Thursday, June 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የሞያሌ የጋራ ፍተሻ ጣቢያ የኢትዮጵያንና የኬንያን ንግድ ለማቀላጠፍ እንደሚያግዝ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዳር 30 ቀን 2013 .. ተመርቆ የተከፈተው የኢትዮጵያና የኬንያ የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ፣ የሁለቱን አገሮች ንግድ ለማቀላጠፍ እንደሚያግዝ ተገለጸ። የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና በኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ነው የተመረቀው፡፡ ሁለቱን አገሮች የሚያገናኘው ሞያሌ የጋራ ፍተሻ ጣቢያ የላፕሴት ፕሮጀክት አካል ሲሆን፣ ከናይሮቢ በስተሰሜን 800 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ ደግሞ በስተደቡብ 780 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

የጋራ ፍተሻ ጣቢያው ግንባታ እ.ኤ.አ.፣ 2018 ቢጠናቀቅም፣ ጣቢያውራውን በብቃት ለማከናወንና አሠራሩን ለማዘመን የዘመናዊ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሣሪያዎች ገጠማ ሲካሄድ መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ግንባታ 329 ሚሊዮን ዶላር እንዲገነባ የታቀደው በኬንያ በኩል ከሜሪሊ ወንዝ እስከ ሞያሌ ድረስ 438 ኪሎ ሜትር፣ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ 300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው አስፋልት መንገድ አካል ነው፡፡

የግንባታው የመጀመርያው ዙር ወጪ በአፍሪካ ልማት ባንክ የብድር ድጋፍ፣ በአውሮፓ ኅብረትርዳታ፣ በኢትዮጵያና በኬንያ መንግሥታት መዋጮ የተሸፈነ መሆኑ ታውቋል። በሁለቱም ወገኖች በኩል ያለውን የተቀናጀ የድንበር አስተዳደር የአሠራር ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል፣ በእንግሊዝ መንግሥት በተሸፈነና ክፍለ አኅጉራዊ የንግድ ድርጅት በሆነው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ በኩል በተደረገ ወጪ ልዩ ልዩ ተግባራት መከናወናቸው ተገልጿል፡፡

እነዚህም የጋራ የፍተሻ ጣቢያ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋትና አሠራሩ እንዲሳለጥ ማድረግ፣ የተለያዩ የሕግ ሰነዶችን ማዘጋጀትና ማዋሀድ፣ በድንበር አካባቢ ለሚሠሩ ተቋማት የአቅም ግንባታ መስጠት፣ የሴት ነጋዴዎችን ግንዛቤ ማዳበርና ድንበር ዘለል የንግድ አሠራሮች እንዲጎለብቱና ተግባራዊ እንዲሆኑ የመደገፍ ሥራዎችን እንደሚጨምሩ ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የጠበቀ የኢኮኖሚ ትስስር ለሕዝቦቻቸው የጋራ ጥቅም፣ እንዲሁም ለጎረቤት መንግሥታት ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች በመካከላቸው አስደሳች የሆነ የኢኮኖሚየዲፕሎማቲክ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ደስታ የሚሰማቸው መሆኑን፣ አዲስ አበባና ናይሮቢ እ.ኤ.አ. 2018 በደረሱት ስምምነት መሠረት በግብርና ዘርፍ ግንኙነታቸውን ለማዳበር፣ በቱሪዝም፣ በወታደራዊ ጉዳዮች፣ በትራንስፖርትናመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመተባበር መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ መገንባት ከፍተኛርምጃ መሆኑን፣ በሁለቱ አገሮች መካከል የሚካሄደውን የዕቃና የጉዞ ምልልስ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና አስተማማኝ እንደሚያደርግ ሙሉ እምነታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አስታወቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ኬንያታ በበኩላቸው፣ ዘመናዊው የጋራ የፍተሻ ጣቢያ የሁለቱን አገሮች ንግድ በማፋጠንናድገትን በማስፈን ረገድ በኩል የጎላ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። በተጨማሪም መንግሥታቸው በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የንግድ ትስስር እንዲዳብር ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱን ገልጸዋል፡፡ ከሜሪሊ ወንዝ እስከ ሞያሌ ድረስ የተገነባው 438 ኪሎ ሜትር መንገድና በቀደም የተመረቀው የጋራ የፍተሻ ጣቢያ መገንባት፣ የሁለቱን አገሮች የንግድ ልውውጥን እንደሚያሳድግና የቀጣናውን ፀጥታ እንደሚያሻሽል ጠቁመዋል፡፡

በኬንያ የእንግሊዝ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጃን ማርዮት የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ የክፍለ አኅጉሩን ንግድ በማስተሳሰር የጎላ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት ኬንያ ለምሥራቅ አፍሪካ መተላለፊያ እንድትሆን በማሰብ አራተኛውን የጋራ የፍተሻ ጣቢያ እንዲገነባ ድጋፍ ማድረጉን፣ ይህንን በማድረጉ ኬንያ ንግዷን ከኢትዮጵያና ከላፕሴት ኮሪዶር ጋር በማስተሳሰር የሥራ ዕድል በመፍጠር ኢኮኖሚዋን ልታሳድግ እንደምትችል አክለዋል፡፡

የፍተሻ ጣቢያው በሁለቱ አገሮች መካክል ያለውን የጉምሩክ አስተዳደር ለማሻሻል፣ እንዲሁም በኬንያና በኢትዮጵያ የጋራ ድንበሮች የሚከናወነውን ሕገወጥ ንግድና ዝውውር ለመቀነስ እንደሚረዳ በሥነ ሥርዓቱ ላይ መገለጹ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ ከኢትዮጵያ ወደ ሞምባሳና ላሙ ወደቦች የሚደረገውን አኅጉራዊ ግንኙነት መተላለፊያ በመሆን እንደሚያገለግል፣ አዲሱና ዘመናዊ መሸጋገሪያ በላጋናሲሲ ሕገወጥ መተላለፊያዎች የሚካሄደውን ሕገወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር በማስቀረት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ፀጥታ በማስፈንና ንግዱን ወደ ሕጋዊነት ለማምጣት እንደሚያግዝ ተነግሯል፡፡

ምንም እንኳን ኬንያና ኢትዮጵያ የክፍለ አኅጉሩ ግንባር ቀደም የኢኮኖሚ መሪ ቢሆኑም፣ በመካከላቸው ያለው የንግድ ግንኙነት በዘመናዊ ትራንስፖርትናመገናኛ ዕጦት ምክንያት ግንኙነቱ የሚጠበቀውን ያህል አልነበረም ተብሏል፡፡ ሆኖም የሞያሌ የጋራ የፍተሻ ጣቢያና በሁለቱ አገሮች መካከል የተዘረጉት የተሻሻሉ የመገናኛ መንገዶች ይህን እንደሚቀይሩት ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡

ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ እ.ኤ.አ. 2019 በሰባት የድንበር ማቋረጫዎች የጋራ የፍተሻ ጣቢያዎች እንዲገነቡ ሐሳብ በማቅረብና በመገንባት የተሳተፈ መሆኑ፣ የድንበር ማቋረጫዎቹን ለማለፍ የሚፈጀውን ጊዜናትራፊክ ፍሰት ለማየት በተደረገው ጥናት ማቋረጫዎቹ በመመሥረታቸው ቀደም ሲል ይፈጅ ከነበረው ጊዜ 70 በመቶ እንደቀነሰ አስታውቋል፡፡

የትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍራንክ ማትስረት ወደፊት በኬንያ ሌላ የጋራ የፍተሻ ጣቢያ እንደሚኖር፣ ለሁለቱ የክፍለ አኅጉሩ ግንባር ቀደም ኢኮኖሚ መሪ አገሮች የንግድ ግንኙነት እንደሚዳብር ገልጸዋል፡፡ የድንበር ማቋረጫዎቹን ለማለፍ የሚፈጀውን ጊዜ 30 በመቶ፣ በድንበር በሚሰጡ አገልግሎቶችና የመሠረተ ልማት አቅርቦቶች የእርካታ ደረጃ 70 በመቶ እንደሚያድግ ያላቸውን እምነት አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች