Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበትግራይና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የታየው የምግብ ዋጋ ጭማሪ አገራዊ የዋጋ ግሽበቱን ማባባሱ...

በትግራይና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የታየው የምግብ ዋጋ ጭማሪ አገራዊ የዋጋ ግሽበቱን ማባባሱ ተገለጸ

ቀን:

በአገር ውስጥ በሚገኙ 119 የተመረጡ የገበያ ቦታዎችን ላይ የሚገኝ ጥናትን መሠረት አድርጎ በሚቀርበው የዋጋ ግሽበት ሁኔታ ሪፖርት፣ በኅዳር ወር በምግብና ምግብ ነክ ባልሆኑ ክፍሎች ላይ ለታየው የዋጋ ጭማሪ፣ መረጋጋት የሌለባቸው የትግራይና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች አስተዋጽኦቸው ከፍተኛ እንደነበረ ተገለጸ፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ የኅዳር ወር 2013 ዓ.ም. የአገር አቀፍ ጠቅላላ የችርቻሮ ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ፣ ከኅዳር ወር 2ዐ12 ዓ.ም. ጠቅላላ ኢንዴክስ ጋር ሲነፃፀር በ19.0 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ለዚህ ጭማሪ አስተዋጽኦ ያደረጉት በቅደም ተከተል ሲቀመጡ ትግራይ 30.3 በመቶ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ 28.7 መቶ፣ ጋምቤላ 26.9 በመቶ፣ ደቡብ 26.6 ከመቶ ሲሆኑ፣ ሌሎችም እንደ ቅደም ተከተላቸው ጭማሪ በማሳየታቸው እንደሆነ አኃዛዊ ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም በወርኃዊ ሪፖርቱ እንደተመለከተው፣ ሁሉም ክልሎች በምግብ ኢንዴክሶቻቸው ላይ ጭማሪ አሳይተዋል፡፡ በትግራይ ክልል ግን የታየው ጭማሪ በአፋር ክልል ከታየው 18.2 በመቶ በእጥፍ ጨምሮ 36.8 በመቶ መሆኑ ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የታየው 35.0 በመቶ ጭማሪ በአማራ ክልል ከታየው 23.1 በመቶ የራቀ እንደሆነ የምግብ ኢንዴክስ መረጃው ያመለክታል፡፡

የኅዳር ወር 2013 ዓ.ም. አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር 2012 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር በ19.0 በመቶ ከፍ ብሏል፡፡ ያለፈው ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር 2012 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር በ22.1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በኅዳር 2013 ዓ.ም. አንዳንድ የእህል ዓይነቶች መጠነኛ ቅናሽ ያሳዩ ሲሆን፣ ለምግብ ዋጋ ግሽበት መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡ አትክልትና የተወሰኑ የጥራጥሬ ዓይነቶች መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ ሲያስመዘግቡ በሌላ በኩል ስኳር፣ ከውጭ የሚገባ የምግብ ዘይት፣ የድንችና የቡና ዋጋ ጭማሪ በማሳየታቸው ለዋጋ ግሽበት ምጣኔ መጨመር አስተዋጽኦ ማድረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

በሌላ በኩል ምግብ ነክ ያልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የኅዳር ወር 2013 ዓ.ም. የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር 2012 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር የ15.1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ምግብ ነክ ካልሆኑ የኢንዴክሱ ክፍሎች የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከፍ እንዲል ካደረጉት ዋና ምክንያቶች ውስጥ በተለይም አልኮልና ትምባሆ፣ አነቃቂዎች ማለትም ጫት፣ የቤት እንክብካቤና ኢነርጂ (ማገዶና ከሰል)፣ የቤት መሥሪያ ዕቃዎች፣ ሕክምናና ጌጣጌጥ (ወርቅ) ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ነው፡፡

አዲስ አበባ በንፅፅር ከሌሎች የክልል ከተሞች ጋር ተቀራራቢ የሚባል የዋጋ ግሽበት አስተዋፅኦ ማድረጓ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም በአዲስ አበባ የምግብ ኢንዴክስ ላይ አስተዋጽኦው 18.6 በመቶ እንደሆነ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በኤልያስ ተገኝ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...