Friday, July 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

የአውሮፓ ኅብረት ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

ቀን:

የአውሮፓ ኅብረት ኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር ሆና እንደምትቀጥል አስታወቀ፡፡ የአውሮፓ ኅብረት የግጭት አወጋገድ ኮሚሽንና ጃኔዝ ሌናርሲች ኢትዮጵያ በቀጣናው ላይ ቁልፍ የመረጋጋት ምሳሌ እንድትሆን እንጂ፣ ግጭቶች የሚዛመቱባት እንዳትሆን ኅብረቱ ፍላጎቱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‹‹ሰላም፣ መረጋጋት፣ ብልፅግና፣ እንዲሁም እየተከናወኑ ያሉት ሪፎርሞች ዕውን እንዲሆኑ የአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡ በሱዳን የሁለት ቀናት ጉብኝት ከትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ወደ 50,000 ሺሕ የሚጠጉ ስደተኞች፣ የረድዔት ሥራ ከሚያከናውኑ ተቋማትና ከሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ቆይታ እንዳደረጉ የገለጹት ሌናርሲች፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ  ይቀርብ ዘንድ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ኅብረቱ ይጠይቃል፤›› ብለዋል፡፡  

ነዳጅ፣ መድኃኒትና ምግብ ነክ አቅርቦቶችን በክልሉ በአግባቡ ለነዋሪዎች ይደርስ ዘንድ ትልቅ ኃላፊነት ወስዶ መንግሥት መሥራት አለበት ያለው ኅብረቱ፣ በክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጿል፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ ይሁንታ ቢሰጥም፣ በውስን ቦታዎች ላይ ብቻ ለማቅረብ መፈቀዱና እያንዳንዱ የኅብረቱ እንቅስቃሴና ተግባር ፈቃድ እየተጠየቀ የሚከናወን በመሆኑ፣ ብዙ ርቀት እንዳይሄድ ሊያደርገው ይችላል ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በተለያዩ መንገዶች ከትግራይ ክልል የተለያዩ ያልተረጋገጡ መረጃዎችና ጭምጭምታዎች እንደሚመጡ፣ ነገር ግን የግንኙነት ዘዴዎች በመቋረጣቸው የመረጃዎችን እውነተኛነት ማረጋገጥ አልተቻለም ብለዋል፡፡

ሌናርሲች ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹የአውሮፓ ኅብረትና አባላት አገሮች መንግሥት በግንባር ቀደምትነት በክልሉ በግጭቱ የተጎዱ አካባቢዎች እንዲደርሱ በሩን መክፈት አለበት፤›› ብለዋል፡፡ በተለይም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በነፃነት ገብተው ተልዕኳቸውን በዓለም አቀፍ ሕግና የሰብዓዊነት መርህን በመያዝ ከአድልኦ የነፃ፣ ገለልተኛና ነፃ የማጣራት ተግባር እንዲያከናውኑ መንግሥት ሊፈቅድ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በግጭቱ ተፈናቅለው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን መንግሥት እንዲመለሱ ማስገደድ የለበትም ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ስደተኞቹ መመለስ ያለባቸው አካባቢያቸው ደኅንነቱ የተረጋገጠና ዳግም ለግጭት የሚዳርግ ችግር አለመኖሩ ሲረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ አበክረው ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ የአውሮፓ ኅብረት ቁልፍ አጋርነቷን ደጋግመው የገለጹት ሌናርሲች፣ በቀጣናዊ መረጋጋትም የኢትዮጵያ ሰላም መሆን ወሳኝ እንደሆነ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተያያዘም ፈረንሣይን በመወከል በኅብረቱ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በሱዳን የጎበኙት ኤሪክ ቼቫሊየር በበኩላቸው፣ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ለብዙ ዓመታት የቆየና ሥር የሰደደ ግንኙነት እንዳላት የኢትዮጵያ ሰላም ማጣት እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል፡፡

የሰብዓዊ ዕርዳታና አገልግሎት አቅራቢዎች ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ተከትለው ለሚያከናውኑት ተግባር፣ የፈረንሣይ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በኤልያስ ተገኝ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አቶ ሰብስብ አባፊራ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

ከአዋጅና መመሪያ ውጪ ለዓመታት ሳይካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ...

ቀጣናዊ ገጽታ የያዘው የኢትዮ ሶማሊያ ውዝግብ

ከአሥር ቀናት ቀደም ብሎ በተካሄደው የፓርላማ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ፣...

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዓረቦንና የጉዳት ካሳ ክፍያዎች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ መጣሉን ተቃወሙ

በአዲሱ ተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ውስጥ የኢንሹራንስ ከባንያዎች ለሚሰበስቡት...