Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የአኖካ ሽልማት ተበረከተላቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የአኖካ ሽልማት ተበረከተላቸው

ቀን:

የአፍሪካ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የዕውቅና ሽልማት (ኦርደር ኦፍ ሜሪት) አበረከተ፡፡

አኖካ በአዲስ አበባ ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው ልዩ ስብሰባ አጋጣሚ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተበረከተውን ሽልማት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር) ተቀብለዋል፡፡

እንደ አኖካ ፕሬዚዳንት ሙስተፋ ቤራፍ አገላለጽ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ የተበረከተው ሽልማት መሪዎች ለኦሊምፒክ ስፖርት ማደግ ለሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ዕውቅና የሚሰጥ ነው፡፡ ዕውቅናው ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች መሪዎች እንደተበረከተም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ለኢትዮጵያ ስፖርት ካበረከቷቸው መልካም ጅምሮች መካከል፣ ለኦሊምፒክ መንደር ግንባታ አስፈላጊነትና ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት የሰጡት ድጋፍ ለአኅጉራዊው ከፍተኛ ዕውቅና እንዳበቃቸው በመድረኩ ተነግሯል፡፡

ሚኒስትሯ ሒሩት ካሳው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለየት ከሚያደርጋቸው ባህሪያት መካከል የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ  በመጠቀም፣ ከዚህ በፊት ላልተገባ ዓላማ ወደ ጽሕፈት ቤታቸው ያመሩ የሠራዊት አባላትን ያረጋጉበትን አጋጣሚ ምሳሌ አድርገው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ወጣቶች ለስፖርትና ለበጎ ዓላማ ትኩረት እንዲሰጡ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሮጀክት የሆነውን የእንጦጦ ፓርክ የስፖርት ማዘውተሪያ ማድረጋቸውን ጭምር ለአኖካ አመራሮች አስረድተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...