በተለያየ የወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ላይ የመያዣ ትእዛዝ መውጣቱን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ኮማንደር ሰለሞን አብርሃ ብስራት፣ ኮማንደር ሀይለማርያም ብርሃኔ ገ/ማርያም፣ ም/ኢ/ር ክብሮም ገብሩ ገ/እግዚአብሄር፣ ም/ኢ/ር አረጋዊ ገ/ሂወት አስፋዉ፣ ረ/ኢንስፔክተር ገዛኢ ገ/ሂወት ገ/ስላሴ፣ ረ/ኢንስፔክተር ተስፋ ኪሮስ ግደይ፣ ረ/ኢንስፔክተር አርአያ ገ/አናንያ ኪዳኑ፣ረ/ኢንስፔክተር ሰለሞን ወላይ ወ/አብዝጊ፣ ዋ/ሳጅን ሀይላይ ወልዱ ገ/ማርያምና ዋ/ሳጅን ሀፍቱ ካህሳይ አብርሃ መሆናቸውንም ተናገሯል፡፡ ኮሚሽኑ እንደገለጸው፣ ተጠርጣሪዎቹ መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ወደ ጐን በመተው፣ መቀመጫቸውን ትግራይ ክልል በማድረግ የህዋሃት ከፍተኛ አመራሮች ተልዕኮ በመቀበል፣ በጽንፈኝነት አስተሳሰብ በመነሣት በሀይል ወደ ስልጣን የመምጣት ፍላጎትን ካነገቡ ሀይሎች ተልዕኮ በመቀበል፣ በሀገር ውስጥ ሌሎችን በማደራጀት አገር የመበተን፣ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠርና ህገ-መንግስታዊ ሥርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ውስጥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በመሳተፍ፣ ህዝብ በመንግስት ላይ አመኔታ እንዳይኖረው በማድረግ፣ በአገር ክህደትና በሰብአዊ መብት ጥሰት ወንጀል መጠርጠራቸውን ዘርዝሯዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በተለያየ የአመራር ደረጃ ላይ የነበሩመሆናቸውንም አስታውቋል፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -