Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮ ቴሌኮም ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ የቴሌኮም መስመሮች ሙሉ ለሙሉ ተቆርጠው እንደነበር አስታወቀ

ኢትዮ ቴሌኮም ከመቀሌ ጋር የሚያገናኙ የቴሌኮም መስመሮች ሙሉ ለሙሉ ተቆርጠው እንደነበር አስታወቀ

ቀን:

ኢትዮ ቴሌኮም በትግራይ ክልል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ የተቋረጡት የቴሌኮም አገልግሎት መስመሮች፣ ሆን ተብለው በመቆረጣቸውና ከዋና ጣቢያዎች ጋር የሚገናኙ መስመሮች በመጥፋታቸው እንደሆነ አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ / ፍሬሕይወት ታምሩ በትግራይ ክልል የተከሰተውን የቴሌኮም አገልግሎቶችና በመሠረተ ልማት ላይ የደረሰውን ጉዳት አስመልክተው ሐሙስ ታኅሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይ ላይት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በተለይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ጣቢያዎች በክልሉ በሽረና በመቀሌ እንደሚገኙ፣ በመቀሌ ከተማ ያለው ዋና ጣቢያ ከሌሎች አገልግሎት መስጫ መስመሮችና ምሰሶዎች ጋር የሚገናኝባቸው መስመሮች ሆን ተብለው ተቆርጠው ነበር ብለዋል፡፡

መስመሮቹ በመቆረጣቸው ሳቢያ ሙሉ በሙሉ በትግራይ ክልል የቴሌኮም አገልግሎት መጥፋቱን፣ በሰዓቱ በአውቶማቲክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት ማወቃቸውንና እንዲህ ዓይነት መቋረጥ እንግዳ ክስተት እንደሆነባቸው ያስታወቁት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ፣ ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወደ ቢሮ በመግባት ምክንያቱን ለማወቅ ጥረት ቢያደርጉም፣ ከጣቢያው ሠራተኞች ጋር መገናኘትም ሆነ ችግሩን መለየት እንዳልተቻላቸው አስረድተዋል፡፡

ለወትሮ የጣቢያው ሠራተኞች እንዲህ ያሉ የአገልግሎት መቋረጦች ሲያጋጥሙ ለማዕከል መቆጣጠሪያ በሳተላይት ስልክ ያሳውቁ ነበር ያሉት ወ/ት ፍሬሕይወት፣ ሠራተኞቹ እንዳላሳወቁና ሲደወልም ሳተላይት ስልኩን የሚመልስ አካል እንዳልተገኘ አስታውቀዋል፡፡

ነገር ግን የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች ቡድን የአገር መከላከያ ሠራዊት ወደ ሥፍራው ደርሶ እስከሚጣራ ድረስ ምንም ፍንጭ እንዳልተገኘና ትክክለኛ ምክንያቱ እዳልታወቀ ያወሱት ወ/ት ፍሬሕይወት፣ መንግሥት በቀኑ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ግን ችግር ተፈጥሮ ሊሆን እንደሚችል መገመታቸውን ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ክልል በአገር መከላከያ ሠራዊትና በትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ መካከል ከጥቅምት 24 ቀን 2013 .. ጀምሮ ሲደረግ በነበረው ጦርነት፣ ወቅት፣ በአገሪቱ 39.8 ቢሊዮን በላይ የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረው እንደነበር ተቋሙ አስታወቋል፡፡ እነዚህ ጥቃቶች የአገልግሎት ክልከላ (Disturbed Denial of Service /DDOS) ያልተፈቀደ መረጃን ለማግኘት መሞከር (Unauthorized Access) መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በቀን እስከ 3.7 ቢሊዮን ያህል የሳይበር  ጥቃቶች ሲሰነዘሩ እንደነበር በማስታወስ፣ በአማካይ በቀን 3.8 ቢሊዮን ጥቃቶች ይሰነዘሩ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ ጥቃቶቹ ይሰነዘሩ የነበረውም በመንግሥት አገልግሎት መስጫና ገጾች ላይ፣ በትምህርት ተቋማት ሥርዓትና ገጾች ላይ፣ በኢትዮ ቴሌኮም ሥርዓትና መሠረተ ልማቶች ላይ፣ በብሮድካስት ሚዲያ ተቋማት ሥርዓትና ገጾች ላይ፣ እንዲሁም በፋይናንስ ተቋማት ሥርዓትና ገጾች ላይ እንደነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የቴሌኮም አገልግሎት ሆነ ተብሎ ሠራተኞቹ እንዳይገኙና ጥበቃዎቹም በግዴታ ቦታቸውን እንዲለቅቁ ተደርገው አገልግሎቱ እንዲቋረጥ የተደረገው በትግራይ ልዩ ኃይል ነው ብለው፣ የኤሌክትሪክና የቴሌኮም መስመሮችን በመቁረጥና በማጥፋት እንደነበር ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አስረድተዋል፡፡ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል እንደነበር ግምቱ ባይታወቅም፣ ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰ ግን ጠቁመዋል፡፡

ይሁንና አገልግሎቱን ለመመለስ በተደረገው ጥረት እስካሁን በዳንሻ፣ በሁመራ፣ በማይካድራ፣ በቱርካ፣ በማይፀብሪ፣ እንዲሁም በቅርቡ በኮረም አገልግሎት መጀመሩን፣  በአላማጣ ደግሞ ሙሉ የቴሌኮም አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ለድርጅቱ ባለሙያዎችና ኃላፊዎች አገልግሎት ሲቋረጥ መልዕክት የሚልክ ሥርዓት መኖሩንና ይኼ ሥርዓት መልዕክት ሲልክ ለምን እንደተቋረጥ ለማወቅ አለመቻሉን፣ የኃይል አቅርቦት ችግር ቢሆን ኖሮ፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚገኘው ኃይል ሲቋረጥ ወዲያውኑ የሚነሳ ጄኔሬተር እንዳለና ነዳጁ 70 በመቶ ላይ ሲደርስ በየጊዜው እንደሚሞላ፣ እሱም ባይሠራ ጣቢያዎቹ በባትሪ 72 ሰዓታት አገልግሎት እንደሚሰጡ፣ ይኼም ባይሆን እንኳን በኢንፍራሪድ የሚሰጠው አገልግሎት ለሰዓታት ማገልገል የሚችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከአዲስ አበባ በተደረጉ የማጣራት ሥራዎች እነዚህ ምልክቶች ባለመታየታቸው የተቆረጡ መስመሮች መኖራቸው የታወቀውና በጥገና ለመመለስ እየተከናወነ ያለው ሥራ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት መቀሌን ከተቆጣጠረ በኋላ እንደሆነ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...