Saturday, December 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የመንግሥት ፋብሪካዎች ገቢ ከዕቅዳቸው በታች መሆኑ ታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካ ብቻ ከዕቅድ በላይ ገቢ አግኝቷል

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ሳምንታት የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አብዛኛዎቹ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወቅታዊ የሥራ አፈጻጸም የታሰበውን ያህል ያለመሆኑ ነው፡፡

ኤጀንሲው በሥሩ ከሚገኙ 22 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውስጥ እስካሁን 15ቱን የ2013 የመጀመርያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸምን ሰሞኑን ያሳወቀ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ በሩብ ዓመቱ እንደርስበታለን ብለው ያቀዱትን ያህል ገቢ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ለሩብ ዓመቱ ያስገኛሉ የተባለውን ያህል ገቢና ትርፍ ካለማስመዝገባቸውም በላይ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲመዘኑም አፈጻጸማቸው አነስተኛ ስለመሆኑ በኤጀንሲው በኩል የወጡ አኃዛዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በአምራች ዘርፍ የተሰማሩት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ ብሔራዊ አልኮልና አረቂ ፋብሪካ፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን፣ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕና የኢትዮጵያ ፕልፕና ወረቀት አክሲዮን ማኅበር በመጀመርያ ሩብ ዓመት በጊዜያዊ የሒሳብ መረጃ መሠረት ብር 2.5 ቢሊዮን አጠቃላይ ገቢ ለማግኘት አቅደው 747.85 ሚሊዮን ብር ማግኘት ችለዋል፡፡ ይህም በሩብ ዓመቱ ከዕቅዳቸው ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ ያነሰ መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ከነዚህ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሥር ካሉት አምስት ድርጅቶች ከዕቅዱ በላይ ገቢ ያስገኘው የብሔራዊ አረቂ ፋብሪካ ብቻ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ አራቱ ድርጅቶች ግን ከዕቅዳቸው በእጅጉ ርቀው ታይተዋል፡፡ በኤጀንሲው መረጃ መሠረት ብሔራዊ አልኮልና አረቂ ፋብሪካ 149.67 ሚሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 194.97 ሚሊዮን ብር ማግኘት የቻለ ሲሆን፣ በ2011 የመጀመርያው ሩብ ዓመትም ሆነ በሙሉ በጀት ዓመቱ ከሁሉም ብልጫ ያለው አፈጻጸም ያሳየ ነበር፡፡ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ፣ የቀድሞ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ደግሞ በሩብ ዓመቱ ከምርት ሽያጭ፣ ከድኅረ ሽያጭ አገልግሎት፣ ከተሰብሳቢና ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ 1.31 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ለማግኘት አቅዶ 395 ሚሊዮን ብር ብቻ መፈጸም ችሏል፡፡ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብር 95 ሚሊዮን በማቀድ ብር 93 ሚሊዮን ብር ማግኘቱ ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ፕልፕና ወረቀት አክሲዮን ማኅበር 64.40 ሚሊዮን ብር አቅዶ አፈጻጸሙ 31.48 ሚሊዮን ብር ሆኗል፡፡ ኬሚካል ኢንዱስትሪዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ ያገኘው ገቢ 428 ሚሊዮን ብር ሆኗል፡፡

ከእነዚህ ድርጅቶች መካከል ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካና ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተሻለ ትርፍ ከታክስ በፊት አፈጻጸም ያስመዘገቡ መሆኑን የሚጠቅሰው የኤጀንሲው መረጃ፣ የኢትዮጵያ ፕልፕና ወረቀት አክሲዮን ማኅበር፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፕሬሽንና ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዝቅተኛ አፈጻጸም እንዳስመዘገቡ ተገልጿል፡፡ በ2011 በጀት ዓመት ግን ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ከኪሳራ ወጥቶ አትራፊ መሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡

በ2012 የመጀመርያ ሩብ ዓመት እነዚህ አምስት ድርጅቶች አግኝተውት የነበረው ገቢ 2.27 ቢሊዮን ብር እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ከገቢ አንንፃር ድርጅቶች አጠቃላይ ገቢ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ የቀነሰ ሆኗል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች