ጋዜጠኛና ጦማሪ ሎቲፍ ዋዳ፣ ፋሲል ከነማ ከቱኒዝያው ዩኒየን ስፖርቲቭ ሞናስቲር ጋር የተጫወተበትን የአዲስ አበባ ስታዲየም በተመለከተ በትዊተር ገጹ ላይ የሰነዘረው አቃቂር፡፡ ለዘንድሮው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ኢትዮጵያን የወከለው ፋሲል ከነማ፣ በቅድመ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ግጥሚያውን በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዕውቅና ባለው የባህር ዳር ስታዲየም ያላከናወነው በሰሜን ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት ነው፡፡ ፋሲል ከነማ እንግዳውን ቡድን ኅዳር 27 ቀን 2013 ዓ.ም. 2ለ1 ያሸነፈበት የአዲስ አበባ ስታዲየም ደረጃውን ያልጠበቀ ነው በሚል ከዓመታት በፊት በካፍ ቢታገድም፣ ይህን ግጥሚያ ያለ ተመልካች እንዲያስተናግድ አኅጉራዊው ተቋም የፈቀደው የአገሪቱን ችግር ከግምት አስገብቶ ነው፡፡