Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልአራተኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሞዛይክ ፋሽን ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

  አራተኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሞዛይክ ፋሽን ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

  ቀን:

  አራተኛው አፍሪካ ሞዛይክ የፋሽን ፌስቲቫል ከታኅሳስ 12 እና 14 ቀን 2013 ለገጣፎ በሚገኘው የዲዛይንና ማምረቻ ማዕከል እንደሚካሄድ አፍሪካ ሞዛይክ አስታውቋል፡፡

  አንድ ሺሕ የሚሆኑ የንግድ፣ የመንግሥት አካላት፣ ዲፕሎማቶች፣ ዲዛይነሮችና ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በፋሽን ፌስቲቫሉ እንደሚታደሙ አፍሪካ ሞዛይክ ለሪፖርተር በላከው በግለጫ አሳውቋል፡፡

  አራተኛው አፍሪካ ሞዛይክ ፋሽን ፌስቲቫል ላይ 25 የሚሆኑ ዘርፈ ብዙ ዲዛይነሮች ሥራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ በዚህ ዓመት የኮሮና ቫይረስ በመኖሩ በዲጂታል መገናኛ ብዙኃን ለዓለም አቀፍ ተመልካቾች የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

  የፋሽን ፌስቲቫሉ የሚካሄደው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተቀመጡ ፕሮቶኮሎችን ተግባራዊ በማድረግ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡

  ማዕከሉ የአገር ውስጥ ዲዛይነሮችን በማበረታታትና በማብቃት ከንግድ ማኅበረሰቦች ጋር አብረው እንዲሠሩ የሚያመቻች ሲሆን፣ የአገር ውስጥና አፍሪካ ፋሽን ኢንዱስትሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡ ለሁለት ቀን በሚቆየው የፋሽን ትርኢት ፌስቲቫል የአልባሳቶችና ጌጣጌጦች ሽያጭ ለታዳሚዎች ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

  በተጨማሪም የፈርኒቸር ዲዛይን፣ የአርት ማሳያዎች፣ የፈጠራ ሥራዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ወደ ዘርፉ ብቅ የሚሉ አዲስ ዲዛይነሮች ልምድ የሚካፈሉበትና የሚማሩበት መድረክ ነውም ተብሏል፡፡

  አፍሪካ ሞዛይክ ፋሽን ፌስቲቫል በተለያዩ ጊዜያት በሚኖው መድረክ አዲስ ነገር ለማሳየት የሚሞክርና ወደ ዘርፉ የሚገቡ አዳዲስ ዲዛይነሮችን በመደገፍ የጀመረ ነው፡፡ ገቢውም ለችግር የተጋለጡ ሕፃናትን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

  ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የፋሽን መሰናዶ ከኢትዮጵያና ከውጭ የሚሳተፉ ዲዛይነሮች ሥራቸውን ያቀርባሉ፡፡ የፋሽን ዲዛይነሮች ሜሮን አብርሃ፣ መዓዛ በየነ፣ ሰሎሜ ክፍሉ፣ ፍቅርተ አዲስ፣ ለምለም ተክለሃይማኖትና ሌሎችም ይሳተፋሉ፡፡ በቦርሳና በጫማ ዘርፍ ኬኒ አለን፣ ዳኔል ታደሰ፣ ሚሊኪ አበራና ዮናታን አሥራት የሚሳተፉ ይሆናል፡፡ በጌጣጌጥ ደግሞ መክሊት ጌታቸው ትሳተፋለች፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...