበሩት መንግታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ 30 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሱዳን መሻገራቸውን አስታውል። ይህ ብቻውን ውንጀላዎቹን የሚያረጋግጥ ባይሆንምየተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን አነጋገርን ያሉ እንደ ዘጋርዲያን ያሉ ጋዜጦች በጦርነቱ ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊነት የሌላቸውን ግለሰቦች መጠቃት ሰምተናል ሲሉ መዘገባቸው የሚባለው እውነት ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው። ከዚህ አልፎም በትግራይ ክልል ማይካድራ በተባለ ፍራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተዋጊ ያልሆኑ ግለሰቦች የመገደላቸው ዘገባ አምነስቲ ኢንተርናሽናል በተባለ ገለልተኛ የውጭ ድርጅት ተረጋግጧል። በዚሁ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ ሰብዊ መብቶች ኮሚሽን ዳር 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው የቅድመ ግኝት የምርመራ ውጤት የኮሚሽኑ መርማሪዎች ተዋጊ ያልሆኑ ግለሰቦች ላይ ዘርን መረት ያደረገ ጭፍጨፋ መድረሱን አረጋግጠዋል ማለቱ የግ ድንጋጌዎች መጣሳቸውን ፍንጭ ይሰጣል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. የተሰማው በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማበር ስት መኪኖች ላይ የደረሰው የተኩስ ጥቃት በመለየት መርህ የተሰጠውን ልዩ ጥበቃ የሚጥስ ተግባር ነው። በተጨማሪም ባለፉት ቀናት ውስጥ በመቀሌ ዩቨርቲ ላይ ጥቃት የመድረሱና በግጭቱ መጀመያ ሰሞን ደግሞ የተከዜ ይል ማመንጫ ግድብ በጦር መደብደብ በማበራዊ ድ ች ላይ ሲናፈሱ ከነበሩ መረጃዎች መካከል ይጠቀሳሉ። እነዚህ መረጃዎች ገና በገለልተኛ ቡድን ያልተጣሩ ከመሆናቸውም ባለፈ በኢትዮጵያ መንግት ውድቅ የተደረጉ በመሆናቸው እውነት ናቸው ለማለት አይቻልም። ሆኖም ሁለቱም በጉ ልዩ ጥበቃ የሚደረግላቸው ቁሶች እንደ መሆናቸው ጥሩ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። እነዚህ ቁሶች በሚሰጡት አገልግሎት (ለምሳሌ የትግራይ ልዩ ይል አባላት በውስጣቸው ሆነው ውጊያ ካደረጉ ወይም በውስጣቸው ለጦርነቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ቁሶችን በውስጣቸው ካስቀመጡ)፣ በአቀማመቸው ምክንያት (ለምሳሌ በአቅራቢያቸው እንደ የጦር ካምፕ ይነት ጋዊ የጦር ላማ ኖሮ ዛ ላይ በደረሰ ጥቃት ተጎድተው)፣ አልያም በላማ (ለምሳሌ የትግራይ ልዩ ይል አባላት እነዚህን ቦታዎች ወደ ጋዊ የጦር ላማነት እንደሚቀይሩ በማያወላዳ ሁኔታ ከተረጋገጠ) ጥቃት ደርሶባቸው ካልሆነ በስተቀር በምንም ሌት ጥቃቱ አግባብነት አይኖረውም ማለት ነው።

ከዚህ ባለፈ በአሁኑ ወቅት በሚታይ ሁኔታ በጉ የተሰጣቸው ልዩ ጥበቃ ወደ ጎን ተደርጎ ለአደጋ ተጋልጠው የሚገኙት ሴቶች ናቸው። ሱዳን ከሚገኘው የተባበሩት መንግታት ድርጅት የወሲባዊና ተዋልዶ ጤና ክፍል ሰማሁ ያለ የቢሮው ተወካይ በግጭቱ የመጀመ12 ቀናት ብቻ አንድ አማካሪ ሰባት አስገድዶ መድፈርና ከእዚያ በቁጥር የሚልቁ አካላዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ማነጋገሩን ገልጿል። እነዚህ እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆኑ ወንጀሎች በማን እንደተፈሙ በጥልቀት መመርመር የሚኖርባቸው ቢሆንምበማንኛይነት አግባብ ግን የድርጊቶቹን ወንጀልነት አያስቀርም።

የመወነጃጀል ምታዎች በጦርነቱ ላይ ከሚሳተፉት ቡድኖች በተጨማሪ በተለያዩ ኢትዮጵያውያንና የው ዜጎችም ይስተዋላል። መንግት የመከላከያ ራዊት ሰሜን ዝ ላይ ጥቃት መድረሱንና የአፀፋ ምላሽ በአየር ይል በታገዘ ጥቃት እንደሚሰጥ ካሳወቀበት ለት ጀምሮበተለያዩ የማበራዊ ድች ላይ የተሰሙ የተቃውሞ ጭምጭምታዎች የጥቃቱ ውጤት ሊገደብ አለመቻሉን እንደ ዋና ምክንያት ይጠቅሳሉ። መንግት በበኩሉ ጥቃቱ የተወሰነ ላማ ያለውና በግጭቱ ላይ በቀጥታ ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች እንዳይጠቁ የተቻለው ሁሉ ጥንቃቄ እንደሚደረግ ደጋግሞ ገልጿል።

የመረጃ እጥረት መሬት ላይ ያለውን ሀቅ መዝኖ እንዴት እየተከበረ ወይም እየተጣሰ እንደ ሆነ ለማወቅ መሰናክል ቢፈጥርምከአየር ላይ ጥቃት ማድረስ ግን ብቻውን የጦርነት ግን የማይፃረር ተግባር መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል። ነገር ግን ለማችን የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ምጥቀት እንደ ተዋጊ የማይሳተፉ ግለሰቦች ላይ ምንም ይነት ጥቃት እንዳይደርስ ከሚያደርግበት ደረጃ እንደ አለመድረሱና ግጭቱ የሚካሄድበት ቦታ ብዙ ሰዎች የሚኖሩባቸውን ከተሞች እንደ ማጠቃለሉ አከራካሪው ጉዳይ ጉዳት መድረሱ ሳይሆን የጉዳቱ መጠን ይሆናል።

የትነግ ማከላዊ ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ዳር 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከትግራይ ቴሌዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ጠመንጃ የያዘም ያልያዘም ጦር ጩቤ የያዘ በሙሉ የሚመክተው ጦርነት ነው ሲሉ መግለቸው ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ጎን ያለው አስተያየት ነው። ለዚህም ምክንያቱ ምናልባትም ይህንን ተከትለው የሚወጡና በዚህ ተግባር የሚሳተፉ ግለሰቦች ካሉ አልፎ አልፎ በሚዋጉ በመደበኛነት ግን በጦርነቱ ውስጥ እንደ ተዋጊ የማይሳተፉ ግለሰቦች ውስጥ ስለሚመደቡ ጋዊ የጥቃት ላማ ይሆናሉ። ይህ ደግሞ ከላይ በተጠቀሱት የተለያዩ ምክንያቶች የሚኖረው የጉዳት መጠን ያላግባብ እንዲጨምር ያደርጋል።

ሁለተኛ የሆነው የተመጣጣኝነት መርህ ደግሞ ማንኛም ጥቃት ይገኛል ተብሎ ከሚገመተው ቀጥተኛና የሚጨበጥ የጦር የበላይነት በላይ በጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ/ኑ ግለሰችና ቁስ/ሶች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደማይገባ ይገልል። የሚገኘው የጦር የበላይነት የሚመዘነው በአንድ ጥቃት ሳይሆን ከግጭቱ ጅማሬ እስከ ፍሜው ድረስ በአጠቃላይ ባለው የጥቃት ውጤት ነው። በተጨማሪም የጦርነት እንቅስቃሴዎች ሲካሄዱ ተገቢውን የተመጣጣኝነት መርህ ለመፈም ይቻል ዘንድ ሊደረጉ የሚገባቸው የተለያዩ ቅድመ ጥንቃቄዎች አሉ። እነዚህ ጥንቃቄዎች የመለየት መርህም እንዲተገበር ጉልህ ሚና ይጫወታሉ። ከጥቃት በፊትና በጥቃት ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎችና ከጥቃት ውጤቶች ለመጠበቅ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች በመባል የሚከፈሉት እነህ የጥንቃቄ ይነቶች እንደ አግባባቸው በተያዩ በግጭቱ ውስጥ በሚሳተፉ ወይም በሁሉም ተሳታፊዎች ላይ የሚጣሉ ግታዎች ይሆናሉ።

ከቅድመ ጥንቃቄዎቹ አንዱ የጥቃት ላማዎቹ በጉ አግባብ የተፈቀዱ መሆናቸውን ማረጋገጥ ነው። ከዚህ አልፎም ጥቃት በሚፈምበት ወቅት የሚደርሰው ጉዳት እንደሚልቅ ከታወቀ ጥቃቱን የመሰረዝ ወይም ለጊዜው የማቆም ርምጃ መውሰድ ጥቃቱን ከሚፈመው ቡድን ይጠበቃል። በተጨማሪም እኩል ውጤት የሚያስገኙ አማራጭ የጦርነት ዘዴዎችና የጦር መሪያዎች በሚኖሩ ወቅት በጦርነቱ ላይ ተሳትፎ በሌላቸው ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ልዩነት ታይቶ አነስተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ አማራጮችን መውሰድ ያስፈልጋል።

ሲቪሎች ላይ የሚደርሰን ጉዳት ቢቻል ለማስቀረት አልያም ለመቀነስ እንዲቻል የሚካሄደውን ጥቃት የሚያደናቅፍ እስካልሆነ ድረስ ማስጠንቀቂያ መስጠት፣ ቀጣይነት ያላቸው ቅድመ ጥንቃቄዎች መውሰድ፣ የጦርነት ዘዴዎችና መሪያዎችን ይህንን ግንዛቤ ስጥ በመክተት መጠቀም፣ እንዲሁም ሊከሰት የሚችለውን ጉዳት ከሚገኘው የጦር የበላይነት ጋር ማመዛዘን ከጥቃት በፊትና በጥቃት ወቅት እንዲወሰዱ የሚጠበቁ ርምጃዎች ሲሆኑ መርሆቹንም ለማሳካት ከሚጠቅሙ አራሮች መካከል ናቸው። በተጨማሪም በጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆነ/ኑ/ ግለሰብ/ቦች/ እና ቁስ/ሶች የጥቃቶች ገፈት ቀማሽ እንዳይሆኑ ይቻል ዘንድ ማንኛውም ቡድን በሩ የሚገኙና በዚህ ውስጥ የሚወድቁትን ሁሉ እንዲጠብቅ ብሎም በተቻለ አቅም የጦርነት ላማዎችን ብዙ ዝብ ካለበት አካባቢ እንዲያሸሽ ያስፈልጋል። ተሳታፊ ያልሆኑ ግለሰቦች ከጥቃት አካባቢ የማሸሽ ጥንቃቄ የጥቃት ቦታውን ተቆጣጥሮ የሚገኝ ቡድን ላይ የተጣለ ግዴታ ሆኖ ግለሰቦቹ ከጥቃቱ መዘዞች እንዲተርፉ ያለመ ጥበቃ ነው።

ከላይ በተዘረዘረው መረት ትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ባለው ግጭት ብቻውን የግ ጥሰት የማያስከትለው የአየር ላይ ጥቃት ይህንን መርህ የሚጥስበት አግባብ ሊኖር ይችላል ማለት ነው። ሆኖም ባለው የመረጃ እጥረት ምክንያት በእርግጠኝነት መርሁ ተጥሷል የሚለው ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አይቻልም። በተጨማሪም በጦርነቱ ውስጥ ያሉትን ሁለቱንም ቡድኖች የሚመሩት በጦር ሜዳ ላቅ ያለ ልምድ ላቸው ግለሰቦች እንደ መሆናቸው የሚመርጧቸው የጥቃት ዘዴዎችም ሆነ መሪያዎች በጦር ጉ ውስጥ በተደነገገው መረት ያሉ የተለያዩ ምክረ ሳቦችን ያገናዝባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ሚዛናዊ ፍርድ ለመስጠት ያለው የመረጃና የግልነት እጥረት አሁን ላይ ብቻ ሳይሆን ለወደፊቱም ፈተና ሊጋርጥ የሚችል ነው።

በጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ላይ የሚደርሰውን የጉዳት መጠን ሊወስኑ ከሚችሉ ነገሮች መሀል አንዱ የሆነውን ማስጠንቀቂያ መስጠት በተመለከተ መንግት በመንግት ሚያዎች ጥቃቱ በማንኛውም ሰት እንደሚፈም ገልጿል። ቢሆንም ግን እንደ ኢትዮጵያ ባለች ቴሌዥን የቅንጦት በሆነባት ገር የተሰጠው ማስጠንቀቂያ ምን ያል ተደራሽነት እንዳለው ማወቅ ከባድ ነው። በዚህም ምክንያት ማስጠንቀቂያው ቢሰጥም ጤታማ የሆነ ማሳሰቢያ የሚለውን የግ መፈርት ማሟላቱን አጠራጣሪ ያደርገዋል። በሌላ በኩል የአገር መከላከያ ራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹምራል ብርኑ ጁላየትግራይ ልዩ ይል አባላት በቤተ ክርስያናት ውስጥ መሽገው እንደ ነበርና አሁንም እንይነት ቦታዎችን እየተጠቀሙ መሆኑን አስታውቀዋል። ይህ እውነት ሆኖ ከተገኘ ቡድኑ የጦርነት ላማዎችን ብዙ ዝብ ካለበት አካባቢ እንዲያሸሽ የሚጠበቅበትን ላፊነት በመወጣት ፋንታ ወደ ዝቡ ወስዷል ማለት ነው።

ስተኛው የአስፈላጊነት መርህ ሲሆን ማንኛም የጦርነት ዘዴዎችና የማጥቂያ መሪያዎች ከመጠን በላይ ጉዳትና አላስፈላጊ መከራን በአካልና በመንፈስ ላይ እንዳይፈጥሩ መደረግ እንዳለበት ያሳስባል። የጦር ግጭት ብቸኛ ላማ አንድን ተዋጊ ወይም የውጊያ ቁስ ለጦር ግጭቱ አገልግሎት መስጠት በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ በማድረግ አሸናፊነት መቀናጀት እንጂ ድምማጡን ማጥፋት አይደለም። ስለሆነም ቃይን ማብዛትና ላስፈላጊ ሞት መፍጠር የተከለከለ ነው። ቃይን ማብዛት የሚለካው አንድ ጥቃት በሚፈጥረው መም ደረጃ፣ በሚያስከትለው ሚ አካል ጉዳትና የመሞት ድል ነው። ይህንን ለመከላከል ጥቃቶች ሲፈሙ በጦር ግጭቱ አሸናፊነትን ለመቀናጀት ያል ብቻ ታሳቢ ተደርጎ መሆን አለበት።

የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊትም ሆነ የትግራይ ልዩ ይል በሚያደርቸው እንቅስቃሴዎች ይህንን መርህ ከግምት ውስጥ ያስገቡ መሆን አለባቸው። የመረጃ እጥረት መኖሩና ከአሉባልታ ያለፈ ማረጋገጫ ማስፈለጉ በዚህ መርህ ላይ የኢትዮጵያን ሁኔታ ያገናዘበ ትንታኔ ለመስጠት ለጊዜው ተግዳሮት ይፈጥራል፡፡

የመጨረሻውና አራተኛው የሆነው የሰብዊነት መርህ በማንኛውም በግ ውስጥ በግል ባልተቀመጡ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን በጦር ግጭት ላይ ያሉ ይሎች ግዳጃቸውን ሰብዊነት በተሞላበት ሁኔታ እንዲያካሂዱ የሚያስገድድ የግ ጥበቃ ነው። ይህ መርህ በኢለም አቀፋዊ የግጭት ሁኔታ ላይ እጅግ በጣም ከፍ ያለ ቦታ ያለው ነው። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚጠቀሰው ይህንን የግጭት ሁኔታ የሚደነግገው የግ ማቀፍ ጠባብና የተወሰነ መሆኑ ነው። ሌተና ጄኔራል ባጫ ደበሌ በግጭቱ መጀመያ ወቅት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ መከላከያ ራዊት ሴሮ አካባቢ ያለ ብርጌድ አባላት ልብሳቸው ተገፎ ራቁታቸውን ወደ ኤርትራ እንዲሄዱ ተደርገዋል ሲሉ ገልዋል።

በገለልተኛ አካል ገና ያልተረጋገጠው ይህ መረጃ እውነት ሆኖ የተገኘ እንደ ሆነ የሰብዊነት መርህን ፍፁም የሚጥስ ተግባር ነው። እንደ አስፈላጊነት መርህ ሁሉ ዝርዝር ውስጥ ለመግባት የሚያስችል መረጃ ባለመኖሩ ከዚህ በላይ በጥልቀት ለመግባት በአሁኑ ሰት ቢያስቸግርም መረጃዎች ወደ ፊት መውጣታቸው ስለማይቀር የምንመለስበት ይሆናል።

ከላይ አጠር ባለ ሁኔታ ለመግለ የተሞከረው ግጭቶችን የሚገዛ የግ ማቀፍ መኖሩና በዚሁ ላይ በግል የተቀመጡ ዋና ዋና ክፍሎች ምንነት ነው። ከዋና ዋና ክፍሎቹ ውስጥ የመለየት፣ የተመጣጣኝነት፣ የአስፈላጊነት (ከመጠን በላይ ጉዳትና አላስፈላጊ መከራ ያለ መፍጠር) እና የሰብዊነት መርሆች የጦርነት ጎች መረት ሲሆኑ አንድ ድርጊት በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ መርህ የሚጥስበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል። እነዚህን ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ላግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላትና ሳቦችን ለመቀነስና ነቅሶ ለማውጣት ይረዳናል። የመረጃ እጥረትና የተሳሳቱ መረጃዎች መንሰራፋት በፈጠሩዋቸው እክሎች ምክንያት በዝርዝር ያልተዳሰሱ ነጥቦች ቢኖሩም በመጪዎቹ ዜያት ችግሮቹ ሲፈቱ በጥልቀት ለማየት የምንችልበት ሁኔታ ይፈጠራል። ከዚህም ባለፈ ጎቹን ተላልፎ መገኘት ምን ምን ይነት ላፊነቶች ያስከትላል? በምን ይነት ወንጀል ሥር ይወድቃል? የሚለው ሰፊ ርስ በሌላ ጽሑፍ የሚዳሰስ ይሆናል።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊዋ የመጀመያ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርቲ በእንዲሁም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከኢሴክስ ዩኒቨርቲ በለም አቀፍ የጦርነት ግ አግኝተዋል ጽሑፉ የጸሐፊዋን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...