Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ የቀረቡ የክልል ዕጩዎች

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምርጫ የቀረቡ የክልል ዕጩዎች

ቀን:

ትግራይ ክልልና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዕጩ አላቀረቡም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ታኅሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚያደርገው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተቋሙን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላትን ያስመርጣል፡፡ ከትግራይ ክልልና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስተቀር ክልሎችና አዲስ አበባ ያቀረቧቸው ዕጩዎች ተለይተው ታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከሳምንት በኋላ እንደሚከናወን የሚጠበቀው የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ፣ ለፕሬዚዳንትነት በድጋሚ ከቀረቡት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እንዲሁም ለሥራ አስፈጻሚነት በብቸኝነት ከቀረበው ገዛኸኝ አበራ ውጪ ብዙዎቹ ዕጩዎች በአትሌቲክሱ ዘርፍ የሚጠቀስ የሙያ ድርሻ የሌላቸው መሆኑ ከወዲሁ ጥያቄ አስነስቷል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት ዓመታት በፕሬዚዳንትነትና በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት  ለመምራት የቀረቡ ዕጩዎችን አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች፣ ‹‹ከትግራይ ክልልና ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በስተቀር የቀሩት ክልሎች የዕጩዎቻቸውን ዝርዝር ለፌዴሬሽኑ ልከዋል፡፡ በዝርዝሩ መሠረት ከኦሮሚያ ክልል በስተቀር በስፖርቱ ዕውቀቱም ሆነ ልምዱ ላላቸው አትሌቶች ዕድሉን ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ ክልል የለም፤›› በማለት የታዘቡትን ይገልጻሉ፡፡

ከአራት ዓመት በፊት በጊዮን ሆቴል የተደረገው የፌዴሬሽኑ ምርጫ ከመከናወኑ በፊት፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በስፖርቱ ባሳለፉና ዘርፉን በሚያውቁ እንዲመራ በተለይም ከቀድሞዎቹ ታላላቅ አትሌቶች ጠንካራ አስተያየት ቀርቦ ነበር፡፡

ይሁንና በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከዕጩ አቀራረብ ጋር ተያይዞ በወቅቱ ተነስቶ የነበረው አለመግባባት ቀዝቀዝ ብሎ ምርጫ መደረግ እንዳለበት፣ ችግሩም በሒደት እንደሚስተካከል ከስምምነት ተደርሶ ነበር ምርጫው የተደረገው›› በማለት የነበረውን ሁኔታ የሚያስታውሱ የፌደሬሽን ሙያተኞችም አልጠፉም፡፡

ፌዴሬሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት ክልሎች ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ለምርጫ ያቀረቧቸው ዕጩዎች፣ ለፕሬዚዳንትነት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ከኦሮሚያ፣ አቶ ተፈራ ሞላ ከደቡብ ክልል ናቸው፡፡ አቶ ተፈራ ከአራት ዓመት በፊት ለተመሳሳይ ኃላፊነት ዕጩ ሆነው ቀርበው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት አትሌት ገዛኸኝ አበራ ከኦሮሚያ፣ ወ/ሮ ሳራ ሐሰን ከኦሮሚያ አቶ በላይነህ ክንዴ ላለፉት አራት ዓመት የነበሩ ከአማራ ክልል፣ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ (የፓርላማ አባል) ከአማራ ክልል፣ በዛብህ ወልዴ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ አቶ ነስረዲን መሐመድ ከደቡብ ክልል፣ አቶ ፈሪድ መሐመድ ከሐረሪ ክልል፣ ወ/ሮ ሲቅራ አሊ ከሐረሪ ክልል፣ አቶ ውብነህ በላይ ከሲዳማ ክልል፣ ወ/ሮ ፎዚያ ኢንድሪስ ከአፋር ክልል፣ አቶ አብደላ ኡስማን ከአፋር ክልል፣ አቶ ፖል ቲት ጋች ከጋምቤላ ክልል፣ አቶ ጉሌድ አብዲ ከሱማሌ ክልል፣ አቶ ሐሰን ሙሳ ከሱማሌ ክልልና ወ/ሮ አሻ ኡስማኤል ከሱማሌ ክልል ናቸው፡፡ የትግራይና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ዕጩዎች እንዳላቀረቡ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...