Saturday, June 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ዕገዳ ተነሳ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙ የባንክ ቅርንጫፎች ሒሳብ ከፍተው፣ በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ባንኮች ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ የተጣለው ዕገዳ ተነሳላቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለደኅንነት ብሎ እንዳይንቀሳቀሱ ዕግድ ጥሎባቸው የነበሩ ሒሳቦች፣ ከማክሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ መንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡

በሕግ ከሚፈለጉና ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንደማይችሉ ዕገዳ ከተጣለባቸው ውጪ፣ በትግራይ በተለያዩ ቅርንጫፎች ሒሳብ ከፍተው በሌሎች ቦታዎች ሒሳባቸውን ማንቀሳቀስ ያልቻሉ የባንክ ደንበኞች ዕገዳ ተነስቶላቸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ዕገዳውን ጥሎ የነበረው በትግራይ ክልል የሚገኙ ቅርንጫፎች ከሲስተም ውጪ በመሆናቸውና የዘረፋ ሙከራዎች ስለነበሩ፣ የሕዝብ ገንዘብ ከመጠበቅ አኳያ ጭምር መሆኑ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምንም ዓይነት የሲስተም ግንኙነት በሌለበት ሁኔታ በትግራይ ክልል ውስጥ ሒሳብ ያላቸው ደንበኞች ገንዘባቸውን ማውጣት አለማውጣታቸው ማረጋገጫ በሌለበት ሁኔታ፣ ከትግራይ ክልል ውጪ በቅርንጫፎች ገንዘብ እንዲያወጡ መፍቀድ አስተማማኝ ባለመሆኑ እንደሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ሪፖርተር ያነጋገርናቸው አንድ የባንክ ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ሒሳቦቹ እንዳይንቀሳቀሱ በማገዱ ምክንያት፣ በተለያዩ ምክንያቶች ትግራይ የነበሩና ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የተመለሱ የባንክ ደንበኞች ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ መቸገራቸውን ሲገልጹ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ክልል ያሉ ከ600 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች እንደ የሁኔታው እየታየ አገልግሎት የሚጀምሩበት ሁኔታ የሚመቻች መሆኑን፣ ብሔራዊ ባንክ ማሳወቁን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች