Sunday, June 23, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ አመሻሹን ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ በአካል የታደሙትን የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፓርላማ ውሎ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን እየተከታተሉ አገኟቸው። ሚኒስትሩ ከባለቤታቸው ጋር በድጋሚ እየተከታተሉ አልፎ አልፎ የንግግሩን ይዘት ቀድመው ይናገራሉ] 

 • እዚህ ጋር አላስተረፏቸውም። 
 • እንዴት?
 • አድምጪ. . . እነሱ 15 ዓመት የፈጀባቸውን እኛ 15 ቀን ነው የተቆጣጠርነው ይሏቸዋል. . . አድምጪ፡፡ 
 • እስኪ ነገሩን አታዛባብኝ . . . ሙሉ ይዘቱን ልስማበት እንጂ?
 • አታዛባብኝ ትላለች እንዴ? እነሱ አይደሉ እንዴ ነገሩን ያዛቡት?
 • ምኑን ነው ያዛቡት?
 • የሠራዊቱን ስብጥር ነዋ፡፡ ሌላው ብሔር የለም እኮ? ይኸው አድምጪ ይናገሩታል። 
 • ሠራዊቱ ወገኑ ላይ ጉዳት አለማድረሱ ድንቅ ነው፣ እኔንም አኩርቶኛል።
 • ለዚያ እኮ ነው ጄኔራሎቹን እንደዚያ ያሞካሿቸው።
 • ምን ብለው አሞካሿቸው?
 • አንዱን ድል ቁርሱ. . .  ሌላውን ትንታጉ. . . ግስላው. . .  ምን ያላሉት አለ. . . አድምጫቸው፡፡
 • ደስ ይላል. . . ለእናንተም እንደዚሁ ስያሜ ቢሰጡ ጥሩ ነበር።
 • ምን ማለትሽ ነው?
 • ለእናንተ የካቢኔ አባሎችም ማለቴ ነው።
 • እኛ ደግሞ ምን አድርገን?
 • እንደፈጸማችሁት ስኬት. . . ካልሆነም እንደ ጉደለታችሁ መሰየም ይችላሉ፡፡
 • ወዴት? ወዴት?
 • ለምሳሌ ኮንዶሚኒየም ቁርሱ. . .
 • ኧረ እባክሽ ሴትዮ ተይ? 
 • ስኳር ምሱ. . .
 • ተይ ብዬሻለሁ. . .  አታበሳጪኝ ብያለሁ እንግዲህ. . .
 • ለምን. . .  ነገሩን እንጂ አንተ ላይ አልደረስኩ? 
 • አንቺ ባትደርሽም መድረሱ አይቀርም፡፡
 • እንዴት? አንተ እንደሆነ በሥራህ ስኬታማ ነህ፡፡ 
 • ተይኝ አልኩ እኮ? 
 • እሺ እራት ይቀረብልህ?
 • ኧረ ተይኝ አንቺ ሴት. . .ተይኝ?
 • እራት እኮ ነው ያልኩት? 
 • እሱ እራት እንዳልሆነ ገብቶኛል። 
 • ምኑ ነው የገባህ? 
 • ምን ቁርሱ. . . እንዳልሽው በእራት አስታከሽ ወደ እኔ ልትመጪ እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ 
 • ስትሸነሽነው ያልፈራህ ስያሜውን ፈራህ? እኔ ባለማምድህ አይሻልህም?
 • አፈንጂው በቃ፡፡
 • አሥር ሺሕ ካሬ ሜትር እራቱ!

[ከፍተኛ አማካሪው የሰሞኑን የሥራ ክንውን ሪፖርት ለሚኒስትሩ እያቀረበ ነው]

 • የውጭ አጋሮቻችን የሚያደርጉትን ድጋፍ መቀጠል ይችሉ እንደሆነ ላቀረቡት ጥያቄ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
 • ለምንድነው መጀመርያ ያቋረጡት?
 • ምንም ዓይነት ግንኙነት ከዚህ ክልል ጋር እንዳይደረግ መንግሥት በመወሰኑ ነዋ ክቡር ሚንስትር።
 • ኦ. . . ውሳኔው የውጭ አጋሮችንም እንደሚነካ አላስተዋልኩም ነበር። 
 • በዚህ ክልል ለምናከናውናቸው ሥራዎች የበጀት ምንጮቻችን አጋሮች በመሆናቸው፣ እንዴት ሥራውን መቀጠል እንደሚቻል እየጠየቁ ነበር። 
 • ተገቢ ማብራሪያ እንዲያገኙ አድርግ። 
 • የክልሉ አመራር ወደ ከተማው እየገባ መሆኑ ተነግሯቸዋል፡፡
 • ምን . . . ከተማውን ደግመው እየተቆጣጠሩት ነው? 
 • እነማን?
 • የክልሉ አመራር አላልክም አንዴ አሁን?
 • ጊዜያዊ አመራሩን ማለቴ ነው። 
 • የቀድሞዎቹ እንደወጡ ነው አይደል? 
 • ከእኔ እርስዎ አይቀርቡም ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ምን ግንኙነት አለኝ ከእነሱ?
 • ኧረ እንደዚያ አልወጣኝም።
 • ምን እያልክ ነው ታዲያ?
 • ቅርብ ነዎት ያልኩት የካቢኔ አባል በመሆንዎ ለመረጃ ቅርብ ነዎት ማለቴ ነው! 

 

[ሚኒስትሩ ከአንድ የአውሮፓ ዲፕሎማት ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው] 

 •  ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ አሁንም ያሳስበናል።
 • ያለንበት ሁኔታ እንዳሳሰባችሁ እንገነዘባለንሐሳባችሁንም እንደ ወዳጅ አገር እናደንቃለን፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ውጊያው መጠናቀቁን እናንተ ብትገልጹም የክልሉ አመራሮች ግን ሌላ ነገር ነው እየገለጹ ያሉት።
 • የትኛው አመራር?
 • ተቀናቃኙን የክልሉ አመራር ማለቴ ነው። 
 • ክልሉ አንድ አመራር ነው ያለው፣ እሱም በክልሉ ዋና ከተማ ተቀምጦ ሥራውን ለመጀመርዝግጅት ላይ ይገኛል።
 • የቀድሞው አመራርስ? 
 • መንግሥታችን ስለዚህ ቡድን ሁኔታ አይጨነቅም። 
 • እና ምንድነው የሚሆነው?
 • ምርጫውን ለራሱ ትተንለታል። 
 • ምን ዓይነት ምርጫ? 
 • ወይ እጁን ሰጥቶ በሕግ እንዲዳኝ ወይም በመረጠው መንገድ መቀጠል ይችላል። ከዚህ በኋላ ግን የክልሉ አመራር በሕግ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ነው።
 • ከከተማዋ የወጣው የቀድሞው አመራርስ በክልሉ የሚኖረው ድርሻ ምንድነው?
 • ታጥቆ ወደ ጫካ የገባ የሚኖረው ድርሻ ምን ሊሆን እንደሚችል አብረን እናያለን። 
 • ስለዚህ መንግሥት ዋና ተልዕኮውን አጠናቋል እያሉኝ ነው?
 • አጠናቆ ወደ መንግሥታዊ ተግባር ተመልሷል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሐዘን ለመድረስ ጎረቤት ተገኝተው ለቀስተኛው በሙሉ የሚያወራው ነገር አልገባ ብሏቸው ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ባለቤታቸውን ስለጉዳዩ እየጠየቁ ነው] 

ጎረቤታችን ሐዘን ለመድረስ ብሄድ ለቀስተኛው በሙሉ በሹክሹክታ ያወራል። ግን የሚያወሩት ነገር ሊገባኝ አልቻለም። ምንድነው የሚያወሩት? እኔ ምን አውቄ? እንዴት? የሚያወሩትን ምንም አልተሰማሽም? እኔ እንድሰማ የፈለጉ አይመስልም ግን ... ግን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...