Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልአሥሩም ክልሎች የሚሳተፉበት ‹‹ወይዘሪት አንድነት›› የቁንጅና ውድድር በሸገር ፓርክ ይካሄዳል

አሥሩም ክልሎች የሚሳተፉበት ‹‹ወይዘሪት አንድነት›› የቁንጅና ውድድር በሸገር ፓርክ ይካሄዳል

ቀን:

ከአሥሩ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ቆነጃጅት የሚሳተፉበት ‹‹ወይዘሪት አንድነት›› የቁንጅና ውድድር ዛሬ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. በሸገር ፓርክ ይካሄዳል፡፡

ፌዴሬሽን ምክር ቤትና ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይንመንት በጋራ ያዘጋጁት የ‹‹ወይዘሪት አንድነት›› የቁንጅና ውድድር፣ የ15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል አካል ነው፡፡ በዕለቱም የተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚካሄዱ የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴንመንት መሥራች አቶ ሞቲ ሞረዳ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሞቲ እንዳሉት፣ ‹‹እኩልነትና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ለጋራ ብልጽግና›› በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 15ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚካሄደው የቁንጅና ውድድር፣ በየክልሎቹ የተካሄደው ውድድር አካል ሲሆን፣ ማጠቃለያው በሸገር ፓርክ ይከናወናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኢትዮጵያ በርካታ ብሔር ብሔረሰቦችን አቅፋ የያዘች ሃገር መሆኗን የተናገሩት አቶ ሞቲ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣውን የእርስ በርስ ቁርሾ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ በመሆኑ፣ በውድድሩ የሚያሸንፉ አንድነትና ሰላም ላይ እንዲሠሩ ይታገዛሉ ብለዋል፡፡

ተወዳዳሪዎቹ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አሸንፈው በመጨረሻው ዙር ለመሳተፍ ዝግጅቱን አጠናቀዋል ተብሏል፡፡ የመጡበትን ክልሎች ውበት፣ ባህል፣ ወግና ሥርዓት በማጉላትና ከልዩነት ይልቅ አንድነትን የሚያጠናክሩ ዕሴቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ውድድሩ እንደሚጠቃለልም ተገልጿል፡፡  

የዚህ ውድድር በዋነኝነት ወጣቶች በሰላምና አንድነት ዙሪያ ቁልፍ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አዘጋጆቹ ተናግረዋል፡፡ አሸናፊዎች ስለ ሰላምና አንድነት በየክልሉ እየዞሩ የሚያስተምሩም ይሆናል፡፡ በ2014 ዓ.ም. ‹‹ወይዘሪት አንድነት›› ውድድር በቀጣይ እንደሚካሄድ የኢስት አፍሪካ ኢንተርቴንመንት ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃድ ተናግረዋል፡፡

ወጣቶች በሰላምና በአንድነት ዙሪያ በሰፊው እንዲሠሩ ለማድረግ በተዘጋጀው ውድድር የትግራይ ክልል እንዲሳተፉ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር እየተሠራ መሆኑን አቶ ሞቲ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በመተባበር በውድድሩ በተሠራው ሥራ የሚሳተፉ መኖራቸውን አክለዋል፡፡ በሌላ በኩል ኅዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ደግሞ በአንድነት ፓርክ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የሽልማት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...