Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየፕላንና ልማት ኮሚሽን ኦዲት ሪፖርትን ለማዳመጥ የተጠራው ስብሰባ ያለ ስምምነት ተበተነ

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኦዲት ሪፖርትን ለማዳመጥ የተጠራው ስብሰባ ያለ ስምምነት ተበተነ

ቀን:

ሰኞ ኅዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም. የፕላንና ልማት ኮሚሽን የዘላቂ ልማት ግቦችን ለመፈጸም ያለው ዝግጁነት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን ለመገምገም፣ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤትና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተጠራው ይፋ የሕዝብ ውይይት ያለ ስምምነት ተበተነ፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን 2008 እስከ 2011 .ም. የክዋኔ ኦዲት ግኝት ላይ ይፋዊ የውይይት መድረክ ለማድረግ ተጠርቶ የነበረው ስብሰባ፣ የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባቀረበው የማጠቃለያ ኦዲት ሪፖርት ላይ በሁለቱም አካላት ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ምክንያት ምክር ቤቱ የጠራውን ውይይት እንዲሰርዝ መገደዱ ተገልጿል፡፡

የዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኦዲት ሪፖርት በዋናነት የዘላቂ ልማት ግቦች 2030 አጀንዳን በአገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ በየደረጃው ተካተው መታቀዳቸውን፣ ከምዕተ ዓመቱ ልማት (MDG) ወደ ዘላቂ ልማት (SDG) የሚያሸጋግር ፍኖተ ካርታ (Roadmap) መዘጋጀቱን በተመለከተ፣ እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦች (2030 አጀንዳዎች) በአገሪቱ ብሔራዊ መሪ የልማት ዕቅድ ውስጥ ተካተው መታቀዳቸውን በተመለከተ የሚሉትና ሌሎችም ነበሩ፡፡

ለውይይት በቀረበው የዋና ኦዲተር ሪፖርት እንደሚያመለክተው ከምዕተ ዓመቱ ልማት ግቦች ወደ ዘላቂ ልማት ግቦች የሚያሸጋግር ፍኖተ ካርታ አለመዘጋጀት፣ የዘላቂ ልማት ግቦችና የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፍርሜሽን ዕቅድን ተግባራዊ የሚያደርጉ ፈጻሚ አካላትን ድርሻ በግልጽ ያላስቀመጠ፣ አጋሮችና ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሚና በግልጽ ለይቶ የማያሳይ ነው የሚሉ ይገኙበታል፡፡

የኦዲት ግኝቱ ከዚህ በተጨማሪም ለዘላቂ ልማት ግቦች ትግበራ የሚሆን ፋይናንስ የሚያፈላልግ ኮሚቴ አለመዋቀሩ፣ እንዲሁም አገሪቱይናንስ የምታገኝበትን መንገድ የሚያመቻች ግብረ ኃይል አለመቋቋሙን አሳይቷል፡፡

ዋና  ኦዲተር አቶ ገመቹ ዲቢሶ ምንም እንኳ የዘላቂ ልማት ግቦችን በየዘርፉ ለመተግበር የሲቪክ ማኅበራት ወሳኝ ሚና እንደሚኖራቸው ቢታወቅም፣ ዕቅዱ ውስጥ የግሉ ዘርፍና የሲቪክ ማኅበራት ከዘላቂ ልማት ግቦች ጋር በተያያዘ የሚሠሩዋቸው በተገቢው እንዳልተካተተ ያሳያል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስታስቲክስ ሥርዓት የዘላቂ ልማት ግቦችን የመሰብሰብ አቅሙ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑና የአመላከቾችን መረጃ የሚይዝበት ቋት፣ (ዳታ-ቤዝ) እንዲሁም የዘላቂ ልማት ግቦችን የሚያመላክቱ ወቅታዊ የሆነ መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችለው ዕቀድ አለመዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡

የኦዲት ሪፖርቱ ይህን ይበል እንጂ የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍፁም አሰፋ (ዶር) በበኩላቸው፣ ምንም እንኳ የዋና ኦዲተር ግኝት ሪፖርት የቀረበው ባለፈው ዓመት መጋቢት 2012 ዓ.ም. ቢሆንም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማስፈጸም የልማት አጋሮች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የኦዲት ሪፖርቱ በቀረበበት መንገድ ኢትዮጵያን መወከል አስፈላጊ ስላልሆነ፣ ተጨማሪ አንድ ውይይት በማድረግ ከልማት አጋሮች ጋር ሊያስማማ የሚችል ሪፖርት ይዞ ለመቅረብ በማሰብ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎችን እንዴት እንደምታስፈጽምና በምን ዓይነት አግባብ እንደምታስተናግዳቸው በደንብ መታየት ስላለበት፣ ለኦዲት ሪፖርቱ መልስ ለመስጠትና ለመወያየት  የኮሮና ወረርሽኝ ተፅዕኖ እንደፈጠረባቸው ኮሚሽነሯ  ገልጸዋል፡፡

ጉዳዩ ያልተዋጠላቸው የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው የኦዲት ሪፖርት ተሠርቶ ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ  አንድ ዓመት ያህል ድረስ መጠበቅ ያልተለመደ አሠራር ከመሆኑም በላይ፣ ኮሚሽኑ ለሪፖርቱ ትኩረት እንዳልሰጠ ማሳያ ነው የሚሉ አስተያቶች ተሰንዝረዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ መሐመድ የሱፍ ዋና ኦዲተር ያቀረበውን ውይይቱ ቢራዘም የተሻለ የኦዲት ርፖርት ሊመጣ ይችላል የሚለውን ሐሳብ በመደገፋቸው፣ የተጠራው ስብሰባ ተበትኖ ለሌላ ቀን እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...