Thursday, May 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ አቀባበል በ “28 ሚኒ ስታዲየም”

ትኩስ ፅሁፎች

በተለያዩ ከተሞች ሲዘዋወር የቆየው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ፣ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ላይ ይገኛል፡፡ ይኸው ዋንጫ ባለፈው ሳምንት ማረፊያውን ያደረገው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ሲሆን፣ ከክፍለ ከተማው በአውቶሞቢል ተጭኖ በወረዳው በሚገኘው 28 ሜዳ (ሚኒ ስታዲየም) በርካታ ነዋሪዎች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡ ከወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ማኅበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው፣ በወረዳው ለታላቁ ህዳሴ ግድብ 6.5 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፡፡ ለህዳሴ ግድቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ባለሃብቶች የህዳሴ ግድብ ዋንጫውን በመያዝና ቤታቸው ድረስ በመሄድ የእንኳን ደስ ያላችሁ ምስጋና መከናወኑም ተገልጿል፡፡  በሥነ ሥርዓቱ ማጠቃለያም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋንጫን፣ ባለተራው ወረዳ 07 አስተዳደር ከወረዳ 06 ተረክቦ በሠረገላ ጭኖ በታላቅ አጀብ ጉዞ አድርጓል፡፡ ፎቶዎቹ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫአቀባበል እስከ አሸኛኘት ድረስ የነበረውን ድባብ በከፊል ያሳያሉ፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ

የታላቁ ህዳሴ

  • ፎቶ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች