Wednesday, February 21, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የዓለም ባንክ በመስከረም ወር ከፈቀደው ብድር በተጨማሪ የ512.5 ሚሊየን ዶላር ብድርና ዕርዳታ ስምምነት ፈረመ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያና ዓለም ባንክ መካከል 512. 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የብድርና ዕርዳታ ስምምነት ተፈረመ፡፡ 

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ኤርትራና ጅቡቲ ተወካይ የሆኑት ዑስማን ዲዮን ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት 312.5 ሚሊየን ዶላሩ ዕርዳታ ሲሆን 200 ሚሊየን ዶላሩ ደግሞ ብድር ነው፡፡

ገንዘቡ በኢትዮጵያ እየተከናወነ የሚገኘውን የምግብ ዋስትና መርሐ ግብር ለማጠናከርና ከዚህ ቀደም በመርሐ ግብሩ ያልተካተቱ ተጨማሪ ቦታዎችን ለማገዝ እንደሚውል ተገልጿል።

መርሐ ግብሩ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችንና በድርቅ ምክንያት ለምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡

የዓለም ባንክ ባለፈው መስከረም ወር 2013 ዓ.ም. 400 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ መንግሥት መፍቀዱ ይታወሳል።

ባንኩ በመስከረም ወር የፈቀደው 400 ሚሊዮን ዶላር ብድር በመላ አገሪቱ ለሚፈጸም የከተማ ሴፊቲ ኔት ፕሮግራም የሚውል ነው።

ከተገኘው ብድር ገቢ ለሌላቸው ወይም ራሳቸውን መደገፍ የማያስችል ዝቅተኛ ገቢ ለሚያገኙ ኢትዮጵያዊያን የከተማ ነዋሪዎችና ስደተኞች የሥራ ዕድል መፍጠሪያ የሚውል እንደሆነም ባንኩ ያወጣው መረጃ ያመለክታል። 

በዚህ ብድር በመላ አገሪቱ 83 ከተሞች የሚገኙ 816,000 ስደተኞችን ጨምሮ የከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መረጃው ያመለክታል። 

በፕሮጀክቱ የሚታቀፉ ነዋሪዎች እንደ ከተማ ፅዳት በመሰሉ ማኅበራዊ ሥራዎች ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ ክፍያ የሚያገኙ ሲሆን፣ እርጅና ለተጫናቸው አቅመ ደካሞችና አካል ጉዳተኞች ላሉት የከተማ ደሃዎች ደግሞ ራሳቸውን ማኖር የሚችሉበት ወርኃዊ ክፍያ በነፃ የሚያገኙበት እንደሆነም መረጃው ያመለክታል። 

ይህ ዓይነቱ የከተማ ሴፊቲ ኔት ፕሮግራም ከተጀመረ በርከት ያሉ ዓመታት የተቆጠሩ ሲሆን አሁን ከዓለም ባንክ የተገኘው ብድር ይህንኑ ፕሮጀክት ለቀጣይ ዓመታት ማስቀጣያ የሚውል ነው። 

በዚህም መሠረት የዓለም ባንክ በሦስት ወራት ውስጥ በድምሩ 912 ሚሊየን ዶላር ብድርና ዕርዳታ ለኢትዮጵያ መንግሥት የፈቀደ ሲሆን፣ የተገኘው የገንዘብ ድጋፍ በወቅታዊው የምንዛሪ ተመን መሠረት 34.6 ቢሊዮን ብር ነው

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች